May 20, 2017
Posted by: Zehabesha

 
ፐርዝ ወይም ኦክላንድ ቢበሩ፤ ሜልቦርን ወይም አስመራ ቢሰፍሩ፤
የኤፍሬም ማዴቦ ጉዳይ ነው። የዐማራውን ትግል ግን ለቀቅ ያድርጉት!!!
አንዱዓለም ተፈራ
አርብ፣ ግንቦት ፲፩ ቀን ፳፻፱ ዓመተ ምህረት“ኦዚ ደርሶ መልስ” በሚል ርዕስ፤ ኤፍሬም ማዴቦ የከተቡትን አነበብኩ። ኤፍሬም ማዴቦ፤ ይህን ጽሑፋቸውን፤ “(እዚህ ጽሁፍ ዉስጥ ያለዉ ሀሳብበሙሉ የኔ የግሌ፣ የኔና የኔ ብቻ ነዉ)” በማለት ይጀምራሉ። ለመሆኑ፤ ያሰፈሩት ጉዳይ፤ በምን ሂሳብ ነው የኤፍሬም ማዴቦ የግላቸውና የራሳቸው ብቻ የሚሆነው? ምን አስፈራቸው? የተላኩት የኤፍሬም ማዴቦን ቤት ለመሥራት ሳይሆን፤ የድርጅታቸውን የግንቦት ሰባትን ተልዕኮ ተሸክመው ነው! ለምን ፈሩ? ከዚያ የተቀበሏቸውም ሆነ ንግግር ያደረጉላቸው፤ የድርጅታቸው አባላትና ደጋፊዎቻቸው ነው። ታዲያ “የግሌ ነው!” ን ምን አመጣው!

 

ልቀጥልና፤ በዚሁ ወቅት፤ የድርጅታቸው መሪ፤ በዘር ከተደራጀ፤ ለዚያውም ኢትዮጵያዊነቱን ከጥያቄ ውስጥ ካስገባ አንድ ድርጅት ጋር፤ የትግል አንድነት በማድረግ ፊርማ አስቀምጠዋል። ያ እንዳይመሳቅልባቸው ፈርተው ይሆን! አይ የፖለቲካ ነገር! ይሄን ለሳቸው ልተወው። እንዳልተወው ግን፤ ይህ የመሪያቸው ኢትዮጵያዊነታቸውን ከጥያቄ ውስጥ ካስገቡ ድርጅቶች ጋር መፈራረምና መግለጫ ማውጣቱ፤ የመጀመሪያቸው ወይንም የመጨረሻቸው እንዳልሆነ ሀገር ያውቀዋል! “አለ ነገር!” ያስብላል። ለመሆኑ ይሄን የመሰለ፤ ለሌሎች ብሔሮች መደራጀት ተገቢ ሲሆን፤ ለዐማራው ግን፤ ሀገር አፍራሽ የሆነበት ምን ምክንያት አለ? ግንቦት ሰባትን ይሄን ያህል ያስፈራው ምንድን ነው? ይሄን ዝቅ ብዬ አቀርበዋለሁ።

 

ኤፍሬም ማዴቦ ዐማራው ያለበትን የኑሮ ሁኔታ፤ እንደባለቤቱ እንዳማራው ሊያውቁና፤ የዐማራውን የልብ ትርታ ሊገነዘቡ እንደማይችሉ፤ ከወዲሁ አውቃለሁ። ነገር ግን፤ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ፤ በተወሰነ ደረጃ፤ ዐማራው አሁን በተፈጠረው የፖለቲካ ሀቅ፤ ስነልቡናው ወዴት እንዳለ በትንሹም ቢሆን ይረዱታል፤ የሚል ግምት ነበረኝ። በርግጥ የባለቁስሉን ያህል፤ ሕመሙን ሌላ ግለሰብ ዘርዝሮ ሊያውቀው እንደማይችል፤ አንባቢ ይረዱልኛል። እስኪ ምን አልባት አእምሯቸውን መክፈት ችለው መከታተል ከሆነላቸው፤ ስለሌላ ሳይሆን ስለራሴ ላውጋቸው። እግረ መንገዳችሁን እናንተም እስኪ እባካችሁ እህ! በሉና፤ አብራችሁን አዝግሙ።

 

ከሃምሳ ዓመት በላይ በኢትዮጵያዊነት ታግያለሁ። የትግሬዎቹ ገዥ ቡድን ጦሩን ከቶ ወልቃይት ሲገባ፤ በቦታው፤ በወቅቱ በነበርኩበት ድርጅት በኩል ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገን፤ በእውነት የወቅቱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር “ጀግንነት!!!” መሬት ለመሬት በሚያስኬድ ሁኔታ እስኪንበረከክ ድረስ፤ አንፏቀን ሰደነዋል። ያን በሌላ ጊዜ። የዚያን ጊዜ የትግሬዎቹ ገዥ ቡድን አመራርና የዛሬ ቢሊኒየር ቱጃሮች፤ እንጭጭ ለጋ የትግራይ ወጣቶችን ማገዶ አድርገው፤ መሰላል አድርገው ተወጣጥተውባቸው፤ ለዛሬው ጉድ ተረፈዋል። በዚያ በሸረላ ጦርነት፤ የቀኝ እጅ ትከሻዬ ላይ ተመትቼ፤ አሁንም ድረስ ሰባራ አጥንት ይዤ እጓዛለሁ። ይህ የሆነው ከሰላሳ ሰባት ዓመት በፊት ነው። ከዚያ በፊት አደርግ እንደነበረው ሁሉ፤ ከዚያ በኋላም በኢትዮጵያዊነት ትግሉን ቀጠልኩ።
ኤፍሬም ማዴቦ በዘር ከተደራጁ ክፍሎች ጋር ለመተባበር ወዲያ ወዲህ ሲሯሯጡ፤ እኔ ትክክል አይደለም ብዬ፤ በ “ኢትዮጵያ ወይም ሞት!” ራዕይ ቀጠልኩ። የፖለቲካ ሂደት አንዱ ገጹ፤ ዛሬ ወሳኝ የነበረው ኩነት ተቀይሮ፤ ነገ ክብደቱ ቀናሽ መሆኑ ነው። ነገ ሌላ ሀቅ ተተክቶ፤ ወሳኝነቱን ከዛሬው ወሳኝ ጉዳይ ይቀማል። በኢትዮጵያ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት አለመኖርና፤ የትግሬዎች መንግሥት መንገሥ፤ ያን ንግሥና ይሄው የትግሬዎች ገዥ ቡድን ይዞ፤ የሀገሪቱን የፖለቲካ ሀቅ መለወጡና ለሃያ ስድስት ዓመታት መሾፈሩ፤ ትናንት የነበረውን የፖለቲካ ስሌት ቀየረው። አልቀየር ብሎ እምቢ ያለ ቢኖር፤ ራስ ደጀን ነው። ራስ ደጀን፤ “አሁንም ጎንደር እንጂ፤ ትግራይ አይደለሁም ያለሁት!” ብሎ ካለበት ንቅንቅ አላለም። በፖለቲካ ትግል፤ የዛሬው ወዳጅ የነገ ጠላት፤ የዛሬው ጠላት ደግሞ የነገ ወዳጅ ሊሆን መቻሉን መቀበል አለብን። ያ የሚሆነው፤ ሁኔታዎች ስለሚለዋወጡ ነው። በኢትዮጵያ ያለውም ሁኔታ ተለዋውጧል።

 

ከላይ እንዳሰፈርኩት፤ በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ መንግሥት የለም። ያለው የትግሬዎች መንግሥት ነው። የዐማራው ትግል፤ ከትግሬዎች መንግሥት ጋር እንጂ፤ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር አይደለም። ይህ የትግሬዎች መንግሥት ደግሞ፤ ከመነሻው ጀምሮ የፖለቲካ ፍልስናው መሠረት፤ በዐማራው መቃብር ላይ፤ የትግራይን ሩፑብሊክ መመሠረት ነው። በፍልስፍና ደረጃ ብቻ ሳይሆን፤ ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት ይሄንኑ ነበር ሲተገብር የቆየው። “ለትግሬው መኖር የዐማራው መጥፋት!” “ለትግሬው መበልጸግ የዐማራው መምከን! ግድ ነው!” ብሎ ያመነ የትግሬዎች መንግሥት መከሰት ያስከተለው የፖለቲካ ሀቅ ውጤት! እኔና መሰሎቼ ኢትዮጵያ ወይም ሞት ስንል፤ የትግሬዎቹ መንግሥት፤ ዐማራውን ከምድረ ኢትዮጵያ ለማጥፋት፤ ያለ የሌለውን ጉልበት፣ ንብረትና፣ እውቀት አረባረበበት። በዚህ ወቅት ዐማራው፤ ከሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ብቻ ሳይሆን፤ ከራሱ ከዐማራው አካባቢም ተፈናቀለ። ተባረረ። ታሰረ። ተገደለ። የመጨረሻው የሞትና ሽረት ደረጃ ሲደርስ፤ እኔም፤ “ኧረ! ይሄማ እንዴት ይሆናል? ዐማራው ከምደረ ገጽ ሲጠፋማ ዝም ብዬ አላይም!” አልኩ።

 

እናም ዐማራው ከምድረ ገጽ እንዳይጠፋ፤ ተፈጥሯዊ ግዴታ አለብኝ። በርግጥ ኤፍሬም ማዴቦ፤ የኔን ያህል የዐማራው ጉዳይ ቆርቁሯቸው ይነሳሉ የሚል ቅዠት የለኝም። ለሳቸው የዐማራው የህልውና ጉዳይ፤ ከፖለቲካ ስሌታቸው ውስጥ፤ አንዱ ክፍል ነው። በምን መንገድ ብይዘው፤ ለትግሌ ስኬት ይጠቅመኛል? ከሚል ነው የሚነሱት። ለኔ ደግሞ፤ “ከሁሉ በፊት ዐማራው መዳን አለበት!” “ከምንም ነገር በፊት የዐማራው ሕልውና!” የሚለው ነው። እንግዲህ በሳቸውና በኔ መካከል ያለው ልዩነት ይሄ ነው። እኔ፤ ለዐማራው የሚደረገውን ትግል፤ ለኢትዮጵያዊነት የሚደረገው ትግል አንድ ክፍል አድርጌ ዓየዋለሁ። እሳቸው ይሄ አይዋጥላቸውም።

 

ዐማራው፤ “ሀገሬ ኢትዮጵያ ናት!” እንዳለ ነው። አሁንም ዐማራው በኢትዮጵያ በሙሉ በኢትዮጵያዊነቱ ሰፍሮ፤ በዚህ ተግባሩ ደግሞ፤ ከማንም በላይ እየተሰቃዬ ነው። አሁንም ጎንደር ተሰለፈ ባህርዳር፤ ወልድያ ተሰለፈ ደብረ ብርሃን፤ “የኦሮሞው ደም የኔ ደም ነው!” እንዳለ ነው። ዐማራው፤ “ሰንደቅ ዓላማዬ አረንጓዴ ብጫ ቀይ ቀለሙ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ነው!” እንዳለ ነው። ዐማራው፤ “ዳር ደንበሬ የኢትዮጵያ ዳር ደንበር ነው!” እንዳለ ነው። ዐማራው፤ “በዐማራነቴ መበደል የለብኝም!” ነው ያለው። ይሄን ለማድረግ፤ የማንንም ፈቃድ ሆነ ምርቃን አይጠብቅም። ምነው ኤፍሬም ማዴቦ፤ ይህ እንቅልፍ ነሳዎት! የርሶን ቡራኬ እስክናገኝ መጠበቅ ነበረብን!
እሳቸው እንዲህ አሉን፤
“ . . . አማራዉ በዘር ተደራጅቶ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን በተለየ መንገድ የኢትዮጵያ ጠባቂ ይሆናልየሚለዉ አባባል እራስን አግዝፎ ወይም ሌሎችን አሳንሶ ከማየት የሚመጣ የአዕምሮ በሽታ ነዉ።”
በማለት፤ ከየት እንዳመጡት ያልገባኝን አባባል አስፍረዋል። አንድን የተነገረ ሀቅ ገጥሞ መሟገት አንድ ነገር ነው። ያልተባለን መሞገት ግን፤ ለኔ ቢያንስ ጤነኝነት አይደለም። ዐማራው በተለይ ተደራጅቼ፤ የኢትዮጵያ ጠባቂ ልሁን አላለም። ብሏል ካሉ፤ የት ቦታ? እና ማን? የሚለውን መግለጥ ይጠበቅባቸዋል። በደፈናው የፈለጉትን እንዳሻቸውና እንደመጣላቸው ሲናገሩ የሰማኋቸው እብዶችን ብቻ ነው። ዐማራው ራሴን ከዘር ማጽዳት ላድን አለ እንጂ፤ ኢትዮጵያን ለብቻዬ ላድን አላለም። ይልቁንም፤ “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለታችሁን ትታችሁ፤ ዐማራውን ለምን አታድኑም!” የሚል መልዕክት ነው፤ በአሁኑ በትግሬዎች ገዥ ቡድን ግፍና በደል የተጠበሰው ወጣት፤ እንደኔ ያለውን ኢትዮጵያዊ ነኝ ያለውን ዐማራ የጠየቀው። የዐማራው ትግል፤ “በማንነት ላይ የሚደረግ በደል፤ መቆም አለበት!” የሚል ነው። ይሄ መቼም በኔ ግምት፤ ኤፍሬም ማዴቦን አብሮ ያዘለና፤ እሳቸውም፤ “እኔም አለሁበት!” ሊሉበት የሚገባ ትክክለኛ ትግል ነው። ነገር ግን፤ የፖለቲካ ጉዳይ ሆነና፤ ያልተባለውን ተባለ፤ ያለውን የለም ብሎ መቅዘፉ፤ የባለ ድብቅ አጀንዳ ነገር ስለሆነ፤ ጠበል አይረዳም።
“ራስን አግዝፎ ወይንም ሌሎችን አሳንሶ ከማየት የሚመጣ የአዕምሮ በሺታ ነው።” ድርብርብ መልዕክቶችን የያዘ ጉዳይ ነው። የመጀመሪያውና ግልጹ፤ እንደ የትግሬዎች ገዥ ቡድን፤ ዐማራው ትምክህተኛ ነው የሚል ነው። ዐማራው በትግሬዎቹ ገዥ ቡድን የተከሰሰበትን ወንጀል አሁንም በሌላ ሸማ ጠቅልሎ መቅረብ ነው። ግድየለም፤ አሁንም እኮ ዐማራው ያለው፤ ሌሎች ለኔ ሊታገሉልኝ ስለማይችሉኅ ተደራጅቼ መታግገሌ ግዴታዬ ነው! እናም አደርገዋለሁ ነው። ኤፍሬም ማዴቦ በግልጽ አይሰለፉ እንጂ፤ ዐማራውን ውንጀላቸው እኮ ከትግሬዎቹ ገዥ ቡድን አልለዋቸውም! አይገርማችሁም! በዚህ አባባላቸው፤ ትምክህተኛ፣ ሌሎችን ናቂ፣ የአዕምሮ በሺተኛ፣ . . .  ምን ያላሉን ነገር አለ! እውነት በሺተኛው ማን ይሆን? የወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል፤ ሆነና !!!
በርግጥ አመቺ ሆኖ ካገኙት፤ ለኤፍሬም ማዴቦና ለድርጅታቸው፤ ከሌላ በዘሩ ተደራጅቶ ከተሰለፈ ድርጅት ጋር መተባበሩ፤ ዓይናቸውን አያሹበትም። ምክንያቱም፤ ቁም ነገር ብለው የሚወስዱት፤ የጉዳዩ አንድነት ሳይሆን፤ ለሳቸው የፖለቲካ ሂደት ይረዳል? ወይንስ አይረዳም? የሚለው የፖለቲካ ቅመራ ነውና! ዐማራውን በተመለከተ፤ ኤፍሬም ማዴቦ ችግር አላቸው። ያሰፈሩትን ልጥቀስ፤
“ . . . አጼ ቴዎድሮስ ዘመነ መሳፍንትን ዘግተዉ ዘመነ አንድነትን ጀመሩ እንጂ እንደዛሬዎቹ የሳቸዉ ልጆች ነንባዮች ቋንቋና ዘርን አልሰበኩም። አንድ ኢትዮጵያዊ የ“ቴዎድሮስ ልጅ” ነኝ ለማለት ቋራ፥ ጎንደር ወይም አማራክልል መወለድ የለበትም። ኢትዮጵያዊ የትም ይወለድ የት አንድነትን እስከሰበከ ድረስ የቴዎድሮስ ልጅ ነዉ።የቴዎድሮስ ትልቅነትና አዋቂነት ይዞት የተነሳዉ ራዕይ ነዉ እንጂ የተወለደበት ቦታ አይደለም።” አሉ።

በሳቸው ቅመራ ከሆነ፤ ድርጅታቸው ከሌሎች የዘር ድርጅቶች ጋር ሲነጋገርና ሲያብር፤ እኒያ የድርጅት አባሎች፤ የቴዎድሮስ ልጆች አይደሉም። ባይሆኑም ግን፤ ስለሚጠቅሙ፤ ከነሱ ጋር መዋሀዱ ተገቢ ነው። ይሄ ኤፍሬምኛ ይባላል። ዐማራውን በተመለከተ ግን፤ እሳቸው፤ ማለት ኤፍሬም ማዴቦ፤ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው በተለሙለት መንገድ ካልተጓዘ፤ ትክክል አይደለም! በሺታ ነው! አይ የዴሞክራሲ ነገር! ብቻ ላመሰግናቸው የሚገባ አባባል ጣል አድርገዋል። አዎ! የቴዎድሮስ ልጅነት፤ ለዐማራው ብቻ አለመሆኑን በሚገባ አቅርበውታል። አሁንም አፄ ቴዎድሮስ የኛ ብቻ ናቸው ያለ ዐማራ አላውቅም። ይልቁንስ ከዘመናቸው በፊት የተወለዱ፤ የመላው ጭቁን ሕዝብ ንጉሥ ናቸው፤ ባዮቹ ብዙ ነን።
ኤፍሬም ማዴቦ አልፈው ተርፈው፤
“እኛ ኢትዮጵያዊያን እንደዚህ አይነት ጠንካራ መርህ እንዲኖረን የግድ አማራ ሆነን፥ ትግሬ ሆነን ወይም ኦሮሞሆነን ወዘተ መፈጠር የለብንም። ኢትዮጵያ የምትባል አገር ዉስጥ ሰዉ ሆነን መፈጠር ብቻ ነዉ ያለብን። ዛሬእንዲህ አይነቶቹ ትላልቅ የኢትዮጵያዊነት እሴቶች ተረስተዉ በአንዳንድ የፖለቲካ መድረኮች ላይ በአገርመዉደድ ስም ብሄረተኝነት እየተሰበከ ነዉ። ይህ አደገኛ ስብከት አገራችን የምትገኝበትን ሁኔታ በሚገባካለመረዳት፥ ከግድ የለሽነት፥ ለራስ ጥቅም ከመቆምና አገር ወዳድነትንና ብሄረተኛነትን ለያይቶ ካለማየትየሚመጣ በግዜ ካልታከሙት የማይድን በሽታ ነዉ።”
በማለት፤ በሺታ አስታቅፈውን አረፉ።  ከመነኮሱ ላይቀር እንደ ኤፍሬም ማዴቦ ነው! ለምንድን ነው ለሌሎች የሠጡትን የመቀራረብና የአንድነት መፍትሔ ፍለጋ ለዐማራው መሥጠት ያልፈለጉት። ዐማራው ያ መብት የለውም ካለው ከትግሬዎቹ ገዥ ቡድን የቀዱት ይሆን! ምን አልባት ብዬ ነው!
በዚህ በኤፍሬም ማዴቦ ጽሑፍ፤ ምን ያህል ራሳቸውን እና ድርጅታቸውን በሚገለባበጥ የፖለቲካ ቅመራ እንደነዱት ማየቱ ቀላል ነው። ነገር ግን፤ እሳቸው ማየት የተሳናቸውን ወይንም ሆን ብለው ያደበዘዙትን ጉዳይ፤ ሌሎች ማየት አይችሉም ብለው መናቃቸው ያስገርማል።
ጥሩ ሰባኪ ናቸው። ችግሩ ግን የሚሰብኩትን ማድረግ አይፈልጉም። “አገር ወዳዶች ሰዎችን ለያይተዉ የሚያዩበት የዘር መነጽር የላቸዉም፥ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚመለከቱት እንደወገናቸዉ ነዉ።” ብለው ሰብከው፤ ዐማራው ይሄን ያህል ተገልጾ በማያልቅ ጉዳት ላይ ተቀምጦ፤ ምንም አንዲት ጣታቸውን ሳይነሱ፤ አሁን ራሴን ላደራጅ ሲል፤ ጉራ ከረዩ አሉ! ምነው ዐማራው ወገኔ ነው ካሉ፤ የዘር ማጽዳት ሲፈጸምበት የት ነበሩ?
አንዳንድ ጊዜ፤ በሌላ በኩል ያለውን ወገኔን ጥሩ ጎን የግድ ፈልጌ ማየት እንዳለብኝ አውቃለሁ። እናም፡
“ዛሬ እያንዳንዳችን የፈለገዉን ያክል ጠንካራ የብሄር ድርጅት ቢኖረንም ህወሓትን በተናጠል ገጥመን ማሸነፍአንችልም፥ ምክንያቱም በብሄር የተደራጁ ሀይሎች ሁሉ እንደ ጠላት አድርገዉ የሚመለከቱት ህወሓትን ብቻሳይሆን ከራሳቸዉ ዉጭ ያለውን ብሄር ሁሉ ነዉ። ስለዚህ እርስ በርስ እየተዋጋን ህወሓትን እናሸንፋለን ማለትዘበት ነዉ።”
ችግሩ ደግሞ፤ በትክክል አንድን ነገር ብቻ ግልጽ አድርጎ ማቅረብን ፖለቲከኞች አይፈልጉም። ተጨማሪ አጀንዳቸውን ሸጎጥ ማድረጉን ተክነውበታልና! “እንደ ጠላት አድርገዉ የሚመለከቱት . . .  ከራሳቸዉ ዉጭ ያለውን ብሄር ሁሉ ነዉ።” በማለት፤ በራሳቸው ጭንቅላት ብቻ የሚሽከረከረውን ጣሉበት። ይሄን የት እንዳነበቡት አላውቅም። ሁሉም የብሔር ድርጅቶች እንዲህ ከሆኑ፤ ታዲያ ድርጅታቸው አብሮ ለመሥራት የሚያሳድደው እነማንን ነው?
አክለውም “እርስ በርስ እየተዋጋን ህወሓትን እናሸናለን ማለት ዘበት ነው።” ብለዋል። ለርስ በርስ ውጊያ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ነገሩን! ይገርማል። ርስ በርስ መዋጋትንና ማቸነፍን እዚህ ላይ ምን አመጣው? ይሄን ሁሉ ልተውና፤ የትግሬዎቹን ገዥ ቡድን በተናጠል ገጥመን ማቸነፍ አንችልም፤ ያሉትን በጎ አባባል ልውሰድላቸው። ትክክል ነው! ታዲያ አንድ ጤነኛ ሰው፤ ከዚህ ተነስቶ፤ ከተናጠል ወደ አንድነት ትግሉ ለመሄድ ምን ላድርግ? ብሎ ነው የሚያስበው። ለምን ይሄ ኤፍሬም ማዴቦን ተሳናቸው! ለሁሉም ድርጅቶች ጠላትና ወዳጅ ቀማሪ እሳቸው ሆኑ!!! ምን የሚሳናቸው አለ!
ኤፍሬም ማዴቦ፤
“ከቅርብ ግዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረኮች ላይ መሰማት የጀመረ አንድ እጅግ በጣም አደገኛ የሆነስብከት አለ . . . . እሱም  የ “አማራዉ አማራ ሆኖ መደራጀት የአማራንም የኢትዮጵያንም ነፃነት ያፋጥናል”የሚለዉ ምንም አይነት መሠረት የሌለዉ ስብከት ነዉ።”
አሉን።
እንዴ! ዐማራው የኢትዮጵያ አንድ አካል መሆኑን ምነው የሚነግራቸው ጠፋ! ምነው የዐማራው መዳን፤ የኢትዮጵያ አንድ አካል መዳን ነው፤ ብለው ማሰብ አቃታቸው። የኦሮሞው መዳን የኢትዮጵያ መዳን ነው። የኢትዮጵያዊ ሱማሌው መዳን የኢትዮጵያ መዳን ነው። ይሄን እንዴት ሳቱት! ወይንስ ሆን ብለው ነው? ወይንስ ለዐማራው ሲሆን ሎጅክ ባፍ ጢንባሩ ይደፋል! ዐማራው ዐማራ ሆኖ መደራጀት ለምን እንቅልፍ ነሳቸው!
እስኪ በቀላል መንገድ የዐማራውን ትግል እንደገና ልግለጥ። ዐማራው የሚታገለው፤ በዐማራነቱ የሚደርስበትን በደል ትክክል አይደለም፤ ብሎ ነው። በዚህ በዐማራነቱ ደግሞ፤ ከማንም የበለጠ በደል ደርሶበታል። ይህ በደሉ ደግሞ፤ በኢትዮጵያ ሶማሌ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በኦሮሚያ፣ በቤንሻንጉል፣ በትግራይ፣ በጋምቤላ፣ በዐማራ ቦታዎች ሁሉ ነው። በበላይነት የትግሬዎች ገዥ ቡድን ሲቀመጥ፤ በበታችነት ደግሞ፤ ይሄው ገዥ ቡድን የፈለፈላቸው የስም ድርጅቶችና ለሆዳቸው ያደሩ ዐማራዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ትግሬዎች፣ ሶማሌዎች፣ ቤንሻንጉሎች፣ ደቡቦች አባሪነታቸውን አስመስክረውበታል። ከመንግሥቱ መዋቅር ወጥቷል። የዘር ማጥፋት በደል እየተፈጸመበት ነው። ይሄን የመሰለ በደል በሌሎች ላይ አለተተገበረም። እንግዲህ ይህ፤ በጠቅላላ ኢትዮጵያዊያን ላይ የትግሬዎች ገዥ ቡድን ካደረሰው በደል ተጨማሪ፤ በተለይ በዐማራው ላይ የተደረበውን ለመጥቀስ ነው። ታዲያ ዐማራው መደራጀትና ራሱን ከዘር ማጥፋት መከላከል የለበትም ወይ?
ኤፍሬም ማዴቦ፤ በተለይ እኔን፤ ቀጥለውም ተመሳሳይ አመለካከት ያለንን በማንሳት፤
“የዚህ ስብከት መሰረተ ቢስነት የሚጀምረዉ ከሰባኪዎቹ ማንነት ነዉ። የዚህ ስብከት ሰባኪዎች ከጥቂትአመታት በፊት አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ከኦነግ ጋር ዉይይት ሲጀምሩ “በዘር ከተደራጀ ድርጅት ጋርዉይይት እንዴት ተብሎ” እያሉ ዉይይቱን ይኮንኑ የነበሩና ባጠቃላይ በዘር መደራጀት ኃጢያት ነዉ እያሉየሚራገሙ ግለሰቦች ነበሩ። እነዚህ ግለሰቦች ከላይ ከሰማይ ተቀብተዉ የተላኩ የዘመናችን ነቢያትካልሆኑ በቀር የኦሮሞን በዘር መደራጀት ኃጢያት የነሱን በዘር መደራጀት ፅድቅ የሚያደርገዉ ምንምምክንያት ሊኖር አይችልም። ማንም ተደራጀ ማን የዘር ፓለቲካና በዘር መደራጀት የአንድን አገር ፖለቲካየአልጋ ቁራኛ የሚያደርግ መርዝ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ብሄር በተናጠል የሚወስዳቸዉ እርምጃዎችየኢትዮጵያን ህዝብ ነፃነት ሊያራዝመዉ ወይም ሊያሳጥረዉ ይችላል፥ ከዚህ በተረፈ ግን ማንም ብሄር በራሱወይም ብቻዉን የኢትዮጵያ ነፃነት ዋስትና መሆን አይችልም። የኢትዮጵያ ነፃነት ዋስትና የኢትዮጵያ ህዝብነዉ።”
በማለት፤ እሳቸውን ጻድቅ፤ ሌሎቻችን ግን ርጉም በማድረግ ስለዋል። ድንቅ ልበልና፤ ውስጡ ልግባ።
በመጀመሪያ ኤፍሬም ማዴቦ ያልገባቸው ነገር አለ። ሊገባቸው ያልፈለጉት ቢባል ይቀላል።
ለኤፍሬም ማዴቦ፤
“ያንተን ጉዳይ  ‘እኔ አዉቅልሃለሁ’ የሚባልበት ዘመን አክትሟል።”
አሉን። ታዲያ እሳቸው መለኮታዊ ሥልጣናቸው ነው፤ ዐማራውን፤ “እኔ በምልህ መንገድ ብቻ ነው መታገል ያለብህ!”  እንዲሉ የፈቀደላቸው?
“እዉነቱን እንናገር ከተባለ የአማራዉ በዘር መደራጀት በአንድ በኩል ህወሓት ከተቃዋሚዉ ጎራ የሚፈልገዉ ትልቁ ስጦታ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የአማራዉ በዘር መደራጀት ኢትዮጵያ ከተጋረጡባት አደጋዎች ሁሉ ትልቁ ነዉ።”
“ለመሆኑ በአማራዉ በዘር መደራጀት ኢትዮጵያ ተጎድታ አማራ የሚጠቀምበት ሁኔታ አለ? መልሱን አማራዉበዘር መደራጀት አለበት ብለዉ ለተነሱ ጥቂቶች እተዋለሁ።”
ይሉናል። ኤፍሬም ማዴቦ፤ ምን ለማለት ፈልገው ነው። ለምን በቀጥታ፤ “ኢትዮጵያና ዐማራ የማይገናኙ፤ ፍጹም የተለያዩና የማይዛመዱ ሁለት ተቃራኒ አካላት ናቸው!” ብለው በግልጽ አይወጡም። ዐማራው ሲጠቀም ኢትዮጵያ ለምን ትጎዳለች? ይህ ምን ማለት ነው? ዐማራውና ኢትዮጵያ ለምን በአንድነት የሚጠቀሙበት ሁኔታ እንዳለ መረዳት አልፈለጉም! ለምን ዐማራውን የኢትዮጵያ አካል አድርጎ መቀበሉ ቸገራቸው? ከዚህ የከፋ ዘረኝነት ከየት ይመጣል? ማንስ ኢትዮጵያ ተጎድታ ዐማራ ይጠቀም አለ? እስከማውቀው ድረስ፤ ኢትዮጵያን አፈራርሰን ኦሮሞን እንገነባለን ያሉት እሳቸው አብረዋቸው ለመስራት የፈለጉት ሰዎች ናቸው። በቪዲዮ ተመልክቼዋለሁ። ታዲያ ዐማሮች ይሄን አሉ የሚሉበትን ማስረጃ ያቅርቡ! አለያ ዋሾው ማን እንደሆን እንረዳ!
“እነዚህ ግለሰቦች ከላይ ከሰማይ ተቀብተዉ የተላኩ የዘመናችን ነቢያት” የሚለው አረፍተ ነገር፤ በድብቅ ዐማራውን የትግሬዎቹ ገዥ ቡድን ባጠቃው መሳሪያ ጎኑን መውጋት ነው። ይሄን ማየት ማንም አይሳነውም። በግልጽ እኮ ብለውታል። ምነው በድብቅ ደግሞ መጨመር አስፈለገዎ! ይሄን ከዚህ በላይ አልሄድበትም።
ዐማራው አሁንም፤ ኢትዮጵያን የሚያድናት የኢትዮጵያዊያን መሰባሰብና በአንድነት መታገል መሆኑን ያምናል። እንዲያውም ሁሉ እንዲተባበርና ባንድነት እንዲታገል ዐማራው ይፈልጋል። ዐማራው ግን፤ በዚያ ለመሳተፍ፤ መጀመሪያ መኖር አለበት። ራሱን በሕልውና ማኖር ደግሞ የዐማራው የተፈጥሮ ግዴታ ነው። ይሄን ለምን ኤፍሬም ማዴቦ መረዳት አቃታቸው! ወይንስ አይፈልጉም። ወይንስ እያወቁ የለም ብሎ መካዱ የፖለቲካ ጉዟቸውን ያቀናላቸዋል! አዛዥ ናዛዡ እሳቸው ናቸው። ምናለ ታዲያ፤ እሳቸው ለራሳቸው እንደሆኑ፤ የኛን ለኛ ቢተውልን! ዐማራው ለካስ በኤሬም ማዴቦ ስሌት፤ ከቁጥር አይገባም!
አዎ! በግልጽ እንነጋገር ከተባለ፤ ድርጅታቸው ከኤርትራ ተነስቶ፤ በኢትዮጵያን ወዳዱ ኢሳያስ አፈወርቂ ታግዞ፤ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው በዐማራው መሬት ነው። አሃ! ዐማራው ከተደራጀ፤ ይሄ መንገዳቸው፤ ከተጓዙ ማለት ነው፤ ችግር ሊገጥመው ነው። እናም ዐማራው መደራጀት የለበትም። ከተደራጀ ደግሞ፤ በኤፍሬም ማዴቦ ፍላጎትና ፈቃድ ብቻ መሆን አለበት። ታዲያ ይሄን በግልጽ ለምን አያስቀምጡትም! አይ ፖለቲከኛ! ፖለቲከኛ ሲጠማዘዝ ይኖራል! ግቡን እስኪመታ!!!
“ከዘረኛዉ የህወሓት አገዛዝ ነፃ ለመዉጣት ብቸኛዉ መንገድ እንደ ህወሓት በዘር መደራጀት ሳይሆንኢትዮጵያዊ ሆኖ በጋራ መታገል ብቻ ነዉ።”
ኤፍሬም ማዴቦ!
ዐማራው ብቻ ነው በዘር የተደራጀው? ለምን ዐምራው ሲደራጅ ይሄን ለመናገር ጣደፉ? አይፍሩ ኤፍሬም ማዴቦ። ዐማራው ከኢትዮጵያ ነፃ ሊወጣ እየታገለ አይደለም። ዐማራው አሁንም ለአስረኛ ጊዜ ልድገመውና፤ የሚታገለው፤ ሕልውናውን ለመጠበቅ ነው። የመንግሥት ሥልጣን ለመጨበጥ መርኀ-ግብር ነድፈው፤ መንግሥታዊ ፖሊሲ አውጥተው የተነሱ ሌሎች ነፃ አውጪ ድርጅቶች ናቸው። ራሱን በመከላከል ያለው ዐማራ አይደለም። በሁለት ቢላዋ መብላቱን ያቁሙ። በዚሁ በዘር መደራጀትን አስመልክቶ፤ በአንድ በኩል ዐማራውን እያወገዙ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከሌሎች ጋር እየተሞዳሞዱ፤ የድርጅትዎን የሥልጣን ሩጫ፤ በዐምራው ወጣት ጉሮሮ ለመሰንቀር የሚጥሩት ዋጋ የለውም። አሁንም ዐማራው ራሱን እየጠበቀ፤ በራሱ ተደራጅቶ፤ ከሌሎች ወገኑ ጋር ይሄን የትግሬዎች ገዥ ቡድን ይጥላል። ከዚያ የሚቀጥለውን የሀገራችንን ሁኔታ፤ በትግሉ ሂደት፤ ታጋዮቹ የሚወስኑት ይሆናል። ዐማራው ግን፤ አሁንም ሆነ ኋላ፤ ይሄን የመሰለ የዘር ማጽዳት በደሉ በማያዳግም ሁኔታ የማይከሰትበትን ሀቅ የመፍጠር ተፈጥሯዊ ግዴታ ስላለበት፤ ያለርስዎ ፈቃድ ይቀጥላል።
አያምታቱት። ነጋዴዎችን፣ ባህል ጠባቂዎችን፣ ምን የተረፈዎ አለ! ብቻ ሁሉንም ከርስዎ በስተቀር ወንጅለው፤
“ . . . ዛሬ ተወልደን ያደግንባት አገራችን ኢትዮጵያ የማናዉቃት አገር ሆናለች። ባህላችን ከመረሳቱ የተነሳ ባህል ያለን ሰዎች አንመስልም። ማህበራዊ እሴቶቻችን ከመዉደማቸዉ የተነሳ ነጋዴዎቻችን በርበሬና ቀይ አፈር ቀላቅለዉ መሸጥ ጀምረዋል። የመሪዎቻችን አዋቂነትና ትልቅነት የሚለካዉ በሚናገሩት የዉሸት አይነትና መጠን ሆኗል። የሀይማኖት መሪዎቻችን ተበዳዮች በዳዮችን ይቅርታ እንዲጠይቁ ማግባባት ዋና ስራቸዉ ሆኗል። ሽማግሌዎቻችን ህሊናቸዉን ሽጠዉ የነብሰ ገዳዮች ተላላኪ ሆነዋል። አንድነታችን ከመላላቱ የተነሳ ጎረቤቶቻችን ንቀዉናል።”
በማለት ከሰማይ የተላኩ አዳኝ ነብይ ሆነውልናል። በሚያመችዎ መንገድ ከግራ ቀኝ እየረገጡ፤ ሰማይ ሊደረመስ ነውና፤ ለኔ ድርጅት ድረሱልኝ ማለትዎ፤ የፖለቲካ ስልትዎ ግቡን ለምምታት ምን ያህል ርቀት እንደሚጓዝ አሳዩን።
በርግጥ የሚመከሩ ቢሆን ኖሮ፤
“የለም፤ የሚታገለውን ክፍል ወደ አንድ ለማምጣት፤ የግድ የአንዱ ድርጅት ፍላጎት ብቻ ሳይሆን፤ የሁሉንም ማዳመጥና፤ ከምን እንደተነሱ አጢኖ፤ የጋራ የሆነውን በመፈለግ፤ መቀራረብ እንዲኖር መጣር ነው። እናም እኔ ካልፈለግሁት በሺታ ነው የሚሉትን ትተው፤ ሌሎችን፤ እኛ እንዲህ ነን የሚሉትን ተቀብሎ፤ በራሳቸው ገለጻ ያቀረቡትን ማንነት ለመረዳት መጠጋት ተገቢ ነው።”
ባልኩዎት ነበር። ነገር ግን ያን ብል እርስዎን አያውቁም ብሎ መስደብ ይሆንብኛል። በያዙት መንገድ ቸር ይግጠምዎ!

August 9, 2015
ይገረም አለሙ
የአርበኞች ግንቦት 7 ቃልን ወደ ተግባር የማሸጋገር እንቅስቅሴ ያሸበረው ወያኔን ብቻ አለመሆኑን ከተቃውሞው ጎራ ከሚሰማው የተቀዋሚ ተቀዋሚዎች ጩኸት እያየን ነው፡፡ ርጥቡ ሬሳ ደረቅ ያስነሳ አንዲሉ ይህ ሰሞነኛ ጩኸት የተረሳ እንዲታወስ የተተወ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኖ የአንዳንዶቹ ጯሂዎች የትናንት ማንነት ድብቅ ዓላማና ፍላጎት ጭምር ጸሀይ እንዲሞቀው እየተደረገ ነው፡፡ የማለባባስ አጉል ባህላችንን ተራምደው የይሉኝታ ገመዳችንን በጥሰው ስም እየጠቀሱ መረጃና ማስረጃ እያጠቀሱ አካፋን አካፋ ለማለት ለደፈሩ ወገኖቼ ያለኝን አክብሮት እገልጻለሁ፡፡ እያለባበስን አርባ አመት አልቅሰናልና በቃ ማለት ይኖርብናል፡፡The Patriotic Ginbot 7 attacks factors
አደባባይ ወጥተው የሚጮኹትም ሆኑ ከኋላ ሆነው የሚገፉት የየግል ፍላጎታቸውም ሆነ አንድ የሚያደርጋቸው ምክንያት ምንነትና አንዴትነት በተለያዩ ሰዎች ተጽፋል፡፡ እውነት ናቸውና መስማማቴን እየገለጽሁ ያልተገለጸ የመሰለኝን ልጨምር፡
ስማቸው ብዙ ነው (ፖለቲከኛ ፣ጋዜጠኛ፣ነጻ ማህበር፣ወዘተ) መገኛቸው ሀገር ውስጥም ውጪም ነው፤ዓላማቸው ቢችሉ ምን-ይልክ ቤተ መንግሥት መታየት ካልሆነም በተቀዋሚነት ካባ አንድም ክብር ሁለትም ብር እያገኙ መኖር ነው፡፡ ተባብሮ መስራት አይሆንላቸውም፡ እነርሱ የሚመሩት ወይንም በቀጥታም ሆነ በተዘዋወዋሪ የሚቆጣጠሩት ካልሆነ በስተቀር ማናቸውም ትግል (ሰላማዊውም የጠብ-መንጃውም) አንድ ርምጃ ሲራመድ ማየት አይፈልጉም፡፡
ሲያልሙት የኖሩትን ሥልጣን ለማግኘት የሚቻለው ደግሞ አንድም በምርጫ አንድም በጡንቻ ነው፡፡እነርሱ በሁለቱም መንገድ ለመሄድ አይችሉም፡፡(አንዳንዶቹ ሁሉን ሞክረው የከሸፈባቸው ናቸው፡፡) የምርጫው ነገር እንኳን ለእነርሱ ፓርቲ መስርተው በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው መቀመጫቸውን ሀገር ቤት አድርገው ለሚፍጨረጨሩትም አልተሳካም፡፡ ሀገር ቤት በሚገኙ ተቀዋሚዎች ተከልለው ያደረጉት ሙከራም አልተሳካም፡፡ ( የኢትዮጵያ ዴሞክራሲዊ ኃይሎች ህብረት ይጠቀሳል) የጡንቻውን መንገድ ቢያልሙትም አልሆነላቸውም፤ አይሆንላቸውም፡፡ ከሌሎች ጋር ተባብረው በተቀዋሚነት ተከብረው ለመኖር፤ ከተቻለም ተከልለውም ቢሆን ወደ ምኒልክ ቤተ መንግሥት ለመድረስ መከጀላቸው ባይቀርም መሪነቱን እነርሱ ካልያዙት ወይንም እንቅስቃሴው በቀዳሚነት የእነርሱን ዓላማና ፍላጎት የሚያሳካ ካልሆነ በጅ አይሉምና፡ በዚህም መንገድ ስንዝር መራመድ አልቻሉም፤አይችሉምም፡፡
ስለሆነም ያላቸው ምርጫ ላለፉት ሀያ አመታት ሲተገብሩትም ያየነው ተቀዋሚ እየተባሉ መኖር ነውና በሰላማዊ ትግል በተአምር፣ ወይንም በተቃራኒው መንገድ በጦር የወያኔ ሥልጣን ቢቀየር ይህን ስለማያገኙ ጠንከር ያለ እንቅስቃሴ ሲጀመር ፈጥነው ይዘምቱበታል፡መገንባቱን ሳይሆን ማፍረሱን፣ ማቀራረቡን ሳይሆን ማለያየቱን፤ መደገፉን ሳይሆን ማደናቀፉን የተካኑበት ናቸውና እስካሁን በአብዛኛው ተሳክቶላቸዋል፡፡ ዛሬ ግን ተነቅቶባቸዋልና ድብቅ ማንነታቸውን ያጋልጡ፣ ቀሪ ህይወታቸውን ያበላሹ ለልጆቻቸው መጥፎ ስም ያቆዩ እንደሁ አንጂ የሚሳካላቸው አይመስለኝም፡፡
ፊሺካው ተነፍቷል ጦርነቱ ተጀምሯል በተባለበት ማግስት በፍጥነት ተጠራርተው ከጀመሩት ጫጫታ ውስጥ አንዳችም መፍትሄ ጠቋሚ ሀሳብ አለመኖሩ ከመነሻው በተቃውሞው ሰፈር ይገኙ እንጂ ለውጥ ናፋቂ ሳይሆኑ ወሬ አሟሟቂ፤ የተግባር ሳይሆን የምላስና የብዕር ታጋዮች መሆናቸውን የመሰከረ ነው፡፡ ትናትም ሆነ ዛሬ ሰላማዊውንም ሆነ የጠብ-መንጃውን ትግል የሚቃወሙት ተቀዋሚ እየተባሉ ሆነው ሳይሆን እያስመሰሉ፣ እየታገሉ ሳይሆን እያውደለደሉ ክብርም ብርም የሚያገኙበት ሜዳ እንዳያጡ በመስጋት ነው፡፡ ግን ለምን? እነርሱ በተቃዋሚነት እንዲኖሩ የወያኔ እድሜ መርዘም አለበት? የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንባ ገነን አገዛዝ ውስጥ መኖር አለበት ?ከእነርሱ ፍላጎትና ከሀገር ነጻነት የቱ ይበልጣል?፤የቱ ይቀድማል፡? በእውነቱ አሳፋሪም በታሪክና በትውልድ የሚያስጠይቅም እኩይ ተግባር ነው፡፡
ይህ አድራጎት ዛሬ የተጀመረ አይደለም፤ እንደውም ከአንዳንዶቹ ጋር አብሮ ያረጀ ነው፤ ትንሽ የቅርብ ግዜ ማሳያዎችን አንመልከት፡
ማሳያ አንድ፤ በ1992 ዓም ኢዴፓ የሚባል ፓርቲ ተመስርቶ በአጭር ግዜ ሰፊ እንቅስቃሴ አደረገና እውቅና አገኘ፤ በዚህ መልኩ እየገነነ ከቀጠለ በግልም ሆነ በድርጅት እስከመኖራቸውም እንዳይረሱ የሰጉት እነዚህ የወያኔም የተቀዋሚውም ተቀዋሚዎች የለመዱትንና የተካኑበትን የማደናቀፍ ዘመቻቸውን ከፈቱበት፤ የፓርቲው አመራሮች ቢቸግራቸው በእነዚህ ሰዎች በተወጠነውና በምድረ አሜሪካ በተዘጋጀ ጉባኤ ተካፋይ ሆነው የኢዴኃህ አባል ሆኑ፡፡ ሊቀመንበሩ ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ የህብረቱ ዋና ጸኃፊ ለመሆን ቢበቁም ከመነሻው የተገባው በእምነት ሳይሆን የሰዎቹን አፍራሽ ዘመቻ በመፍራት ነበርና ብዙም ሳይቆይ ፓርቲው ከህብረቱ ወጣ፣ መኢአድ ለጉባኤ የላካቸው አባላቱ ሀገር ቤት ሳይመለሱ ነበር ጉባኤው በእነዚህ ሰዎች ሴራ መጠለፉን ገልጾ የጉባኤውን ሂደት በመቃወም ጥያቄ አቅርቦ፤ጥያቄው ካልተመለሰ እንደማይቀጥል ያስታወቀው፡፡ ኢዴኃህም የቡና ውሀ ሆነ፡፡ (በምርጫ 97 የሰሩትም የሚረሳ አይደለም፡፡)
ማሳያ ሁለት፤ ቅንጅት ሲመሰረት መሪነቱን እንያዝ እንዳይሉ ከመስፈርቱ አንዱ በሀገር ቤት ያሉ የሚል በመሆኑ፣ እነርሱ ደግሞ አብዛኛዎቹ ከሀገር ውጪ ስለሚኖሩና ሀገር ቤት ፓርቲ ስለሌላቸው አልተቻላቸውም፤ በእጅ አዙር አንዳይቆጣ ጠሩት ከቅንጅት የወቅቱ ጥንካሬ አንጻር ለዛ የሚያበቃ አቅም አልነበራቸውም፡፡ እናም በሚያውቁት በለመዱትና በተካኑበት ስልትና መንገድ ብዙ ዘመቱበት፤ ወዳጅ መስለው በመቅረብ መጥፎ እየመከሩ አቅጣጫ ለማሳት፣ በአመራሩ መካከል መጠራጠር ለመፍጠር ብሎም ቅንጅትን ከመረጠው ሕዝብ ለማጣላት ከውጪም በሀገር ውስጥም በመልእክተኞቻቸው በኩል ብዙ ሰርተዋል፡፡ የቅንጅት አመራሮች ለፓርላማ ሳይሆን ለወህኒ ሲዳረጉም ተደስተዋል፡፡
ማሳያ ሶስት፤ የቅንጅት አመራሮች ከእስር ከወጡ በኋላ የፈጠሩት አለመግባባት እስከ መለያየት እንዲያደርሳቸው ከሁለቱም ወገን ደጋፊ መስለው በመሰለፍ የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል አይነት የተጫወቱት አፍራሽ ሚና ቀላል አይደለም፡፡ ይህን ለማረጋገጥ በወቅቱ በዌብ ሳይቶች በጋዜጦችና በማህበራዊ ድረ-ገጾች ወዘተ ላይ የተጻፉትን ማየት በየፓልቶኩ በያራዲዮው የተነገሩትን ማደመጥ በቂ ነው፡፡
ማሳያ አራት፤ የቅንጅት ከፊሉ ወገን ተሰባስቦ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ሊቀመንበሩ አድርጎ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ የተሰኘ ፓርቲ መስርቶ በአጭር ግዜ በሀገር ውስጥም ሆነ አውሮፓና አሜሪካ ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የተበለጥን ሰይጣናዊ ስሜታቸው አገርሽቶ የከፈቱት ዘመቻም የሚረሳ አይመስለኝም፡፡(በአብዛኛው የሚዘምቱት ሀገራዊ ድርጅት ላይ ነው)
አንድነት የቅንጅት ወራሽ መሆኑና ( ቅንጅት የሚለው ስምና ሁለት ጣት ምልክት ወያኔዎችን ያባንናቸዋል)ከጅምሩ ያገኘው ተቀባይነት ያሰጋው ወያኔ ወ/ት ብርቱካንን ዳግም ሲያስር ለእነዚህ ሰዎች ፌሽታ ነበር፡፡አጋጣሚውን በመጠቀምም ቀሪዎቹን አመራሮች ከቅርብም ከሩቅም ወዳጅ መስለው በመቅረብ በምክርም በገንዘብም በሌላ ሌላውም ከወዲያ ወዲህ እያላጉ የት ይደርሳል የተባለውን አንድነት ሽባ አደረጉት፡፡ የእነርሱም የወያኔም ሴራ ተደማምሮ አንድነት አምስት አመት ሙሉ ታሞ በምርጫ 2007 ዋዜማ ግብአተ መሬቱ ተፈጸመ፡፡ እናቃብራችሁ አንኳን አላሉም፡፡
ማሳያ አምስት፤ ሰማያዊ – ይህኛውም ፓርቲ በ2004 ዓም ተመስርቶ በአጭር ግዜ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ለስድስት አመት የተዘጋን የሰላማዊ ሰልፍ ክልከላ በር አስከፈተ ተብሎ ስሙ ሲናኝ የሌላው መግነን የእኛን መኮስመን ያስከትላል የሚል ከይሲ አስተሳሰብ ያላቸው እነዚህ ወገኖች ዘመቻ የጀመሩት ከመቅጽበት ነው፡፡
ይሉት ቢያጡ ሰበብ ቢቸግራቸው ከሌሎች ጋር ተባብሮ መስራት አለበት ብቻውን የትም አይደርስም አሉ፡፡ አልተሳካላቸውም እንጂ ይህን ሰበብ አድርገው በፓርቲው ውስጥ ክፍፍል እስከመፍጠር ደርሰውም እንደነበር ይታወቃል፡፡ሌላም ሌላም መጥቀስ ይቻላል፡፡አንድ ፓርቲ ጠንክሮ እንዳይወጣ ወይንም ፓርቲዎች ተባብረው በግንባርም ይሁን በውህደት ጠንክረው እንዳይታገሉ ካደረጉዋቸው ምክንያቶች አንዱ የእነዚህ ወገኖች ሴራ ነው፡፤
እነሆ አሁን ደግሞ የተለመደውንና መታወቂያቸው የሆነውን አፍራሽ ተግባር ጀመሩ፡፡ የኢሳይያስ ማንነትና የሻዕቢያ ምንነት የታያቸው ዛሬ ነው ? ጅብን ሲወጉ በአህያ ተከልሎ እንደሚባለው ይህ ሰበብ ነው፡፡ ዋና አላማው ኢሳይያስንና ሻዕቢያን ከለላ አድርጎ በነጻነት ትግሉና ታጋዮቹ ላይ መዝመት ነው፡፡
ተቃውሞአቸው ምንድን ነው፡፡
የሚያነሱት ነገር ለክርክር እንዳይቀርብ ለመለስ ምትም አንዳይመች ተቃውሞአቸው ስልታዊ መንገዳቸው የጎንዮሽ ነው፡፡የሚደግፉትም ሆነ የሚቃወሙት ነገር በግልጽ አይታወቅም፤ ዛሬ ያመሰገኑትን ነገ ይኮንኑታል፤ባከበሩ ማግስት ያዋርዳሉ፤ የእነርሱ የሆነ ሁሉ ቅዱስ በተቃራኒ የቆመ ወይም ለእነርሱ ያልተመቸ ሁሉ ርኩስ ነው፡፡ እነርሱ ሞክረውት አላስኬድ ባላቸው መንገድ ሌሎች መሄድ ከቻሉ በቅናት ያራሉ፡ እነርሱ ሊወዳጁት ያልቻሉትን ሰው ወይንም ድርጅት ሌሎች መወዳጀት ከቻሉ የውግዘት ናዳ ያወረዳሉ፤ እነርሱ ሞክረውት ያቃታቸውን ሌሎች ለማሳካት ከጀመሩ የማጥላላት ጥሩንባ ይነፋሉ፤ በታላቁ መጽኃፍ ትንቢተ ኢሳይያስ ም፣48 ቁ.22 ላይ “ክፉዎች ሰላም የላቸውም” ተብሎ እንደተጻፈው በክፋታቸው ለራሳቸው ሰላም አጥተው ሌላውንም ሰላም ያሳጣሉ፡፡
የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ተብሎ አንዳይተው፣ ዓላማችን ላሉት ስኬት አስበው ወቅት ጠብቀው የሚሰሩ መሆናቸውን አይተናል እያየንም ነው ፡፡ የተለመደ ተግባራቸው ነው ተብሎ ተንቆ አንዳይተው ብእራቸውም ሆነ ምላሳቸው የሚረጨው መርዝ ለትግሉ ውጤታማነት ሆነ ከድል በኋላ ለሚፈለገው መረጋጋት ብሎም ለኢትዮጵያውን አንድነት ጠንቅ ነው፡፡ መፍትሄው አላማችሁ ገብቶናል በቃችሁ ማለት መቻል ነው፡፡ይሄ ካልበገራቸውም ማንነታቸውን ጸሀይ ማሞቅ፡፡
የተግባር ሳይሆን የምላስና የብዕር ታጋዮች
May 20, 2017 at 1:29 p