ጌታቸው ረዳ ( ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ )

ከቴዎድሮስ እስከ ቴዎድሮስ የሚል የግንቦት 7ቱ ለሻዕቢያ ያደረው ምልምል ቅጥረኛ ኤፍሬም ማዴቦ የተጻፈ ፕሮፓጋንዳውን የሚየናፍሱለት በየድረገጹ ተለጥፎ አንባብችሁ ይሆናል። ካላነበባችሁ ሳተናው ላይ የተለጠፈውን በሚከተለውአንብቡ። http://www.satenaw.com/amharic/archives/34222 ይህ መልስ ለፓስተር ለኤፍሬም ማዴቦ ለመጻፍ አልከጀልኩም ነበር፤ ያውም ሌላ የሳምነቱ ትችት እየጻፍኩ በነበረበት ወቅት ስለበር፡ እንዲሁም የሰውየው መሰሪነትና ጥበበኛነት በበቂ ሰዎች በሚዲያ ተጋልጣል እና አልፈለግኩም ነበር። ሆኖም ፓስተር ኤፍሬም የተጠቀመበት ርዕስ ማራኪ እና ብዙ ሰው ሊጃጃል ስለሚችል፤ ውስጡን ገልብጦ ማሳየት የኛ ሃላፊነት ስለሆነ በዚህ አጠር ያለ ትችት ጽፌአለሁ።

እላይ ያልጠቀስኩት ነገር በተለይ ይህ መልስ ለመጻፍ አልፈለግኩኝም ነበር ከገፋፋዩኝ መሃከል አንዱ ምክንያት ‘የክንፉ አሰፋ “ኢ ኤፍ ኤም” የሄኖክ ዓለማዮህ “ዘሐበሻ” ላይ ፓስተር ኤፍሬም በላከላቸው በዚያው አጭበርባሪ ጹሑፉ ላይ ከስሩ “ኮመንት” በሚለው ገጽ ላይ ትንሽ ቻር አድርጌ ጽፌ ነበር እና እነዚህ ወዳጆቹ የኔን ትችት ስላገዱት (ድሊት) ስላደረጉት፤ በይፋ እንድተቸው ገፋፉኝ (ሁሌም እንደሚገፋፉኝ ማለት ነው)። ፓስተር ኤፍሬም ከቴድሮስ እስከ ቴድሮስ ጹሑፉ ላነበበ እና የግንቦት 7ቱ ኤፍሬም ማንነት ለማያውቅ ወይንም አብረው ለሚነጉዱ ‘ደደብ ምሁራኖች እና ደደብ ጀሌዎቹ” ግሩም ትችት ነው። ሆኖም ቴድሮስን እና ኢትዮጵያዊነትን እንዲሁም ቴዲን ሲያሞግስ ፤ ኤፍሬም እውን አንዲያ ያለ ሞራል የተላበሰ ሰው ነው ወይ ነው ጥያቄው። ባጭሩ ለጥቀስ፤ እንዲህ ይላል። (1) (ለእንግሊዝ እጅ አትስጡ የሚል ድምፅ መቅደላን አንቀጠቀጣት¬¬ );

የግንቦት 7ቱ አመራር ፓስተር ኤፍሬም ማዴቦ “ቴድሮስ ለወራሪው እንግሊዝ እጅ አትስጡ የሚል ድምፅ መቅደላን አንቀጠቀጣት” በማለት የቴዎድሮስን ምክር በመጠቀም ኤፍሬም የቴዎድሮስን ቃል አክባሪ ይመስል ሰውን ለማጃጃል እና እሱ እራሱ ኤፍሬም ከጠላት ጋር አንዳልወገነ ሁሉ ሌሎችን ሲመክር እንዲህ ያለ ድርቅና/ ዓይን ያወጣ

ቅጥፈት  ምን ትሉታላችሁየሻዕቢያ መሪው ኢሳያስ አማራና ቴድሮስ ያቀናትን አገር ‘ኢትዮጵያ” በጠላትነት ፈርጆ ብዙ መከራ እና ወንጀል የፈጸመ አየወላጆቹን አገር ኢትዮጵያ የከዳ፤ ወደቦቻችን በዓረቦች አንዲያዝ እና እኛም ዳግም በጠላቶቻችን አንደንከበብ ያደረገ የታሪክ ማፈርያ የለየት ጠላት ነው ኤፍሬም እጁን የሰጠው። ኤፍም እጁን ለዚህ ጠላት የሰጠ እና አብሮት የሚኖር ብቻ ሳይሆን ለዚህ ጠላት ጥብቅና ቆሞ በይፋ ኢትዮጵያን የዘለፈ ፤ ኢሳያስ አፈወርቂን ያወደሰ፤ ክፉ ከጂ ነው። ‘ለኤርትራ እጁ የሰጠ ሰው ፤ቴድሮስ ለጠላት አጅ አትስጡ ብሏል ሲለን ለእንዲህ ያለ ‘ድርቅና’ ምን እንበል’? ኤፍሬም አንድ ነግር ላስታውስህ። በቅርብ ባለፈው በሰሞኑ ጽሑፌ ያስታወስኳቸው የምጽዋ ጀግኖች ከአንተው አለቆች “ሻዕቢያዎች” ጋር የተዳሙ እነ ጀኔራል ተሾመ፤ የመሳሰሉ ኢትዮጵያዊያን ጀግኖች “በምንም መልኩ በማንም ሰዓትና ውጥረት ብትሆኑ “ለሻዕቢያ” እጃችሁን እንዳትሰጡ/ እንዳትንበረከኩ/ እነሱ ቤት አንዳትገኙ፤ ለሻዕቢያ እጃችሁን አንዳትሰጡ” ብለው የገዛ ሽጉጣቸውን መዝዘው “የቴድሮስን ቃል በተግባር የተገበሩ” ጀግኖች ቃል አራክሰህ አይደለም አንዴ አንተ ለሻዕቢያ እጅህን ሰጥተህ ከወላጆቻችን እና ጀግኖቻችን ገዳዮች ጋር ተወሽቀህ የምትገኘው? !! ለመሆኑ እነኚህ ጀግኖች ሻዕቢያን “የአራብ ደላላ” ብለው ሲሉዋቸው እኮነው፤ አንተ ኦክላንድ ካሊፎርኒያ (አሜሪካ ውስጥ) በሿኢቢያ ድግስ ተገኝተህ “በባለገው ምላስህ” ቃላቸውን ለማራከስ ስትል “ወራሪዎች ነበሩ/የቅኝ ግዛት አስፋፊዎች ነበሩ፤ የአረብ ደላሎች እያሉ ሲየንኳስሷችሁ ነበሩ” እያልክ በዩቱብ ተቀድቶ ‘ሿኢቢያዎች” ለጥፈውልሃል።

ከጠላታቸው ከሻዕቢያ ጉያ ውስጥ ገብተህ እጃችሁ ለሻዕያ ስጡ እያልክ እራስህ እጅህን ሰጥተህ ሌሎች ምስኪኖችን ለማስገባት ያለ እረፍት አስመራ ውስጥ ሆነህ ስትሞነጫጭር የቴድሮስን ቃል በምሳሌ ስትጠቀም ትንሽ አታፍርም? ምን ታደርግ አንተ?! ባልተወቀረ ጭንቅላት የሚሰሩ አጋዥ ሚዲያዎችህ እና ተከታዮችህ ሲያንጨበጭቡልህ አንተ ምንተ ታደርግ። የነቀዘውን ትውልድ በቴድሮስ ቃል እየገባህ “ኢትዮጵያዊነት ቃል አክባሪ መስለህ ‘ኢትዮጵያዊንተን” ለማጃጃያ ትጠቀምበታለህ።

የሚከተለውም እንዲህ ትላለህ፦

2- (‘ኢትጵያዊነትን’ ትርጉም ብናወቅ ጡንቾቻችንን ጠላት ላይ እንጂ ወዳጅ ላይ አናስርፍም ነበር) ትላለህ።  አታፍረም? ጠላት ጋር ሆነህ በየሻዕብያው ድግስ እየተገኘህ አማራው ላይ {“ነፍጠኛ”} እያልክ የምላስህ ጡንቻ እያስጮህ ትንሽ ሳታፍር “ኢትጵያዊነትን’ ትርጉም ብናወቅ ጡንቾቻችንን ጠላት ላይ እንጂ ወዳጅ ላይ አናስርፍም ነበር” ሰትል ኢትዮጵያዊነትን አክባሪ ትመስል ምክር ስትለግስ ለማያውቅህ አጅግ አደገኛ አጃጃይ ነህ።


እንዲህም ትላልህ፤


3- (
ቴዲ አፍሮ አንድነትንና ኢትዮጵያዊነትን እንጂ የዘመነ መሳፍትን መከፋፈልና ትንሽነት አንሰብክም ነበር።)
አየ ኤፍም ማዴቦ!!! ኢትዮጵያዊነት ብታውቅ ኖሮ ነው ፤ ሻዕቢያ ጎን ተሰልፍህ ኤርትራን ባንዶች ሲያንጨበጭቡልህ ፤ሞቅ ብሎህ “ዓሰብ ዓሰብ” “ኤርትራ ኤርትራ’ “አስራ አራት ክ/ሃገር ዘማሪዎች” እያልክ “ነፍጠኞች የምታላቸውን “አማራዎችን” ታዋርድ ነበር? ከዘመነ መሳፍን ባሰ አገር ከሚገነጥሉ ጋር አብረህ እየዶለትክ ትንሽ ሳታፍር ስለ ዘመነ መሳፍንት ትኮንናለህ። ይገርማል። ጉደኛ ቄስ ነህ!ቴዲ አፍሮን በዚህ ትጠቀምበታለህ፤ አንዲህ ስትል፦

( 4-) { ለዚህ ይመስለኛል አንዳንዶቻችን ቴዲ ለምን “ኢትዮጵያ” ብሎ እንደሚጮህ ያላወቅንለት።} ትላለህ።

ለምን ኢትዮጵያ ብሎ ጮኸ ብለህ እንደሚጮህ አርግጥ ነው አታውቀም። ራስክን ግን ነፃ ለማውጣት አባባሉን አሳምረህ ትጠቀምበተለህ።   አንተ ኢትዮጵያ የምትባል ምንሊከ  ያስረከበህን አገር ስትዘለፍ“’ምኒልከ እያለ ቴዲ ሲዘፍንለት” አንተ ምኒሊክ ወራሪ፤ገዳይ፤ትምክሕተኛ፤ ባለጌ/ስድ (አሮጋንት) በቃላት የሚኮፈስ፤ ባዶ ነበር እያልክ የሰብክ፧!!} ለማያውቅህ ንገረው። “’ምኒልከ እያለ ቴዲ ሲዘፍን” አንተ ምኒልክ ወራሪ፤ገዳይ ነበር; አስተምሮህ። መለስ እና ምንሊክ “ተስፋፊዎች’ ‘ገዳዮች’ “ቅኝ ገዢዎች “ ነበሩ እያልክ የጻፍከው እንዴት ድሮ ረሳኸው? እስኪ ያንተው ርዕስ ልስጥህ እና አንባቢዎችህ ቢገነዘቡህ ፤ አንዲህ ትላልህ ፤ረስተኸው እንዳተሆን ላስታውሰህ፦

Emperor Menelik and Meles Zenawi both “killed Ethiopia” (Ephrem Madebo )

Emperor Menelik and Meles Zenawi both used language to unify Ethiopia, they both killed people in the process and they both failed to create a unified country. Menelik made a strategic mistake, a mistake that emanates from false sense of superiority and arrogance. Meles, the most educated of all Ethiopian leaders, repeated the same mistake that he vowed to correct. Menelik and Meles have different goals but the same ending.” Emperor Menelik and Meles Zenawi both “killed Ethiopia” say Ginbot 7 Ephrem Madebo


ምኒልክ ትምክሕተኛ፤ ወራሪ ፤ኢትዮጵያን የገደለ፤ሕዝብ የጨፈጨፈ ፤ገዳይ እያልክ ከመለስ ዜናዊው የትግሬ/ኤርትራ ባንዳ ጋር አነጻጽረህ ዘልፈሃቸዋል። ቴዲ “ምኒልክ/ኢትዮጵያ’ ብሎ በጥቁር ሰው አለኝታ ሲያስታውሳቸውና ሲዘፍንላቸው ፤ አንተ ግን የቴዲን ተቃራኒ ነው ለሕዝብ እና ለትውልድ ትትህ ለማለፍ የከጀልከው። ወደ መድረክ ይህንን ይዘህ ስትለፈልፍ፧ ትንሽ ሓፍረት አይሰማህም፤ ወይ ዘመን!ያተላዮች ዘመን! ደግሞ አታፍርም

(5)- {“ኢትዮጵያዊነት” ጥብቅና አጥቶ ሲወንጀል} ብለሃል።

ወይ አለማፈር፡ ኢትዮጵያዊነት ጥብቅና አጥቶ በነ ኤፍሬም ማዴቦ ሲወነጀል፤ ኢትዮጵያን የመሰረቱ እና ኢትዮፕያዊነትን አስከብረው የጥቁር ሕዘብ ኩራት የነበሩትን እነ እምዬ ምኒልክን ኢትዮጵያን ገደሉ እያልክ ከወያኔ መሪዎች እኩል “ትምክህተኛ’ ጉረኛ እያልክ ስትዘልፍ ጥብቅና ያሳጣሃትን ኢትዮጵያዊነትን ነው ቴዲ ጥብቅና የቆመለት። አንተ ያረከስከው ማለት ነው። አስኪ አንተ እንደ ፕሮተስታንት ፓስተርነትህ የምትሰብክበትን መጽሐፍ ቅዱስ አንዴ ገንጠል አድርግ እና “ኢትዮጵያዊንትን ጥብቅን ለቆሙት እነ ምኒልክን መዝለፍህ ይቅርታ ጠይቅ? Emperor Menelik and Meles Zenawi both “killed Ethiopia” (Ephrem Madebo ) ኤፍሬም ይህ ያንተ ባንዳዊ ወንጀል አይደለም? ቴዲ አፍሮ ይህንን አልሰበከም እኮ። ተቃራኒው ነው ያስተማረህ (የሚማር ጭንቅላት ካለህ)


አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) (Ethiopian Semay) getachre@aol.com