” የኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ላይ ያለውን ሕገ-መንግስታዊ ልዩ ጥቅምን አስመልክቶ የተዘጋጀ” ( Concept-Paper-for-Special-Interest-Over-Finfinne ) የሚል አንድ ሰነድ እና አዲስ አበባ ላይ የ”ኦሮሞዎች” መብትን እንዲያስጠበቅ ተብሎ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ አነበብኩ። ሰነዱም ሆነ አዋጁም በኦፌሴል በማን እንደተዘጋጀ ግልጽ አይደለም። ሆኖም የህዝቡን ስሜት ለመለካት አስቀድሞ በኦህዴድ አመራሮች የተለቀቀ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ።

በነዚህ ሰነዶች ላይ የተቀመጡ ሐሳቦች አዲስ ሐሳቦች አይደለኡም። እንደ ጸጋዬ አራርስ፣ ጃዋር መሐመድ ያሉ፣ በዉጭ የሚገኙ አካራሪና ጸንፈኛ የኦሮሞ ፈርስት ሰዎች በተደጋጋሚ ሲያንጸባርቋቸው የነበሩ ሐሳቦች ናቸው። ዉጭ ያሉ የኦሮሞ ፈርስት ሰዎችም፣ ከኦህዴድ ጋር እጅና ግኗት ሆነው እንደሚሰሩም የታወቀ ነው። እነዚህን ሰነዶችም በኦሮሞ ፈርስት ሰዎች ተዘጋጅተው፣ በነ ኦቦ ለማ መገርሳ በኩል የሕዥብ አዎንታ ሳይጠየቅ በፓርላማ እንዲጸድቅ የታሰቡ ሰነዶች ናቸው ።

በነገራችን ላይ ኦህዴዶችም ሆነ ኦነጎች፣ ኦሮፎ ፈርስቶችና ዉጭ ያሉትም ሆነ አገር ዉስጥ ያሉ የኦሮሞ አክራሪዎች ትልቁ ግባቸው አዲስ አበባን እና አካባቢዋን በሃይል oromized ለማድረግ ነው። በአዲስ አበባም ሆነ በሸዋ የሚኖረው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ራሱን ኦሮሞ ብሎ የማይጠራ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ለነርሱ ጉዳያቸውም አይደለም። “ፊንፊኔ የኦሮሞ ናት፤ሌላው በኦሮሞው ፍቃድ ነው የሚኖረው” የሚል እምነት ነው ያላቸው። በአዲስ አበባ የሚኖር 10% የሚሆን የሜጫ ቱሉማ ኦሮሞ የሚሉት አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ፣ መብቱ እንዲከበርለት በሚል አዲስ አበባ ወደ ኦሮምያ እንድትጠቃለል ሲጠይቁ፣ 90% የሚሆነው አፋን ኦሮሞ የማይናገረው ሕዝብ ኦሮሚያ ዉስጥ በመግባቱ መብቱ እንደሚረገጥ ግን ሊታያቸው አልቻለም። 85% የሚሆነው የአዳማ፣ 82% የሆነው የደብረዘይት ፣ 77% የሚሆነው የሻሸመኔና የዝዋይ ፣ 65% የሚሆነው የጂማ ህዝብ … አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ ስላልሆነ በአሁኑ ወቅት መብኡ እየተረገጠ እንደሆነ ማየት ተሰኗቸዋል።

አስቡት አዳማ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ነው የምትባለው። ጨፌ የሚሉት ምክር ቤታቸው የሚሰበሰበው በአዳማ ሆኖ፣ በጨፌው ውስጥ የሚነገረው አፋን ኦሮሞ ብቻ ስለሆነ ፣ የአዳማ ህዝብ ጨፌው ውስጥ ምን እየተደረገ እንደሆነ እንኳን መከታተል አልቻለም። ጨፌው የኦሮሞዎች ምክር ቤት እንጅ በክልሉ የሚኖረው ህዝብ ምክር ቤት አይደለምና።፡

በአዳማ ማዘጋጃ ቤት ጉዳይ ለማስፌጸም የግድ ፎርሞች በአፋን ኦሮሞ መሞላት አለባቸው። የከተማዋ ነዋሪ በብዛት አማርኛ ተናጋሪ ሆኖ የከተማዋ የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ ብቻ መሆኑ ምንም ያህል በዘር ላይ የተመሰረተ አፈና እንዳለ የሚያመላክት ነው።

ሌላው እነዚህ ሰዎች ስለ ገበሬው መፈናቀል ያወራሉ። ለመሆኑ ገበሬው የመሬቱ ባለቤት እንዲሆን የማይፈለጉ መሆናቸው ምን ያህል ሰው እንደሚያወቅ አላውቅም። አንድ የኦሮሞ ብሄረተኛ “ገበሬው የመሬቱ ባለቤት ይሁን፣ መሬት ለአራሹ ይሁን” የሚለውን መርህ ተቀብሎ ሲናገር ሰምቼ አላውቅም። መሬትን መሸጥና መለወጥ ከተቻለ አማራው ይወስድብናል የሚል መሰረት የሌለው ፍርሃት አለባቸው። ይሄም የሚያሳየው ሰዎቹ ለገበሬው ደንታ እንደሌላቸው ነው። የሚይስጨንቃቸው የገበሬው መፈናቀል፣ በገበሬው ላይ የሚደርሰው የሰብአዊመብት መጣስ ሳይሆን አቢሲኒያዎች ይየሚሏቸው መሬታችንን ወሰዱት፣ ኦሮሚያ ልትከፈል ነው የሚለው ነው።

በነዚህ ሰነዶች ዙሪያ የተነሱ ነጥቦችን በማንሳት አስተያየቶችን በስፋት እንሰጥበታለን። እኛ ጋር ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ አማራ ብሎ ነገር የለም። ይሄ መሬት የኦሮሞ ነው፣ ያ መሬት የትግሬ ነው፣ የሚለው ፖለቲካ የኋላ ቀር፣ ወደ ርስ በርስ ጦርነት የሚወስድ፣ በአስቸኳይ መስተካከል ያለበት መርዛማ ፖለቲካ ነው ብለን ነው የምናምነው። ሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው ብለን ነው የምንታገለው። አዲስ አበባ ወይም ፊንፊኔ፣ አዎን የኦሮሞዎች ናት። ግን ደግሞ የአማራዎችም ፣ የትግሬዎችም፣ የጉራጌዎችም፣ እንደኔ ያሉ የድብልቆቹም ናት።አዳማ የሁሉም ናቸው።፡መቀሌ የሁሉም ናት። ማን ነው መቀሌን የትግራይ ብቻ ያደረገው ? ወልቃይት አዎን የአማራ ናት። ወልቃይት የትግሬና የኦሮሞም ናት። ማንም ዜጋ በአራቱም የአገሪቷ ማ እዘናት ይሄ አገሬ ነው ብሎ ሳይሸማቀቅ፣ ሳይፈራ መኖር መቻል አለበት።

እነዚህ ሰነዶች በአዲአ አበባና በኦሮሞኢያ መካከል ያለዉን ችግር ለመፍታት በሚል ነው የተዘጋጁት። ግን እንድ መፍትሄ የቀረቡት ችግሮችን የበለጠ የሚያወሳስቡ ናቸው።፡በተለይም ደግሞ ለኦሮሞው ማህበረሰብ ትልቅ ጉዳትን የሚያመጡ ናቸው።፡

እሁሉም የሚበጀው ትልቁ መፍትሄ አሁን ያለው በዘር ላይ የተመሰረተ ፌዴራል አወቃቀር መቀየር ነው። በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ባሉ ኦሮሞች መካከል አለ የተባለው ችግር የሚፈታው፣ በተለይም አዲስ አበባና እና አራቱ የኦሮሚያ የሸዋ ዞኖች፣ እና የአማራው ክልል የሰሜን ሽዋ ዞኦን እና የከሚሴ ዞንን ያጠቃለለ፣ አፋን ኦሮሞና አማርኛ የሥራ ቋንቋ የሆኑባት፣ ሁሉም ዜጎንች እንደ እኩል የሚታዩባት፣ መሬት ለአራሹ የሆነበት፣ አዲስ ክልል በመፍጠር ነው። የድሮ ሸዋን አይደለም እየጠየቅን ያለነው። ግን ኦሮሞው ከሌላው እኩል ባህሉን ቋንቋዉን የሚያሳድግባት፣ ከሌላው ጋር ለዘመናት የነበረዉን ትሥር አጠናክሮ የሚቀጥልባት አዲስ ሸዋን ነው እየጠየቅን ያለነው።

እነዚህን እምነቶቻችን ለማስረዳት በዚሁ Concept-Paper-for-Special-Interest-Over-Finfinne በሚለው ሰነድ ፊንፊኔ በኦሮሚያ መቀላቀል እንዳለባት ለማሳየት የቀረቡ መከራከሪያዎችን በመጠቀም ሸዋ የሚባል ከዞህ በፊት የነበረ አዲስ አበባን ያጠቃለለ ክልል መቋቋም እንዳለበት ለማሳየት እንሞክራለን።