May 1, 2017

ከቻርተሩ ጥቂቶቹ,,,,

5. ስያሜ
1) የከተማው ስም ፊንፊኔ ከአዲስ አበባ ጋር እኩል መጠሪያ ይሆናል፡፡
2) የከተማው ሕጋዊ ስም በፅሁፍ ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ተብሎ ጥቅም ላይ መዋል
ይኖርበታል፡፡
7. የስራ ቋንቋ
የከተማው አስተዳደር የስራና ኦፊሴላዊ ቋንቋ አማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ነው፡፡
6)ፊንፊኔ/አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ዋና ከተማ ሆና ታገለግላለች፡፡
3) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና የከተማው ነዋሪ የኦሮሞ ተወላጆች አደባባዮች፣
ማዕከላት፣ አዳራሾች፣ ስታዲየሞች፣ ሜዳዎች…ወዘተ አገልግሎት ማግኘት ሲፈልጉ
ቅድሚያ የመጠቀም ሙሉ መብት ይኖራቸዋል።……..

ይቺን ያገኘሁት ከወዳጄ አንዋር ገጽ ላይ ነው። ሙሉ ቻርተሩ ያላችሁ ወዳጆች እስቲ በውስጥ መስመር አድርሱኝማ…

እዚህ ላይ በኔ ምልከታ 1 ፣ 2 ፣ 7 እና 6 ላይ የተቀመጡት ሃሳቦች በግሌ ችግር አይመስሉኝም… በኔ ሃሳብ አዲሳባ ብቻ ሳትሆን መላው ኢትዮጵያ ከአማርኛ ጎን ለጎን ኦሮምኛ አቀላጥፋ ብትናገር ደስታዬ ነው።

በተራ ቁጥር 3 ላይ የተቀመጠው ግን በጣም አስቂኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ሃገሪቷ መላው ኢትዮጵያ የመላው ኢትዮጵያውያን ሆና ሳለ ቅድሚ ለእንትን ተወላጆች ማለት ምን ማለት ነው? ያለ ምንም ተጨማሪ መስፈርት ኦሮሞ ስለሆኑ ብቻ ስታድየም፣ ስብሰባ አዳራሽ፣ አደባባዮች፣ ወዘተን ቅድሚያ የመጠቀም መብት ይኖራቸዋል። … ይሄ እብደት ይባላል የለየለት እብደት።

እኔ ብምኖርበት እንግሊዝ እንኳ እኔ ተሰድጄ የመጣሁት ሰውዬ ከእንግሊዛዊው እኩል መብት ነው ያለኝ። ምንም ነገር ላይ ለእንግሊዛውያን ቅድሚያ የሚባል ነገር የለም። የተመሳሳይ ሃገር ልጆች በዘር ማንነታቸው አንዱን ቀዳሚ አንዱን ተከታይ ናቸው ብሎ ማወጅ መንግስታዊ እብደት ካልሆነ ሌላ ምንም ቃል የለውም!!!

ዘሐበሻ