June 4, 2017

(ዘ-ሐበሻ) በኢንቨስትመንት ጉዳይ ለመወያየት በ እስራኤል ኢየሩሳሌም ከተማ ያቀኑት የሕወሓት መንግስት ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ እዚያው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ደረሰባቸው::

ኃይለማርያም ጥቂት የሕወሓት ደጋፊዎችን እና በሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ሥር ያሉ ቄሶችን ሰብስበው እንደነበር የጠቀሱት ምንጮች ስብሰባው ላይ የታሰበውን ያህል ሰው ማግኘት እንዳልቻሉ ታውቋል:: በኢየሩሳሌም ያሉ ቄሶች ግልጽ ባልሆነ ግዳጅ ወደ ስብሰባው እንዲሄዱ ት ዕዛዝ እንደወረደላቸው አለበለዚያ ወደፊት የሚያስቡትን ሹመት እንደማያገኙ በደረሰባቸው ማስፈራሪያ መሰረት ወደ 8 የሚጠጉት ሲሄዱ ሌሎቹ ግን አንሄድም ማለታቸው ታውቋል:: ወደ ስብሰባው የሄዱትም የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ቄሶች ብቻ ናቸውም ተብሏል::

የሕወሓት መንግስት ከ20 ሺህ ዶላር በላይ በማውጣት በኢየሩሳሌም ያዘጋጀው ይኸው ስብሰባ በኪሳራ መጠናቀቁን የሚገልጹት ምንጮች ኢትዮጵያውያን ውስጥ እንዳይገቡ ፖሊሶችን በመቅጠር ቢያግድም ከውጭ ሆነው ብርቱ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ውለዋል:: የተቃውሞው ተንቀሳቃሽ ምስል ደርሶናል ይመልከቱት::