ቅጽ 45 .2 ግንቦት 2009

አገራችን ወደከፋ አጣብቂኝ ውስጥ እየገባች ነው!

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማክተሚያ ጀምሮ ዓለማችን ርዕዮተዓለምን መሠረት ባደረጉ ሁለት ጎራዎች ተከፍላለች። የምዕራቡ ክፍለዓለም በኃያሏ አሜሪካ መሪነት ወደ አንድ ጎራ ሲሰባሰብ፣ የምሥራቁ ክፍለዓለም ደግሞ በዚያን ጊዜ ኃያል በነበረችው በሶቪዬት ኅብረት ዙሪያ ጎራውን ለይቶ ቆመ። አወሮጳም በዚሁ ምክንያት ድንበር ተከልሎላት ምዕራብና ምሥራቅ ተብላ ተከፈለች። ከዚህም ጋር ተያይዞ ሁለት ከፍተኛ የወታደራዊ ቃል ኪዳን ድርጅቶች ተመሠረቱ። በምዕራቡ ዓለም የሚመራው ኔቶ (NATO) ተብሎ ሲሰየም፣ በምሥራቁ ጎራ ያለው ደግሞ በሶቪዬት ኅብረት መሪነት ዋርሶ (WARSAW) ተብሎ ተሰየመ። አርባ አምስት ዓመታት በቆየው በዚህ የክፍፍል ወቅት ሌሎች ሁኔታዎችም ተከስተዋል። ለምሳሌ በርካታ የእስያና የአፍሪቃ አገሮች ከቅኝግዛትነት ተላቀው ነፃ አገሮች ሆነዋል።

ለማንበብ(PDF)ይህን ተጫኑት⇓

https://ethiopanorama.comwp-content/uploads/2017/05/Demo-Vol-45-No-2.pdf