አርበኛ ዘመነ ካሤ ይናገራል፤ – ሙሉቀን ተስፋው

ምንም እንኳ አሳማኝ ባይሆንም አንዳንድ ሰዎች አውቀው ሆን ብለው ሌሎች ደግሞ ሳያውቁ በየዋኅነት ለዘመነ የሚያስፈልገውን እርዳታ ለማድረግ የምናደርገውን እንቅስቃሴ አጓተውብናል፡፡

ለምሳሌ ያክል ለጎፈንድ ሚ ድርጅት የፈጠራ ኢሜሎችን በመላክ ሁለት ጊዜ ያክል የገንዘብ ማሰበባሰብ ዘመቻው እንዲቋረጥ ያደረጉ አካላት መኖራቸውን ስናውቅ በዕውነት ያሳፍራል፡፡ በዚህ ምክንያት ዘመነ አጠር ያለ መልዕክት እንዲያስተላልፍ ግድ ብሏል፡፡ እነሆም ዘመነ ያለእርሱ እውቅና ምንም ነገር እየተደረገ እንዳልሆነ አስረግጦ ይናገራል፡፡
በተረፈ ግን ኤርትራ በነበረ ጊዜ ገንዘብ የላኩለትን ሰዎች በስም እየጠቀሰ አመስግኗል፡፡ ወደፈፊት በሚኖረው ደግሞ የጤንነቱን ሁኔታ ካስተካከለ በኋላ በዝርዝር ቃለ መጠይቅ ይሰጣል፡፡
በመጨረሻ ለዘመነ የተከፈተው ጎፈንድ ሚ ከላይ በተጠቀሰው ምክንያት ለጊዜው የቆመ ሲሆን ከድርጅቱ ጋር እየተነጋገርን ስለሆነ መልስ እንዳገኘን ወዲያውኑ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ከአክብሮት ጋር