Audio Player

በኅብርቱ ልዩ ልዑክ ስታቭሮስ ላምብሪኒዲስ መሪነት በአዲስ አበባ በቅርቡ የተካሄዱት ውይይቶች የሕግ የበላይነት መከበር፣ የእስረኞች ይዞታና መንግሥቱ በያዘው የልማታዊ መንግሥት አቅጣጫ የዜጎች የምጣኔ ሀብት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚነቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በሰብዓዊ መብት ጉዳይ ላይ አስተያየት የሚሰጡ ጸሐፊዎች “ኢዮጵያ ውስጥ ያለውን የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ችግር አስረድተናቸዋል” ብለዋል።

በኅብርቱ ልዩ ልዑክ ስታቭሮስ ላምብሪኒዲስ መሪነት በአዲስ አበባ በቅርቡ የተካሄዱት ውይይቶች የሕግ የበላይነት መከበር፣ የእስረኞች ይዞታና መንግሥቱ በያዘው የልማታዊ መንግሥት አቅጣጫ የዜጎች የምጣኔ ሀብት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ነው።

የአውሮፓ ኅብረት ከሦስት ቀናት በፊት ያወጣው መግለጫ የውይይቱን አንኳር ነጥቦች የያዘ ነው። በኢትዮጵያ በተለይ የዜጎች መብትና የአስተዳድር ሁኔታን እንዲሁም ለወጣቶች የሥራ እድል መፍጠርና በስደትና ፍልሰት ዙሪያ አብሮ ለመሥራት የሚያስችሉ የጋራ ማእቀፎችን በመገንባት ዙሪያ ያተኩራል።

የልዑካን ቡድኑን የመሩት የኅብረቱ ልዩ ወኪል ስታቭሮስ ላምብሪኒዲስ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በተጨማሪ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ካሳ ተክለብርሃን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አጣሪ ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳን ማነጋገራቸው በመግለጫው ተጠቅሷል።

በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ይዞታን ከገዥው ፓርቲና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ተነጋግረዋል። በዚህ ስብሰባ ከተገኙት መካክል በኢትዮጵያ ትልቁ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት መድረክ ይገኙበታል።

መድረክን ወክለው ከለኡካን ቡድኑ ጋር ከተነጋገሩት መካከል አንዱ የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጥሩነህ ገምታ ሲሆኑ በነበረው ውይይት በርካታ ጉዳዮች መነሳታቸውን ገልፀዋል።

“በሀገራችን ስላጋጠሙት ችግሮች፣ በተለይም ደግሞ የዴሞክራሲ ምሕዳሩ መጥበብና ሰብዓዊ መብትን አስመልክቶ እንዲሁም በሀገሪቱ ስላሉት የተለያዩ ችግሮች ተወያየትናል” ይላሉ የመድረኩ አቶ ጥሩነህ።

አቶ ጥሩነህ በተነሱት ጉዳዮች ላይ ፓርቲው ያለውን አቋም በማስረጃ ጭምር እያጣቀሱ በዝርዝር መወያየታቸውን ተናግረዋል። ሌላው ይህ የልኡካን ቡድን ካነጋገራቸው መካከል በእስር ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት (መድረክ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር፣ የኦሮሞ ፌደላራዊ ኮንግረስ (ኦ.ፌ.ኮ) ሊቀመንበርና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የረጅም ዓመት የፖለቲካ ሳይንስ መምሕር የነበሩት ዶ/ር መረራ ጉዲና ጠበቃ አቶ ወንድሙ ኢብሳን ነው።

አቶ ወንድሙ የልኡካን ቡድኑ የዶ/ር መረራን ጉዲናን ክስ በተመለከተ ጥያቄዎች እንዳቀረቡላቸው ይናገራሉ። ቡድኑ መንግሥትን ሲያነጋግር ዶ/ር መረራ በሽብር መከሰሳቸውን እንደገለፀላቸውና ክሱም በሽብር እንደሆነ ጠቅሰው እንደጠየቋቸው ግልፀው፤ ዶ/ር መረራ በሽብር አለመከሰሳቸውን ከሽብርና ከሽብርተኛ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው የሚያዩትን ችግር በሰላማዊ መንገድ የሚቃወሙ ምሑር ፖለቲከኛ መሆናቸውን ማስረዳታቸውን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ውይይቱን በተመለከተ የነበረውን ሁኔታ እንዲነግሩን ለመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ጥያቄ አቅርበን ነበር። ዶ/ር ነገሪ በውይይቱ ውስጥ እንዳልተሳተፉና ከሰብዓዊ መብት ጋር በተያያዘ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት ስላሉ ጉዳዩን አጣርተው እንደሚነግሩን ቃል ገብተዋል። እኛም መንግሥትን ምላሽ እንደሰጠን የምናቀርብ መሆኑን ገልጨላቸዋለሁ።

የኅብረቱ የሰብዓዊ መብት ልዑካን ቡድን ካነጋገራቸው ኢትዮጵያን መካከል በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ታሥረው የተፈቱ የኢንተርኔት ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ይገኙበታል። “በኢትዮጲያ ስላለው የሰብዓዊ መብት አያያዝና ፖለቲካዊ ሁኔታ፣ እንዲሁም አንዳንዶቻችን በእስር ቤት ስለነበረን ቆይታና የእስረኞች አያያዝን በተመለከተ ከልዑካን ቡድኑ ጋር ተወያይተናል፡፡” የሚለው በአምቦ ዩኒቨርስቲ ወሊሶ ካምፓስ መምሕሩ ነባራዊ ሁኔታውን ለማስረዳትና በቀጣይ የተሻለ ነገር እነዲመጣ ያስችላል ያልነውን ምክረ ሐሳብ አቅርበናል ብሏል።

በዚህ ጉብኝት ወቅት ስታቭሮስ ላምብሪኒዲስ የዓለም አቀፉን የፍልሰት ድርጅት ሥራዎች ለማመልከትም ስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ያሉበትን ሁኔታ በጉብኝታቸው አካተዋል። በስተመጨረሻም በኢትዮጵያ ማእከላዊ የምርመራ ጣቢያ ተገኝተውም የማቆያ ጣቢያውን ጎብኝተዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ጨመሮ በፀረ ሽብር ዐዋጁና በሌሎች ተመሳሳይ ክሶች በእስር ላይ የሚቆዮ ሰዎች ላይ የሚደረጉ ምርመራዎችን አስመልክቶ ከማዕከላዊ ከፍተኛ የእስር ቤቱ ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል።

በእስር ቤቱ የሰቆቃ ይዞታ ይታያል፣ መብቶች አይከበሩም የሚሉ ውንጀላዎችን በገለልተኛ ወገን ማጣራት እንደሚያስፈልግም ለእስር ቤቱ አመራር አስረድተዋል።

የአውሮፓ ኅብረት ልዩ ልዑክ ስታቭሮስ ላምብሪኒዲስ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ወቅት በሀገሪቱ ላለፈው አንድ ዓመት የዘለቁ ሰላማዊ ሰልፎች ያስተጋቧቸን የአስተዳድር፣ የመብትና የምጣኔ ሀብት ጥያቄዎች አስመልክቶ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይተዋል።

ከዚያም ተከትሎ በሀገሪቱ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በቁጥጥር ስር የሚገኙ እስረኞች ይዞትና መብት አስመልክቶም ከዐዋጁ አጣሪ ቦርድ ጋር ተነጋግረዋል። ቦርዱ በተለይ የእስር ይዞታዎች እንዲሻሻሉ ያቀረባቸው ሐሳቦች ተቀባይነት አግኝተው አፈጻጸሙ እንዲቀላጠፍም ጠይቀዋል።

የአውሮፓ ኅብረቱ ልዑክ በኢትዮጵያ ባለፉት ዐስር ዓመታት የተመዘገቡ የምጣኔ ሀብት ዕድገቶችን አወድሰው፤ በተለይ የፖለቲካና አስተዳድራዊ መሻሻሎች፤ እድገቱን የሚያጸኑ መሰረቶች ናቸው ብለዋል። ወጣቶች እንዳይሰደዱ የትምህርትና የሥራ እድልን በሀገር ውስጥ መፍጠር በጋራ የአውሮፓ ኅብረትና ኢትዮጵያ የሚሰሩባቸው ስልታዊ ግንኙነቶች ናቸው ብለዋ ስታቭሮስ ላምብሪኒዲስ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው