May 5, 2017 07:30

በቅድሚያ ከበርካታ መሰናክሎችና ፈተናዎች በኋላ ሥራዎቹን ለሕዝብ ጆሮ ስላበቃው ቴዲን እንኳን ደስ አለህ! ልለው እወዳለሁ፡፡ ጥሩ ሥራዎችን ሠርተህልናል ወደናቸዋል እናመሰግናለን! ተባረክ፡፡ በዐፄ ቴዎድሮስ ዘፈንህ አስለቀስከኝ፡፡
አንዳንድ ነገሮች አሉ እነሱን እናነሣለን፡፡ ከምቀኝነትና ከጥፋት ኃይሎች ተልእኮ የጸዳ ገንቢ አስተያየትና ትችት (Criticism) ይጠቅመዋልና ለግሱት፡፡ በዚህ ሥራው የተመቸኝን ነገር ከነምክንያቱ ልዘርዝር ብል አውየ  ላሳድራቹህ እችላለሁና ለሚያስተውል ሰው በግልጽ የሚታይ ነገር ነውና እሱን ትቸ ቅር ያሰኙኝን ነገሮች ብቻ አነሣለሁ፡፡ ቅኝቴ በሁለት መንገድ ነው፡፡ ባለፈው “የቴዎድሮስ ካሳሁን ዜና ያስነሣው ተቃውሞ ምንጩ ምንድን ነው? ዘፈንስ ኃጢአት ነውን?” በሚለው ጽሑፌ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እየጠቀስኩ “ዘፈን የተባለ ሁሉ ኃጢአት ነው አልተባለም! አይደለምም! ኃጢአት የሆነ ዘፈን አለ ያልሆነ ዘፈንም አለ!” ብየ መጻፌ  ይታወሳል? አሁን አንዱ መቃኛዬ ይሄ ይሆናል፡፡ ሁለተኛው መቃኛየ ከስሕተት አንጻር ይሆናል፡፡

በመጀመሪያው መቃኛዬ አዲሱ የቴዲ አልበም (የዘፈን ጥራዝ) ሲፈተሽ “ይሄ ዘፈን ኃጢአት ነው!” ተብሎ ሊባል የሚችል ያገኘሁት አንድ ዘፈን ብቻ ነው፡፡ እሱም በቁጥር 6ኛ ላይ የሚገኘው “ታሞልሻል!” የሚለው  ዘፈን ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ገጸ ባሕርይው አስቀድሞ የነበረችውን ትቶ ሌሎች ሴቶችን ሲወዳጅ ቆይቶ እንደሷ ማለትም እንደበፊተኛዋ አልሆን ስላሉት የተጸጸተን ገጸባሕርይ የሚገልጽ በመሆኑ ነው፡፡ እርግጥ ነው የገጸባሕርይውና የሴቲቱ ግንኙነት የትዳር ይሁን ከትዳር ውጭ ያለ ግንኙነት (በዘልማድ በስሕተት “የፍቅረኛነት  ግንኙነት” የምንለው ማለቴ ነው) የትኛው እንደሆነ አልተገለጸም፡፡ የትኛውም ቢሆን ግን ድርጊቱ ኃጢአት ነው፡፡

ግንኙነታቸው የትዳር ከነበረ በመፍታቱና ሌሎችን ሴቶች ሲወዳጅ በመቆየቱ ኃጢአት ሠርቷል፡፡ ምንም እንኳ መጨረሻ ላይ የተጸጸተና ወደ ቀደመችው ለመመለስ የፈለገ ቢሆንም ቅሉ፡፡ ግንኙነታቸው ከትዳር ውጭ የነበረ ግንኙነት ነው ከተባለ ደግሞ በሃይማኖት ከትዳር ውጭ የፍቅር ግንኙነት መመሥረት የተከለከለ በመሆኑ ኃጢአት ነው ዘፍ. 2 22, ዘጸ. 20 22, ዕብ. 13 4 ነገር ግን ግንኙነታቸው የእጮኝነት የነበረና ወሲባዊ ግንኙነትን ያልጨመረ ከነበረ ገጸባሕርይው ያሳለፈው ነገር ኃጢአት ስላልሆነ ዘፈኑም ኃጢአት አይሆንም፡፡ ይሁን እንጅ ከገጸባሕርይው አገላለጽ እንደምንረዳው ተመሥርቶ የነበረው ግንኙነት መስሎ የሚታየው “ገጸባሕርይው ኃጢአት  ሠርቷል!” ሊያስብለው ከሚችሉት ከላይ ከተገለጹት ከሁለቱ በአንደኛው ግንኙነት ውስጥ የነበረ እንደሆነ የሚያመዝን በመሆኑና መጨረሻ ላይ ቢጸጸትም የሠራው ሥራ ኃጢአት በመሆኑ ይሄንን ዘፈን “ኃጢአት ነው!” ልንለው እንገደዳለን ማለት ነው፡፡ ገጸ ባሕርይው ሌሎች ሴቶችን ቢያይ ቢያይ እንደሷ አልሆን ስላሉት መጸጸቱንና መመለስ መፈለጉን ስለገለጸነው እንጅ የመጀመሪያው እሷ ሆና ከእሷ ሌላ ሌሎች ሴቶችን ማየቱ ስሕተት መሆኑን አውቆ የተጸጸተና መመለስ የፈለገ ቢሆን ኖሮ አሁንም ዘፈኑ ኃጢአት አይሆንም ነበረ፡፡
ከዚህ ውጭ ያሉ በጾታዊ ግንኙነት ላይ የተቀነቀኑ ዘፈኖቹ ግን ገጸባሕርያቱ ዓይተው ወደዷቸውን የራስ የማድረግ ፍላጎትን የሚገልጹ፣ ውበትን ማለትም ሕንፃ እግዚአብሔርን የሚያደንቁ በመሆናቸው ገጸባሕርያቱን “ይሄንን በማድረጋቹህ ኃጢአት ሠርታቹሀል!” የሚላቸው የእግዚአብሔር ቃል ስለሌለ ኃጢአት አይደሉም፡፡ በቁጥር 4ኛ ላይያለው “አናኛቱ!”

የሚለው ዘፈን ግን ያጠራጥራል፡፡ ግንኙነቱ የከንፈር ወዳጅነት ግንኙነት ይመስላል፡፡

ከንፈር ወዳጅነት  ማለት የእጮኝነት ግንኙነት ማለት ስላልሆነ ይሄንን ዘፈን “ኃጢአት ነው!” ልንለው የምንችልበት ክፍተት አለው፡፡ ምክንያቱም ከትዳር ውጪ እንዲህ ዓይነት ግንኙነት መመሥረት ኃጢአት ስለሆነ፡፡ በተራ ቁጥር 2 ላይ ያለው “ሠምበሬ!” የሚለው ዘፈን ላይ በገጸባሕርይው ሕይዎት ውስጥ ሁለት ሴቶች ስላሉ ኃጢአት  የተፈጸመ ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን ገጸባሕርይው መጀመሪያውን የተዋት እሱ ስላልሆነና ተከድቶ ወይም ትታው የሔደችው እሷ በመሆኗ ወይም ስትወሰልትበት ስላገኛት ገጸባሕርይው እሷን ትቶ “እርም የሴት ነገር!” ብሎ ቆይቶ እንደገና ሌላ ሴት በመውደዱ ኃጢአት ሠራ ልንል አንችልም፡፡ ሚስት ወይም ባል ሚስቱ ወይም ባሏ ወስልታ ወይም ወስልቶ በተገኘ ወይም በተገኘች ጊዜ መፍታትና ሌላ ማግባት እንደሚቻል ጌታ በወንጌል ተናግሯልና ማቴ. 5 32 ፡፡ የዚህ ዘፈን ገጸባሕርይ የነበረው ግንኙነት በዘልማድ በስሕተት የፍቅረኝነት የምንለው ከነበረ ግን ጥላው የሔደችው ወይም የወሰለተችበት እሷ ብትሆንም እንኳ የነበረው ግንኙነት ኃጢአት በመሆኑ ዘፈኑን በኃጢአት በሆነ ዘፈንነት  ልንፈርጀው እንገደዳለን ማለት ነው፡፡

ከዚህ ሠምበሬ ከሚለው ዘፈን ሳንወጣ ግን አንድ ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር የዘፈኑ መልእክት ወርቁ በጣም ነው የተመቸኝ፡፡ ቴዲ በሰሙ የተናገረው ነገር ስለራሱ ከሆነ ግን ተሳስተሀል ልለው እፈልጋለሁ፡፡ ምክንያቱም ባለቤቱ አምለሰት ሙጨ ትግሬነቷ በእናቷ እንጅ ባባቷ ስላልሆነ፣ አባቷ አማራ ያውም ጎንደሬ በመሆናቸውና የአምለሰት ውበት ከመልኳ እስከ ጸጉሯ ከጸጉሯ እስከ ቁመናዋ ሁሉም ያባቷ ወይም ካባቷ የወሰደችው በመሆኑና የእናቷ ባለመሆኑ ነው ቴዲ የተሳሳተው፡፡ ያለውን ነገርና እውነታውን አላንጸባረቀምና፡፡ የአማራን ለትግሬ መስጠት ሆንበታል፡፡

በተራ ቁጥር 5 ላይ ያለው “መማፀኔ!” የሚለው ዘፈንም ችግሩ የገጸባሕርይው ባለመሆኑ ዘፈኑ ኃጢአት ሊሆን አይችልም፡፡ ሌላው ስለ ባለቤቱ አምለሰት የዘፈነው በተራ ቁጥር 10 የሚገኘው “ማራኪዬ!” የሚለው ዘፈን ምንም ችግር የለበትም፡፡  ብዙዎች እንዲህ ዓይነት ዘፈን ኃጢአት ይመስላቸዋል፡፡ የሚገርማቹህ ነገር ግን ፍቅራቸውን “ይገልጽልኛል!” ያሉትን ቃል ተጠበውና ተጨንቀው እያወጡ ፍቅራቸውን ለሚስቶቻቸው የሚገልጹ ሆነው እያለ ነው እንዲህ ዓይነቱን ዘፈን “ኃጢአት ነው!” የሚሉት፡፡ በዜማ ሲሆን ነው ኃጢአት የሚሆነው? “በአንደበት የምትናገሩትን ነገር በዜማ ካላቹህት ነው ኃጢአት የሚሆነው!” የሚለውን ሕግ ከየት አገኙት? ፍቅራቹህን ለሚስቶቻቹህ አትግለጡ የሚል ቃልስ የት ነው ያለው? ባልገባቸው ነገር ላይ ግትር ሲሉ ይገርመኛል፡፡

መጽሐፉ የሚለው “ሚስቶቻቹህን ውደዱ!” ነው የሚለው 2ኛ ቆላ. 3 19 በተራ ቁጥር 8 ላይ “እማ ዘንድ ይደር!” የሚለው ዘፈንም ከዚህ ዘፈን ጋር ይመሳሰላል፡፡ ዘፈኑ ካንቺ ሌላ ልሻም  የሚል በመሆኑ ዘፈኑ ኃጢአት ሊሆን የሚችልበት ምክንያት የለም፡፡ ኃጢአት የሚሆነው ገጸባሕርይው እንዲህ እያለ ያለው ከትዳር ውጪ በተመሠረተ ግንኙነት ውስጥ ሆኖ ግንኙነታቸው ወሲብን የጨመረ ከሆነ ነው፡፡ በተራ ቁጥር 3 ላይ “ማር እስከ ጧፍ!” የሚለው ዘፈንም የክቡር ደራሲ ሐዲስ ዓለምዓየሁ ድርሰት ፍቅር እስከመቃብር ድንቅ በሆነ መንገድና ቅኔ የተገለጸበት ዘፈን በመሆኑና መጽሐፉ የሚተርከው ታሪክንና የሰዎችን ሕይዎት በመሆኑና እንዲፈጸም የሚያበረታታው የሚገፋፋው ኃጢአት ባለመኖሩ ዘፈኑን ኃጢአት ነው ሊያስብል የሚችል ነገር የለም፡፡

በዚህ የቴዲ ሥራ ውስጥ የጾታዊ ግንኙነት ዜማዎች በዝቶ ታይቶኛል፡፡ ቴዲ በተመሳሳይ ርእሰ ጉዳይ ዘፈን ከሚደጋግም ይልቅ ከሀገርና ከታሪክ ዘፈኖች በተጨማሪ በተጨማሪ እንደ ባልደራሱና ኡኡታየ ያሉ ድንቅ ሥራዎችንም ቢጨምርልን እንዴት ጥሩ ነበር! እርግጥ ሠምበሬ የዚህ ዘይቤን የያዘ ቢሆንም አንሶናል፡፡ ሊዘፈንባቸው የሚገቡ ሌሎች በርካታ ማኅበራዊ ጉዳዮችም አሉና በአንድ አልበም ውስጥ የጾታዊ ግንኙነት ወይም በዘልማድ የፍቅር የምንለው ዜማ  ቢበዛ ከአራት በላይ መብለጥ ባይኖርበት መልካም ነው፡፡ የፍቅር ማለት የማልፈልገው ከማንም ጋር ስተናገድ
የወሲብ ስሜት ፍላጎትና ኃላፊነት የጎደለው ሕገወጥ የወሲብ ጉድኝት ሁሉ ፍቅር እየተባለ ቃሉ እጅግ አላግባብና በስሕተት ጥቅም ላይ እየዋለ ስለሆነና ፍቅር ማለት ይሄ ስላልሆነ ነው፡፡ ኃጢአት ከሚለው ዕይታ አንጻር ያለውን ቅኝታችንን በዚሁ እንቋጭና ወደ ሁለተኛው ቅኝታችን እንሻገር፡፡

ሌላኛው የቅኝት ዕይታችን ከስሕተት አንጻር ነው፡፡ በዚህ ቅኝት የቃኘኋቸው ሦስት ዘፈኖችን ነው፡፡ ኢትዮጵያን፣ ዐፄ ቴዎድሮስንና አደይን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ላይ ቅር ያሰኘኝ ሐረግ አለ፡፡ ሐረጉ እንደ ቴዲና ብዙዎቻቹህ ትክክል ነው፡፡ እንደ እኔ ዓተያይና እንደ አንዱ እውነት ግን ስሕተት ነው፡፡ የብዙዎቻቹህን ስሜት ላለመጉዳት ስል ሐረጉን ከመጥቀስ እቆጠባለሁ፡፡
ዐፄ ቴዎድሮስ ላይ የምለው ምንድን ነው መሰላቹህ ዜማው በዐፄ ቴዎድሮስ ዕረፍት ወይም መሠዋት ላይ እንደማተኮሩ  ለመሠዋቱ ምክንያት የሆነውን የከሀዲውን የባንዳውን የበዝብዝ ካሳን የኋላውን ዐፄ ዮሐንስ 4ኛን ነውረኛና ወራዳ የክህደት የባንዳነት ተግባርም በግልጽ መግለጥ እንኳ ቢያቅተው በቅኔ መግለጥ ነበረበት፡፡ ቴዲ “ዐፄ ቴዎድሮስና ደናቁርት አንባቢ ተችዎቻቸው!” የሚለውን ጽሑፌን አንብቦት ቢሆን ኖሮ በርካታ ግብአት ሊሆነው የሚችል ሐሳብ ያገኝ ነበረ፡፡ ትግሮቹ ግን ጭራሽ “ቴዲ መጀመሪያ ለዐፄ ኃይለሥላሴ 1ኛ ዘፍኗል ቀጥሎ ለዐፄ ምኒልክ ሁለተኛ ዘፍኗል አሁን ተራው የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ነበረ እሳቸውን ዘሎ ወደ ኋላ ሔዶ ለዐፄ ቴዎድሮስ 2ኛ ዘፈነ” ብለው አኩርፈዋል አሉ!

የዘለለውስ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛን ብቻ አይደለም ዐፄ ተክለ ጊዮርጊስንም ነው ዘሎ ዐፄ ቴዎድሮስ ላይ ያረፈው፡፡ የሚባል ነገር ካጣባቸው እሱ ምን ያድርግ? ቆይ ግን ትግሮቹ ስለ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ምን ብሎ ነው እንዲዘፍን የፈለጉት? ባንዳ ከሀዲነቱን አንሥቶ ነው የሚዘፍነው? ባሕረ ምድርን (የኋላዋ ኤርትራን) ዝም ብሎ በመመልከት በጣሊያን ማስወረሩን፣ማስያዙን፣ ማስወሰዱን አንሥቶ ነው የሚዘፍነው? ነው ወይስ ለቅኝ ገዥዎችና ሀገራችንን ሊወሩ እየገሰገሱ ለነበሩት የግብጽና የቱርክ ጦር አብሮ ለነጻነታቸው እየተዋጉ የነበሩትን ደርቡሾችን ወይም መሐዲስቶችን በመውጋቱ በሀገሪቱ ላይ ደርቡሽን ያህል ጠላት ስለተከለብንና ጎንደርን በደርቡሾች በተደጋጋሚ እንድትቃጠል፣ እንድትወድም፣ እንድትዘረፍ ስላደረገብን ይሄንን አንሥቶ ነው የሚዘፍንለት? ምን የሠራው መልካም ሥራ ኖሮ ነው የሚዘፈንለት? ደፋሮች ናቹህ በእውነት! በሀገርና በሕዝብ ላይ ክህደት መፈጸም ክብር መሰላቹህ? እንዲያው ትንሽም አታፍሩም? እናንተ እንኳን ልታነሡት ከማፈራቹህ የተነሣ አዲስ ዐፄ ዮሐንስ እስክትፈጥሩ ድረስ የምትሸማቀቁበትን ወራዳ ነውረኛ ባንዳ ጭራሽ እኛ እናንሣው? እዚህ ዜማ ላይ ቴዲ የአንጋፋውን ዘፋኝ የይርጋ ዱባለን ዜማ በማካተቱ ወጥ የሆነ ዜማ እንዳልሠራ ቆጥረውታል፡፡
ግጥሙ ላይም እኔ ጠንካራ ጎን አድርጌ የማስበውን ስላልገባቸው ደካማ ጎን አድርገው ረውታል፡፡ ዜማውን ልብ ብለው ቢያዳምጡት ግን የጋሽ ይርጋ ዜማ ተደርቦ ቀረበ እንጅ ተከልሶ የተሠራ ዜማ አይደለም፡፡ ቴዲ የተሟላ አዲስ ዘፈኑን አዚሞ ከጨረሰ በኋላ ነው የጋሽ ይርጋን ተወዳጅ ዜማ በጥሩ ቅንብር የደረበው፡፡ ይሄም የራሱ የሆነ ምክንያት አለው፡፡ ይሄ የቴዲ ዜማ ዜማው በጣም ከባድ ዜማ ነው አቀናባሪውን አማኑኤልን በጣም እንዳደከመ ይሰማኛል፡፡
ግሩም አድርጎ አቀናብሮታል፡፡ ይሄን መረዳት ያልቻሉ ስለዜማ የማያውቁ ሰዎች ናቸው ትችቱት ያቀረቡት፡፡ ስለቅንብር ካነሣን አራት ዜማዎች ለየት ብለው ታይተውኛል፡፡ ያምራልን አበጋዝ ክብረወርቅ፤ ማራኪየን፣ ማር እስከ ጧፍን፣ እማ ዘንድ ይደርን አቤል ጳውሎስ የወርቃማው የኢትዮጵያ ሙዚቃ (ዘፈን) ዘመንን እጅግ አድርጎ ባስታወሰ መልኩ ግሩም አድርገው ብረውታል፡፡
በዚህኛው ቅኝት ወደ ቃኘሁትና በጣም ቅር ወዳሰኘኝ ወደ ሦስተኛው ዘፈን ሳልፍ፦ ቴዲ አደይ በሚለው ዘፈኑ ከባድ ስሕተት ፈጽሟል፡፡ ስሕተቱ ግን የሱ ብቻ አይደለም፡፡ ይሄንን ስሕተት ፖለቲከኞች የኪነት ሰዎችና ተራው ዜጋ በሁለት ምክንያቶች ይሳሳቱታል፡፡ የኪነት ሰዎችና ተራው ዜጋ የሚሳሳተው አሁን ላይ አክሱም የሚገኙት ትግሮች ስለሆኑ ታሪክን ካለማወቅ የተነሣ አክሱም የትግሬ ስለሚመስላቸው ሲሆን፡፡ ፖለቲከኞች ደግሞ ከዚህ ምክንያት በተጨማሪ በሀገራችን ታሪክ የትግሬ ልኂቃን የሚያሳፍር የሚያስነውር እንጅ የሚያኮራ የሚያስከብር የሠሩት መልካም ሥራ ስለሌለ የትግሮችን ሥነልቡና ለመጠበቅ ሲሉ ትግሮችን “የአክሱም ሥርዎ መንግሥት ባለቤትና የሀገራችን ታሪክ መሠረት!” እያሉ ሥነልቡናቸውን በመጠበቅ ትዮጵያዊነት እንዲሰማቸው ለማድረግ ከጥንት ጀምሮ ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ለሀገር ሰላምና ደኅንነት ሲባል ለትግሬ የተሰጠው ማንነት የነሱ ስላልሆነ ትግሮቹ እንዲህቢባሉም ምንም ቢባል የራስ ያልሆነ ነገር አይዋሐድምና ሳይዋሐዳቸው እየቀረ በሚገርም ሁኔታ ዘወትር በዚህች ሀገር ላይ ክህደት እንደፈጸሙ ከጠላት ጋር እያበሩ እሷን ከመውጋት፣ እሷን ለማፍረስ ከማሴር ተቆጥበው የሚያውቁበት ዘመን ኖሮ አያውቅም፡፡ ያልደከሙባት ሀገር፣ ያልደከሙበት ሥልጣኔና ነጻነት ስለሆነ የባለአደራነት ስሜት የሚባል አይሰማቸውም፣ የጎሳቸው እንጅ የሀገር ፍቅር የሚባል ስሜት ደማቸው ውስጥ የለም፡፡ ለዚህች ሀገር ከመድከም ከሚገኝ የባለአደራነት ስሜት የመነጨ የሥነልቡና ውርስ የላቸውማ! የሌላቸውን ከየት ያመጡታል? ባሪያ ሆነው ሲረገጡ እንደኖሩ ባላቸው ትውፊታዊ መረጃቸው ስለሚያውቁ ሀገሪቱን የጠላት ሀገር አድርገዋት ለመበቀል ብለው ከጥንት ጀምሮ ወራሪ ጠላት በመጣ ቁጥር ከጠላት ጋር በመሰለፍ ሀገሩቱን እንደወጉ እንዳቆሰሉ፣ ሀገሪቱን ለማፍረስ እንዳሴሩ አሉ፡፡

ቴዲ ተሳሳተው የምላቹህ ስሕተት አደይ በሚለው ዘፈን ላይ ትግሮችን ከንግሥተ ሳባ ጋር በማያያዝ ንግሥተ ሳባን  ትግሬ አስመስሏታል፡፡ ግጥሙ በተጻፈበት ደብተር ላይ ደግሞ ይሄንን ዘፈን ከአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያንና ከአክሱም ሐውልት ጋር አያይዞ በማውጣት አክሱም ጽዮንንና የአክሱም ሥርዎ መንግሥትን የትግሬ አስመስሎታል፡፡ ስሕተቱ ይሄ ነው፡፡ ነገር ግን የአክሱም ሥርዎ መንግሥታትን የትግሬ ነው የሚል የታሪክ ሰውም (Historian) ወይም የታሪክ
መጽሐፍ ወይም በቁፋሮ የተገኘ መረጃ ብትፈልጉ አንዲት እንኳ አታገኙም፡፡

ትግሬን ከአክሱም ሥርዎ መንግሥት ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡ የአክሱም ሥርዎ መንግሥትና ከዚያ በፊት የነበረው ሥርዎ መንግሥት የአማራ መሆኑን ከዚህ በፊት በበርካታ መረጃዎች አስደግፌ አማራን ከአክሱምና አካባቢዋ ዮዲት ጉዲት እንዳጠፋችው፣ ከዚያ በኋላ ሀገሩ በአካባቢው አናሳ በነበሩት በባሮቹ ትግሮች ተወርሶ መቅረቱን ከነምክንያቱ በተለያዩ ጽሑፎቸ ላይ በተደጋጋሚ በሰፊው የጻፍኩበት ጉዳይ መሆኑን ታስታውሳላቹህ፡፡ ሁለቱን
ለማስታወስ ያህል “የዘር ማጥፋት ወንጀል በአማራ ሕዝብ ላይ በታሪክ ሒደት ከትናንት እስከ ዛሬ!” እና “የአማራ ሕዝብ ማንነትና አስቂኙ የትግሬዎቹ የተጋሩ ነን ተረት!” በሚሉት ጽሑፎቸ ላይ በበርካታ ታሪካዊ መረጃዎች አረጋግጨላቹሀለሁና ጥርጣሬ ያለበት ሰው ቢኖር ጽሑፎቹን ጎግል አድርጎ በማንበብ ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡

ሌላው ቅር ያሰኘኝ ነገር ምንድን ነው ከሲዲውና ሽፋኑ ላይ የጎንደር ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን ላይ ያሉ የመላእክትን ሥዕል ማስቀመጡ ነው፡፡ “ምነው ባለፈው የዘፈን ዓይነቶችን እየዘረዘርክ እነዚህ ዓይነት ዘፈኖች ኃጢአት አይደሉም! እንዲያውም ከእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋና ክብር ያሰጣሉ! ብለህ አልነበረ? እንዲህ ከሆነ ታዲያ የመላእክት ሥዕል ቢደረግበት ምን ችግር አለው?” ትሉኝ ይሆናል፡፡ አዎ ብያለሁ! ነገር ግን የጠቀስኳቸው ዓይነት ዘፈኖች ኃጢአት ባይሆኑም የጊዜና የቦታ ገደብ እንዳለባቸው አያይዠ መግለጼም መረሳት የለበትም፡፡ በሥርዓተ ቤተክርስቲያን መሠረት አንድ ነገር ኃጢአት አይደለምና ተብሎ የትም ቦታ መቸም ሰዓት እንደማይደረግ በአንክሮ ገልጫለሁ፡፡ ለምሳሌ “ጋብቻ ቅዱስ ነው መኝታውም ንጹሕ ነው!” ዕብ. 13 4 ይላል ቃሉ፡፡ የባልና ሚስት ጾታዊ ግንኙነት የተቀደሰ ነው ተብሎ ግን ለምሳሌ ቤተክርስቲያን ውስጥ ግንኙነት እንዲያደርጉ አይፈቀድም ብቻ ሳይሆን ጨርሶ የሚታሰብም አይደለም፡፡ ምክንያቱም ወሲብ የሥጋ ሥራ ነውና፡፡ ዘፈንም እንዲሁ ነው፡፡ ኃጢአት አይደሉም ያልኳቸው የዘፈን ዓይነቶች ኃጢአት ባይሆኑም ለምሳሌ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሊደመጡ አይችሉም ብቻ ሳይሆን የሚታሰብም አይደለም፡፡ ምክንያቱም እንደ ወሲብ ሁሉ ዘፈንም ኃጢአት ባይሆኑም የሥጋ ሥራ ናቸውና፡፡ በመሆኑም የመላእክት ሥዕል በዚህ የዘፈን ሲዲና ሽፋኑ ላይ መደረጉ ትክክል አይደለም፡፡ በዚህ ላይ ከዘፈኖቹ ውስጥ አንዱ ኃጢአት ተብለው ከሚመደቡት ዘፈኖች ውስጥ የሚመደብ እንደሆነ ገልጫለሁ፡፡

ስለዚህ ጉዳይ በዝርዝር የሙዚቃ (የዘፈን) ባለሙያው እነ ሠርፀ ፍሬስብሐት በስድስት ዓመታት በፊት በሸገር ሬዲዮ (ነጋሪተ ወግ) ላይ ያዘጋጁት በነበረው ዝግጅት “ዘፈን ኃጢአት ነው ወይስ አይደለም?” በሚል ርእሰ ጉዳይ ተከታታይ ዝግጅት ባቀረቡ ጊዜ ለሠርፀ በሰጠሁት ቃለ መጠይቅ ላይ የትኞቹ ዘፈኖች ኃጢአት እንደሚሆኑና እንደማይሆኑ፣ ኃጢአት ያልሆኑቱ ዘፈኖች ለነማን በምን በምን ምክንያቶች እንደሚፈቀዱና እንደማይፈቀዱ በዝርዝር ገልጨለት ነበር፡፡ እረጅም ስለነበረ ቀንጭቦ ነበር ያቀረበው፡፡ ከዚያ በኋላ እኅቱ ጋዜጠኛ ሕይዎት ፍሬስብሐት ሙሉውን ልታቀርበው እንደምትፈልግ ነግራኝ ነበረ፡፡ አቅርባው ከሆነ ሰምታቹህት ይሆናል፡፡ እናም ነገሩ እንዲህ በሆነበት ሁኔታ የመላእክትን ሥዕል መጠቀም በፍጹም ትክክል አይደለም፡፡ ለገበያውም ቢሆን ጥሩ አይመስለኝም፡፡ እስላም ክርስቲያን ሳይባል ሁሉም እጅ ላይ ሊገባ ሲችል ነውና ገበያ ላይ የተሻለ ተጠቃሚመሆን የሚቻለው፡፡ ከዚህ ውጪ ግን ሽፋኑ ላይ ያሉ ፎቶዎች (ምስለ አካሎች) በምክንያትና በዘፈኖቹ ከተላለፉ መልእክቶች ጋር የተሰናሰሉ በመሆናቸው መልካም ነው፡፡ አንደኛው ለምሳሌ ቴዲሻ ዐፄ ቴዎድሮስ ከአናብስቶቻቸው ጋር እንደተቀመጡ ሆነው የሚያሳይ ሥዕል ግድግዳው ላይ በተሰቀለበት ቤቱ ተቀምጦ፤ በነገራችን ላይ በርጋታ ሰዎች ዐፄ ቴዎድሮስ ከተቆጡ አናብስቶቻቸው ጋር ሆነው የሚያሳየው ሥዕል የእውነት መሆኑን አያውቁም፡፡ የድርሰት ሥዕል ነው የሚመስላቸው፡፡

በሥዕሉ ላይ የሚታየው ትእይንት ግን እውነተኛ ነው፡፡ አውሮፓውያኑ የዐፄ ቴዎድሮስ እስረኞች የነበሩት ራሳም ሆርሙዝና ብላንክ መጻሕፍቶቻቸው ላይ ጽፈውታል፡፡ እና ቴዲ ይህ የዐፄ ቴዎድሮስ ሥዕል በግድግዳው ላይ በተሰቀለበት ቤቱ ውስጥ ተቀምጦ የንቡረ እድ ኤርሚያስ ከበደን “ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት!” የሚለውን መጽሐፍ ሲያነብ ይታያል፡፡ ንቡረ እድ ኤርሚያስ ኢትዮጵያዊነትን ጥሩ አድርገው የሚሰብኩ ሰው ናቸው፡፡ ምንም እንኳ የሀገር ፍቅራቸው ትንሽ በዛ ያለ ቢሆንም ቅሉ፡፡ አንዴ “እውን ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ ነውን?” በሚለው ጽሑፌ ላይ ክርስቶስን ኢትዮጵያዊ ነው እያሉ የሚናገሩ ሦስት አባቶችን ገስጨ ስለነበረ ንቡረ እድ ኤርሚያስ “አምሳሉ ስሜን አይጥቀስ እንጅ ከሦስቱ አንደኛው እኔን ማለቱ ነው!” ብለው በቁጣ ተነሳሥተው የራሳቸው ተከታዮች ሳይቀር ያልወደዱላቸውን “መልስ ለሠዓሊ አምሳሉ!” በሚል ርእስ ጽፈው እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ ይብቃን መሰለኝ፡፡ በሉ እንግዲህ የቴዲን ዐፄ ቴዎድሮስ ጥኡመ ዜማ ጋብዣቹህ ልሰናበት አሃ አሃ አሃ! እንዴት ነው ነቃ ነቃ ነው እንጅ…

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail