By ሳተናው
May 20, 2017 19:09
ኤፍሬም ማዴቦ
ሚር ማደቦ ጥሩ ፖለቲከኛ ይሁን አይሁን አላውቅም ነገር ግን ጥሩ ፀሃፊ አይደለም ። ያ ማለቂያ የሌለውና እንደ ስምጥ ሸለቆ የተጠማዘዘና የተንዛዛ ፅሁፍ ግማሹ በአውሮፕላን በአየር ላይ ስላደረገው ጉዞ የሚተርክ ነው። አቶ ኤፍሬም ከሚንሳፈፍበት አየር ላይ መሬት ይወርዳል ብዬ ብጠብቀው ብጠብቀው አልወርድ ሲል እኔም ማንበብ የጀመርኩትን ፅሁፍ ዘግቸው እብስ አልኩኝ ።

ሰሞኑን የእሱን ፅሁፍ ትእግስቱ ኖሮኝ ከጨረስኩት ሙሉ አስተያየቴን ይዤ እቀርባለሁኝ ። እስከዛው ግን ለአቶ አፀፍሬም ማደቦና የሱን ሃሳብ ተጋሪዎች ይችን አጭር ነገር ልበል ።
አንድ ህዝብ ለነፃነት፣ ለዕኩልነትና ለብልጽግና በሚያደርገው ትግሉ፣ የትግሉ መሰካትና ያለመሳካት ሊወሰን የሚችለው በራሱ በህዝብ ንቃተ ህሊና ስፋትና ጥንካሬ፣ እንዲሁም ድክመት ነው። የአንድን ህዝብ ብሶት በደንብ አዳምጦና ተረድቶ፣ እንዲሁም ደግሞ ተጨባጭ ሁኔታዎችን አንብቦ የህዝቡን የ ትግል አቅጣጫ ፈር የማሲያዝው ከራሱ ከህዝቡ አብራክ የወጡት ልጆቹ ናቸው።
የራስን ማንነት መምረጥ እና ማሳወቅ እና በማንነትም ዙሪያ ተሰባስቦ መታገል የማንኛውም ብሄር ብሄረሰብ መብት ነው። አማራ በማንነቱ ዙሪያ ለመታገል የከምባታ ፣ የሱማሌ ወይም የኦሮሞ ቡራኬ አያስፈልገውም።
የኦሮሞን ፣ የሱማሌን ፣ የአፋሩን የትግሬውን መደራጀት አጨብጭበው እየተቀበሉ የአማራው መደራጀት ዝቅ አድርጎ ማየት ወይም ከነጭራሹ ‘የለም’ ብሎ መከራከር መሰሪነት ብቻ ሳይሆን አላዋቂነት ነው።

አማራ ከዚህ በኋላ appeaser አይሆንም። አማራ እስካሁን ቀድሞ ዝም ባይልና በብሄሩ ቢደራጅ ኖሮ ብዙ ለውጥ ሊፈጠርና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦቹ ላይጠፉ ይችሉ ነበር።
በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር የሆነው ዊንስተን ቸርቺል ይህን አይነት ሌላውን ለማስደሰት ራስን የመጉዳት ፖሊሲ ሲገልፀው እንድህ ብሎ ነበር <<፥ An appeaser is someone who feeds a crocodile hoping it will eat him last. >> አለ። እውነትም፥ አስደሳችና የማያስቆጣ ሰው ዐዞው ራሱን እስኪበላው ድረስ ጊዜ ለመግዛት ዐዞውን የሚቀልብ ሰው ማለት ነው።
አማራ ለ25 አመታት Appeaser ሆኖ ኑሯል ። የሚበሉትን አዞዎች ሲቀልብ ኖሯል ።መበላት ካልቀረ ማብላት ጠቀሜታው ምንድር ነው?
ዝም የማይባሉ ጉዳዮች ላይ ዝም ማለት ጉዳትና ውርደትን ከእልቂት ጋር መጥራት ነውና ዝም ማለት ተገቢ አይደለም ።አማራም ከዚህ በኋላ ዝም አይልም።