ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያምን ከጀርባ ሆነው በአማካሪ ሰበብ ከሚዘውሩት የሕወሓት ባለልጣናት መካከል አንዱ የሆኑት አርከበ እቁባይ ከጀርመን ድምጽ ራድዮ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ መንግስታቸው ለኢኮኖሚ ዕድገት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ገልጸው የዲሞክራሲያዊ መብት ጥያቄን ወዳልታወቀ ዘመን አሸጋግረውታል::

ከአፍሪቃ ወደ አዉሮጳ የሚሰደደዉን ሕዝብ በየሐገሩ ለማገድ ይረዳል በተባለዉ ዕቅድ ላይ የተነጋገረ ዓለም አቀፍ ሥብሰባ ባለፈዉ ሳምንት በርሊን ጀርመን ዉስጥ ሲደረግ ተካፋይ የነበሩት አርከበ ዕቁባይ ከጀርመን ድምጽ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ለግንዛቤ ይረዳዎ ዘንድ ያድምጡት::