የማጠቃለያው መግቢያ

እስኪ አንድ ጥያቄ እንመልስ፤ እንዴት መሽቶ ይነጋል? እነዚህ ወገኖች እንዴት ቻሉት? እንዲህ ያለው ስቃይ እንዴት ሌሎችን ያስደስታል? በህይወት ያለ ሰው በኤሌክትሪክ ማቃጠል ምን ማለት ነው? ሰውን ማኮላሸት ምን የሚሉት ጭካኔ ነው? ሰውን ሰቅሎ መርሳት፣ ገልብጦ ሲደበድቡ ማደርና ማቃጠል፣ ተነግሮ፣ ተወርቶ፣ የማያልቅ ጉድ! እንዴት ነው እነዚህ ሰዎች የሚያስቡት? ሕዝብ ስሜት ያለው አይመስላቸውም? የወላድንና የህጻናትን እንባና የፈጣሪን ፍርድ ለጊዜው ወደ ጎን ቢሉትም፣ ነገሮች በዋይታ የሚዘልቁ ሆነው ስለመሰራታቸው እርግጠኞች ናቸው? የትግራይ ሕዝብስ ለምን ዝም ትላለህ? የትግራይ ምሁራን ይህ እርካታን ይሰጣችኋል? ከመጠርጠር እስከ መመርመር፣ እስከ ማሰር፣ መክሰስ፣ መፍረድና ይቅርታ ማስጠየቅ በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) እየተከናወነ፤ የአሳሪው ቋንቋ ትግርኛ፤ የታሳሪው ኦሮምኛና አማርኛ እየሆነ ባለባት አገር ኢትዮጵያዊ ነን የሚሉ የትግራይ ልጆችም ሆነ የቀድሞ የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ዝምታ አልበዛም? ወዴት እየሄድን ነው? ያሳስባል፣ ያስፈራል፣ እጅግ ያስደነግጣል።

የማጠቃለያው መግቢያ እስኪ አንድ ጥያቄ እንመልስ፤ እንዴት መሽቶ ይነጋል? እነዚህ ወገኖች እንዴት ቻሉት? እንዲህ ያለው ስቃይ እንዴት ሌሎችን ያስደስታል? በህይወት …[ሙሉውን አስነብበኝ / read more]