Posted on June 4, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 ቃል አቀባይ የነበረው ታጋይ ዘመነ ካሴ በገዛ ፈቃዱ ሲያገለግለው የነበረውን ድርጅት እንደለቀቀ ፕሮፌሰር አርበኛ ብርሃኑ ነጋ ይፋ አደረጉ። የጤና ችግር እንዳጋጠመው አረጋገጠው ለህክምና ከአስመራ ወደ ሌላ በስም ያለጠቀሱት አገር መሄዱንም አመልክተዋል። እሳቸው የተናገሩትን ተከትሎ በማህበራዊ ገጾች ትችት እየተሰነዘረ ነው። ረዘም ላለ ጊዜ ድምጹ በመጥፋት ከተለያዩ ወገኖች የተለያዩ ዜናዎች ዘመነን አስመልክቶ ሲሰራጩ ቆይተዋል። ” ዘመነ ሞቷል” ከሚለው ጀምሮ በየዕለቱ የሚወጡትን ዜናዎችን ተከትሎ አርበኞች ግንቦት 7 በማስተባበል ወይም በመቀበል ያለው ነገር ባለመኖሩ ወሬው ግራ መጋባትን ፈጥሮ እንደ ከረመ የሚታወቅ ነው። ለዚህም ይመስላል በቶሮንቶ ከኢትዮጵያዊያን ጋር ሕዝባዊ ስብሰባ ያካሄዱት የድርጅቱ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ታጋይ ዘመነን አስመልክቶ ” እውነት ነው” ያሉትን ይፋ አድርገዋል። እሳቸው እንዳሉት ዘመነ፣ የመኪና አደጋ ደርሶበት ነበር። ኳስ ሲጫወት ተደጋጋሚ ስብራት ደርሶበት ነበር። በመኪና አደጋና በኳስ ጨዋታ ተደጋጋሚ ስብራት አስመራ በህክምና ቢረዳም ሊድን አልቻለም። ዘሃበሻ እሳቸውን ጠቀሶ እንዳለው፣ የአስመራው ህክምና በቂ ባለመሆኑ ታጋይ ዘመነ ወደ ውጭ አገር ሄዶ መታከም እንዲችል አርበኞች ግንቦት 7 እንዲያሰናብተው ጠይቆ በድርጅቱ ህገ ደንብ መሰረት ተፈቅዶለታል።

ኢካድኤፍ ከፌስ ቡክ ምንጭ ተገኘ ባለው ዜና እንዳለው ታጋይ ዘመኔ አውሮፓ ግብቷል። ፐሮፌሰር ብርሃኑ በበኩላቸው ታጋይ ዘመነ ያለበትን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። ይሁን እንጂ ከአስመራ መንግስት ጋር በመነጋገር ፓስፖርት ተዘጋጅቶለት እና አርበኞች ግንቦት 7 ሙሉውን ወጪ ሸፍኖ ለህክምና ወደፈለገበት አገር በአስመራ ልዩ ኮማንዶ ታጅቦ እንደሄደ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ሲድን ድርጅቱን መልሶ ስለመቀላቀሉ ግን የተባለ ነገር የለም።

ታጋይ ዘመነ ካሴ ተገሏል፣ ቆስሏል፣ ጉዳት ደርሶበታል፣ ታፍኖ መንግስት እጅ ወድቋል የሚሉ የተለያዩ መረጃዎችን በተለያዩ ማህበራዊ ገጾችና የመገናኛ ዘዴዎች ሲያሰራጩ የነበሩትን ” የኪይቦርድ ታጋዮች” ሲል የሚጠራዉ የኢካድኤኤፍ የፌስ ቡክ ዜና ትግል መስዋዕትነትን እንዳለበት ያመለክታል። አርበኞች ግንቦት 7 አስገድሎታል በሚል የሃሰት ዜና ሲሰራጭ መቆየቱን በአሉታዊ መልኩ ገልጾታል።
..እነዚህ የኪቦርድ ታጋዮች፣ ህይወቱን ለመስጠት በርሃ የገባ ታጋይን ካላሳያችሁን እያሉ ያዙን ልቀቁን ሲሉ መስማት እንጭጭነታቸውን ወይም አለማወቃቸውን በአደባባይ ከማስመስከር ውጭ የትም እንደማይደርሱ መገንዘብ እንኳ የተሳናቸው ናቸው። የዘመነ ፋይል እዚህ ላይ ሲዘጋ ነገ ደግሞ በረሃ ያሉትን ሌሎች ጓዶቻችንን ምክንያት እየፈጠሩ አዲስ የመጨቃጨቂያ አጀንዳ እንደሚከፍቱ ምንም ጥርጥር የለም። በዘመነ ላይ በተወራው ብዙ ማለት ይችላል” ሲል ስጋቱ የግልሳል። አያየዞም ” ዘመነ ተገድሏል፣ ታስሯል እያሉ ሲያደነቁሩን የነበሩ አሉባልተኞች አውሮፖ መግባቱን ሲሰሙ ምን አርዕስት ይከፍቱ ይሆን?” ሲል ኢካድ ኤፍ “ፌስቡክ ገጽ የተወሰደያለው ዜና አስተያየቱን አስነብቧል።

በሌላ ወገን በ አማራ ስም ተደራጅተናል የሚሉ ወገኖች ዜናው እንዳልተዋጠላቸው በመግለጽ፣ ዘመነን ለማሳከም ገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻ ላይ መሆናቸውን እየገለጹ ነው። የእርዳታ ማሰባሰቢያ አስፈንጣሪ አዘጋጀተው ድጋፍ እየጠየቁ ይገኛሉ። የዘመነን መታመም እየገለጹ የሰነበቱ ወገኖች መካከል አንዳንዶቹ ዘመነ የአማራ እንቀሰቃሴ አካል መሆኑንንም እየገለጹ ሲሆን የየትኛው አማራ ድርጅት እንደሆነ ግን አይጠቁሙም።

አቶ አበበ ቦጋለ የስጡትን ይመልከቱ

https://www.youtube.com/watch?v=zzInIQNqnlc