Posted on May 9, 2017
“ቅባትና ደረቅ” በአማኑኤል የአዕምሮ ህክምና ሆስፒታል ታካሚዎች እንደ ደረጃ መዳቢ የተሰጠ ስም ነው። ታሪኩ ዘግናኝ፣ ኅሊናን የሚፈትን፣ ወዴት እያመራን እንደሆነ ግራ የሚያጋባ፣ መፈጠርን የሚያስጠላ፣ ሲሰሙት ግራ የሆነ፣ ቃላት ሊገልጹት የማይችል የክሽፈታችን ሁሉ ከሽፈት ነው። አማኑኤል ሆስፒታል ተኝቶ ለመታከም አርባ ሺህ ብር እንደሚከፈል ከመስማት በላይ ዘግናኝ ጉዳይ የለም። ጎልጉል ባሰባሰበው መረጃ ሌሎችም ጉዳዮች አሉ።
ወ/ሮ ፋጡማ ሐሰን (ስማቸው ለዘገባው የተቀየረ) ከደሴ ከተማ የመጡ አስታማሚ ናቸው፡፡ በሃያዎቹ አጋማሽ ዕድሜ ላይ የምትገኝ የአዕምሮ ህመምተኛ ልጅ አለቻቸው፡፡ ልጃቸው በ2006 ዓ.ም. የሳውዲ አረቢያ መንግስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን “ህገ-ወጥ” በሚል በግፍ ሲያባርር የሰራችበትን ደመወዝ እንኳ ሳታገኝ ባዶ እጇን የተመለሰች ኢትዮጵያዊት ነች፡፡ በወቅቱ ስትመለስ ከፍተኛ የሆነ የመንፈስ ጭንቀትና መረበሽ የነበረባት ቢሆንም፣ የአዕምሮ ህመሟ አሁን ባለበት ደረጃ አልነበረም፡፡ “በሂጃብ ፊቷን የሸፈነች ሙስሊም ሴት ባየች ቁጥር ‹ብሬን! ብሬን! . . . › እያለች ትጮኻለች”
በአማኑኤል ሆስፒታል ሴት የአዕምሮ ህመምተኞች መደፈራቸውን፣ ሲያረግዙ ጽንስ የሚቋረጥበት ክሊኒክ በውስጥ በተደረገ ስምምነት ይሰጥ እንደነበር ይፋ በተሰማ ጊዜ ጫጫታ ተሰምቶ ነበር። ጉዳዩን በወቅቱ ይፋ ያደረጉት አንድ የሆስፒታሉ ነርስ ነበሩ። ዛሬ ያ ግፍ ተመርምሮ መልስ ሳያገኝ ተጨማሪ ጉድ እየሰማን ነው። የሟቹ መለስ ዜናዊ ባለቤት የበላይ ጠባቂ ሆና ስትመራው በነበረው ሆስፒታል ያለውን የቁሳቁስና የጽዳት፣ እንዲሁም የአልባሳትና ተመሳሳይ ችግሮች ሳያነሱ፣ ከሰውነት ደረጃ በወረደ የሚፈጸመውን ጉድ “ህሊና” ያላቸው ወገኖች እንዲያውቁት እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
ለአማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግንባታ ከኮንትራት ውጭ 82 ሚሊየን ተከፈለ
የሚያሳዝነው አማኑኤል ሆስፒታልን ያዩ “ባለሃብቶች፣ ታዋቂ የሚባሉ የጊዜው ባሮች፣ ሃብት ካፈሩ በኋላ መሬት ለቆለሉት ሃብት ሲሉ የሚልከሰከሱ “ወገኖች” እንዲሁም ያደፈ ጓዳቸውን ተሸክመው በሚዲያ የሚዘመርላቸው “ለጋሶች” ለመሆኑ የት ናቸው?” ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ ምን ይሆን? ለሁሉም ሙሉ መረጃውን እነሆ!
የተዘነጋው አማኑኤል የአዕምሮ ህሙማን ሆስፒታል!
-
አንድ መቶ ሚሊዮን ህዝብ አላት ተብሎ በሚገመተው ኢትዮጵያ አንድ ብቸኛ የአዕምሮ ህሙማን ሆስፒታል አላት!
-
አማኑኤል ሆስፒታል 70 ዓመት የአገልግሎት ጊዜ አለው፡፡ ሦስት መቶ አስር አልጋዎች ብቻ አሉ!
-
አማኑኤል ሆስፒታል ውስጥ አልጋ ለማግኘት አስታማሚዎች እስከ 40,000 ሺህ ብር ድረስ ለህክምና ቡድኑ ሙስና ይከፍላሉ!