እንዴት ሰነበታቹህ? ወያኔ የኢንተርኔት (የዐውደ መረብ) አገለግሎቱን ጥርቅም አድርጎ ዘግቶት ተለያይተን ሰነበትን፡፡

የአሜሪካ ድምፅን፣ የጀርመን ድምፅን የአማርኛ የአገልግሎት ክፍሎች ጨምሮ የተለያዩ ታላላቅ ዓለማቀፍ የብዙኃን መገናኛዎች በብሔራዊ የ10ኛና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ብሔራዊና የመግቢያ ፈተናዎች ምክንያት የኢንተርኔት (የዐውደ መረብ) አገልግሎት ካለፈው ረቡዕ 23,09,2009.. ጀምሮ እንደተቋረጠ በተደጋጋሚ የተሳሳተ ዘገባ ሲዘግቡ ሰንብተዋል፡፡ በተጨባጭ ግን መደበኛው የኢንተርኔት (የዐውደ መረብ) አገልግሎት ከተቋረጠ ዓመት ሆኖታል፡፡

የሞባይል ኢንተርኔት (የተንቀሳቃሽ መናግር ዐውደ መረብ) አገለግሎት እና የኢንተርኔት ካፌ (የዐውደ መረብ አገለግሎት መስጫ ሱቅ) የኢንተርኔት (የዐውደ መረብ) አገልግሎት የተቋረጠው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመታወጁ ከወራት በፊት ጀምሮ ነው፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ ስምንት ወራት ሆኖታል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመታወጁ ከወራት በፊት ግን በተነሳውና እየተጋጋለ በመጣው ሕዝባዊ የእንቢተኝነት ዐመፅ የተነሣ አስቀድሞ የነበረው የመደበኛው የሞባይል ኢንተርኔት (የተንቀሳቃሽ መናግር ዐውደ መረብ) አገልግሎት እና የኢንተርኔት ካፌዎች (የዐውደ መረብ አገለግሎት መስጫ ሱቆች) የኢንተርኔት (የዐውደ መረብ) አገልግሎት ከወራት በፊት እንዲቋረጥ ተደርጎ ቆይቷል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ባንኮች (ቤተ ንዋዮች) ፣ ሆቴሎች (ቤተ እንግዳዎች) ፣ ኤምባሲዎች (የመንግሥታት የእንደራሴ መሥሪያ ቤቶች) እና የተለያዩ የመያድ (NGO) ድርጅቶች በስተቀር ከዛሬ ዓመት ጀምሮ የሞባይል ኢንተርኔት (የተንቀሳቃሽ መናግር ዐውደ መረብ) አገለግሎት እና የኢንተርኔት ካፌዎች (የዐውደ መረብ አገለግሎት መስጫ ሱቆች) የኢንተርኔት (የዐውደ መረብ) አገልግሎት እየተጠቀምን ወይም እየተገለገልን ያለነው እንደ ፒሲ ፎን እና ኦፔራ ሚኒ የመሳሰሉ ወያኔ ብሎክ ያደረገውን (የገደበውን) የኢንተርኔት (የዐውደ መረብ) አገልግሎትን ሰብረው መግባት የሚችሉ አፖችን (መተግበሪያዎችን) እና ማስፈንጠሪያዎችን በመጠቀም ነው እየተጠቀምን ያለነው፡፡

እነኝህ መተግበሪያዎችም የዐውደ መረብ አገልግሎቱን የሚሰጡት ኢመደበኛ በሆነ መንገድ እንደመሆኑ መጠን መደበኛው አገልግሎት ይጠይቅ ከነበረው የአገልግሎት ክፍያ ከእጥፍ በላይ ክፍያ እየከፈልን ነው አማራጭ ስለሌለን እየተጠቀም ያለነው፡፡ የኢትዮጵያ የዐውደ መረብ አገልግሎት ክፍያ በራሱ በጣም ውድ ከሚባሉት ጥቂት ሀገሮች አንዱ ሆኖ እያለ በዚህ ላይ ደግሞ አገልግሎቱን ስለተከለከልን ለማግኘት ስንል ውድ ዋጋ ከፍለን በሦስተኛ ወገን በኩል ለመጠቀም በመገደዳችን ለአላስፈላጊ ወጪ ዳርጎን በዚህ የኑሮ ውድነት ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሮብን በከፍተኛ ከደጃ ከአቅማችን በላይ እየተበዘበዝን እንገኛለን፡፡ ወያኔ ይሄንን የሚያደርግበት ዋነኛ ምክንያት ሕዝቡ ወጪ ተማሮ መረጃ ከማግኘት እንዲርቅ ለማድረግ ነው፡፡

ሁኔታው በፈጠረለት አጋጣሚም ኢቲዮ ቴሎኮም ቀድሞ ከመደበኛው የኢንተርኔት (የዐውደ መረብ) አገለግሎት ከደንበኞች የአገልግሎት ክፍያ ያገኝ ከነበረው ገቢ ይልቅ ደንበኞች አማራጭ ከማጣት የተነሣ ኢመደበኛ በሆነ መንገድ የተለያዩ ውድ የሆኑ መተግበሪያዎችን በመጠቀም የኢንተርኔት አገለግሎት በመጠቀማቸው የሚያገኘው ገቢ በላቀ ሆኖ ስላገኘው መደበኛ የሆነውን የኢንተርኔት አገለግሎት ለሞባይል ኢንተርኔት (ለተንቀሳቃሽ መናግር ዐውደ መረብ) አገለግሎት እና ለኢንተርኔት ካፌ (ለዐውደ መረብ አገለግሎት መስጫ ሱቅ) መደበኛ የኢንተርኔት (የዐውደ መረብ) መደበኛውን አገልግሎት ማቋረጡ የሚያሳስበው ሆኖ አልተገኘም፡፡ ድርጅቱ የዐውደ መረብ አገልግሎትን ባለማቅረብ ይከስር የነበረው ልክ እንደሰሞኑ ሙሉ ለሙሉ የዐውደ መረብ አገልግሎትን ጥርቅም አድርጎ የዘጋ ቢሆን ነበረ፡፡

ተጠቃሚው ግን መደበኛ ባልሆነ መንገድም ቢሆን በውድ ዋጋ መጠቀሙን ስላላቆመ የድርጅቱ ትርፍ ከወትሮው በተለየ መልኩ ጨመረለት እንጅ ከዓመት በላይ ተቋርጦ በቆየው መደበኛው የሞባይል ኢንተርኔት (የተንቀሳቃሽ መናግር ዐውደ መረብ) አገለግሎት እና የኢንተርኔት ካፌ (የዐውደ መረብ አገለግሎት መስጫ ሱቅ) የዐውደ መረብ አገልግሎት ኪሳራ አልደረሰበትም፡፡ ይሄንን በተመለከተ በብዙኃን መገናኛዎች እየሰማን ያለነው ዘገባ የተሳሳተ በመሆኑ ነው ይሄንን የምጠቅሰው፡፡ በዚህ በወያኔ ዘመኑን ያልዋጀ ደንቆሮ አንባገነናዊ እርምጃ የተነሣ በየመንደሩ ተስፋፍተው የነበሩት የኢንተርኔት ካፌዎች (የዐውደ መረብ አገልግሎት መስጫ ሱቆች) በኪሳራ ምክንያት ለመዘጋት ተገደው ደብዛቸው እየጠፋ ይገኛሉ፡፡ አልፎ አልፎ ነገ የተሻለ ሁኔታ ይፈጠር ይሆናል በሚል ተስፋ ኪሳራዎቻቸውን ተቋቁመው ሳይዘጉ የቀሩ ጥቂት ጥቂት ቢኖሩም ትናንትና እንደ አሸን ፈልተው የነበሩት የኢንተርኔት ካፌዎች (የዐውደ መረብ አገልግሎት መስጫ ሱቆች) በወያኔ ሸፍጠኛና አንባገነናዊ እርምጃ ዛሬ ላይ ታሪክ ሆነው ቀርተዋል፡፡

ሕዝቡም አማራጭ የብዙኃን መገናኛ ዘገባዎችንና መረጃዎችን የማግኘት ጥማቱን የማርካት ፍላጎቱን ለማርካት አልብላ አልጠጣ ብሎ እጅግ ውድ በሆነ አገልግሎት ለመበዝበዝ ተገዷል፡፡ ያለው እውነታ ይሄ ነው፡፡ ወያኔ ግን ጫካ የወለደው ወንበዴና ወሮበላ ነውና መንግሥታዊና ተቋማዊ ሥነሥርዓት (discipline) የማያውቅ፣ የሞራል (የቅስም) ስሜት የሌለው፣ ሕግ የማይገዛው በመሆኑ አስቀድሞ የነበረንን የመንግሥት ተቋማትን የመታመንንና የመታፈርን ግርማ ማንንም ሊያታልል የማይችል ሐሰተኛና ነውረኛ መግለጫዎችንና ቃላቶችን በመንግሥት ተቋማት ስም ምን ይሉኝ ሳይልና ቅንጣት ታክል እፍረት ሳይሰማው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ በመስጠት የነበረንን የመንግሥታዊ ተቋማትን የመታመንን እና የመታፈርን ታላቅ እሴት ደብዛውን አጥፍቶ የኢትዮጵያን ሕዝብ በወንበዴ ከወንበዴም እጅግ በጣም ነውረኛና ባለጌና ወራዳ አገዛዝ ሥር እንደወደቀ እንዲያምንና በዚህም የተነሣ በከፍተኛ የቀቢጸ ተስፋ ስሜት ውስጥ እንዲዋጥ አድርጎታል፡፡

ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ አንዲት ምሳሌ መጥቀስ ቢያስፈልግ የ6 ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንደተጠናቀቀ ኢትዮ ቴሌኮም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው መደበኛው የሞባይል ኢንተርኔት (የተንቀሳቃሽ መናግር ዐውደ መረብ) አገለግሎት እና የኢንተርኔት ካፌ (የዐውደ መረብ አገለግሎት መስጫ ሱቅ) የኢንተርኔት (የዐውደ መረብ) አገልግሎት እንደሚጀምር፣ መጀመር ብቻም ሳይሆን አዳዲስ ደንበኞች እነኝህ አገልግሎቶችን በአዲስ ደንበኝነት በሚቀላቀሉበት ጊዜ የሚሰጠውን የቦነስ (የምርቃት) የአገልግሎት ሰዓት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት የመደበኛው የኢንተርኔት አገለግሎት ሲቋረጥ ተጠቅመው ያልጨረሱትን በቦነስ (በምርቃት) የተሰጣቸውን የኢንተርኔት አገልግሎት ሰዓት ጭምር መጠቀም እንደሚችሉ መግለጫ ከተሰጠ በኋላ እንኳንና የቦነስ (የምርቃት) አገልግሎቱ ሊገኝ ይቅርና ከነጭርሱኑ ተቋርጦ የቆየውን መደበኛውን የዐውደ መረብ አገልግሎት ሳናገኝ ቀርተናል፡፡

እነሱ ግን እፍረት የሚባል ነገር ቅንጣት ያልፈጠረባቸው ወንበዴዎች በመሆናቸው ለሌላ አካል እንኳ በሆነ ለእኛው ለራሳችን ከዓመት በፊት የነበረውን መደበኛውን የሞባይል ኢንተርኔት (የተንቀሳቃሽ መናግር ዐውደ መረብ) አገልግሎትን እና የኢንተርኔት ካፌ (የዐውደ መረብ አገለግሎት መስጫ ሱቅ) የኢንተርኔት (የዐውደ መረብ) አገልግሎትን እንደለቀቁ ያለአንዳች መሸማቀቅ በየብዙኃን መገናኛው ይለፍፋሉ፡፡ አሁን ታዲያ እነኝህን በሽተኞችና ለከተቢስ ነውረኞች የኢትዮጵያ ሕዝብ በምንም ነገር ላይ ፈጽሞ የማያምናቸው ሆኖ መገኘቱ እነሱን እራሳቸውን ይገርማቸው ይሆን? እነሱ እኮ አያፍሩም ይሄኔ እኮ በሕዝብ ባለመታመናቸው ይገርማቸውና ይናደዱም ይሆናል! ተጠቃሚውም መደበኛውን የዐውደ መረብ አገልግሎት ፈጽሞ መልሶ ማግኘት ባለመቻሉ ከተቋረጠ ከዓመት በፊት ጀምሮ ከላይ የጠቀስኳቸውን መተግበሪያዎች በመጠቀም የዐውደ መረብ አገልግሎትን ስንጠቀም የቆየን ቢሆንም ወያኔ በ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ብሔራዊና የመግቢያ ፈተናዎችን ምክንያት አድርጎ ሙሉ ለሙሉ የዐውደ መረብ አገልግሎትን በዘጋው ጊዜ ግን እነዚያን ኢመደበኛ ውድ መተግበሪያዎችን ተጠቅመንም ቢሆን የዐውደ መረብ አገልግሎትን ማግኘት ወይም መጠቀም ሳንችል ሰንብተናል፡፡ የተዘጋው ሙሉ ለሙሉ በመሆኑ፡፡ በዚህ ሁኔታ ከሳምንት በላይ ከቆየን በኋላ የቀድሞው መደበኛው ሳይሆን ውድ የስርቆት መተግበሪያዎችን በመጠቀም የዐውደ መረብ አገልግሎትን መጠቀም የምንችልበት ሁኔታ በመመለሱ መደበኛ በሆነ መንገድ ሳይሆን ኢመደበኛ በሆነ መንገድ የዐውደ መረብ አገልግሎት የምናገኝበት ሁኔታ በመመለሱ ከተቀረው የዓለማችን ክፍል ጋር መልሰን ለመገናኘት ችለናል፡፡

እንግዲህ በወሮበላና ወንበዴ ኢዲሞክራሲያዊ (ኢመስፍነ ሕዝባዊ) አንባገነን አገዛዝ የመገዛት ትርፉ ነጻ መረጃን ከማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛዎች የማግኘት መብትን በማግኘት ረገድ ያለው ሁኔታ ባጭሩ ይሄንን ይመስላል፡፡ ይሄንን ሁኔታ ማንም ኢትዮጵያዊ ይወደዋል ብየ አልገምትም፡፡ ይሄ ከሆነ ዘንዳ በትግል እንጅ በምኞት የሚለወጥ አንዳችም ነገር የለምና ይሄንንና ሌሎች በርካታ የወያኔ አረመኔያዊ ኢፍትሐዊና ኢዲሞክራሲያዊ እርምጃዎቹን ዓለም የተለወጠበትን 21ኛውን መቶ ክ/ዘ ፈጽሞ የመይመጥነውን ደንቆሮውን፣ ኋላቀሩን የወያኔን አገዛዝ ገርስሰን በመቅበር ታሪክ አድርገን ለማስቀረትና
ነጻ ለመውጣት ሁላችንም እንረባረብ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com