የምንገኝበት ዓለምና ወቅት ምን ይመስላሉ?

ኢትዮጵያ በርግጥም በዓለም ውስጥ ተበታትኖ ለሚኖረው ጥቁር ሕዝብ ተስፋ ሰጪና አበረታች ምሣሌ ሁና ኑራለች። በአፍሪካ ውስጥ በተለይም ከሳሃራ በታች ባለው ክፍል በቅኝ ግዛትና በነጭ ወራሪዎች አገዛዝ ሥር ይማቅቁ ለነበሩት የነፃነት ትግል ኢትዮጵያችን የማይታበል ትልቅ አርዓያነት ነበራት። ኢትዮጵያውያን/ት ራሳችንም በተለይ ከ1983 ዓም በፊት የነበረው ትውልድ አባላት እጅግ በጣም በርካታዎቻችን በኢትዮጵያዊነታችን ኮርተንና፣ በሄድንበት ሁሉ ራሳችንን በባህሪአችንና በተግባሮቻችን አስከብረንና ተከብረንም ነበር የኖርነው። እሰይ፣ የምሥራች የሚያሰኝ ነው፣ አሁን ደግሞ ልክ እንደ ወትሮዎቹ ለመብቱ የሚቆምና በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ አዲስ ትውልድ እየበቀለልን ነው። ይህ የሆነው ኢትዮጵያ የምትታወቅባቸው፣ ኢትዮጵያውያን/ት የምንኮራባቸውም ክህሎት፣ እሴቶች፣ ፀጋዎችና ቅርሶች ስለነበሩንና ስላሉንም ነው። እንዲያው ስለምንኩራራና ስለምንኮፈስ ብቻ አልነበረም።

ለማንበብ (PDF)ይህን ይጫኑት⇓

https://ethiopanorama.comwp-content/uploads/2017/06/Untitled-1.2pdf.pdf