June 11, 2017

 አዳም አጸብ ከድቀቱ በፊት በበጎ ህሊና ይኖር ነበር ሲባል መጥፎ ነገር ለማሰብ አይችልም ማለት ነው።ለምሳሌ መግደል፣ መዋሸት መመኘት ክህደት ኑፋቄ የተባሉ ስጋዊ ጠባዮች በአእምሮው መዝገብ ውስጥ አልተጻፉምና አያውቃቸውም። ለምሳሌ አዳም ምንም ቅሉ የሰላሳ አመት ጎልማሳ ሆኖ ቢፈጠረም ልቡናው እንደ ህጻናት ልቦና ነበረና ሃፍረተ ስጋውን አላየውም። ስለሆነም ልብስ አላስፈለገውም ነበር። እጸ በለስ በበላ ግዜ ግን ክፉና ደግ ለይታ የምታሳውቀውን የእውቀት ፍሬ በላና የሚኖርበትን አለም መጥፈፎውን ጎን ያይ ዘንድ አይኑ ተገለጠ። አንድ ግዜ ከጸጋ በታች ወድቋልና በመሆንና ባለመሆን በማድረግና ባለማድረግ ክፉ ምኞት ተዋጠ።ሃፍረተ ስጋውን አይቶ ልብስ ፍለጋ የሮጠው ያን ግዜ ነው። ሰላሙ ተወስዶበት የምኞት ባሪያ ሆኗልና በምኞት የሚፈተን አይምሮ ይዞ ደግሞ በገነት መኖር አይቻልም፤ ስለዚህ የቁርበት ልብስ አልብሶ ውጣ፣ እስከ ዕለተ ሚጠት ድረስ በዛው ቆይ ብሎታል።አዳም በገዛ ኑፋቄው ከገዛት ክፉ ምኞት ጋርም ወደ ተረገመችው መሬት ወርዷል።

ኑሮ በገነት ምን ይመስላል የሚለውን እንዲህ ማየት የሚቻል ይመስለኛል

በገነት ውስጥ መኖር ማለት ፍላጎት ምሉእ የሆነበት አለም ውስጥ መኖር ማለት ነው። ከምኞት ውጭ መኖር ማለት ነው። ይህም ማለት ሰው የሆነ ነገር ማግኘት ሲፈልግ አግኝቶታል። የሆነ ቦታ መድረስ ሲፈልግ ደርሷል። በጥቅሉ በዚህ አለም ላይ ያለው የታይም እና ስፔስ ሊሚቴሽን በርሱ ላይ ስልጣን የላቸውም ማለት አንድን ነገር በመመኘት ቀጥሎም በመፈለግና ፈልጎ በማግኘት መካከል የሰከንድ ክፍተት የለም፤እንዲሁም አንድ ቦታ መሄድ በመፈለግና ያሰበው ቦታ በመድረስ መካከል ምንም አይነት ዲስታንስ ሊሚቴሽን ወይንም የቦታ ውሱንነት የለም ማለት ነው ማለት ነው።
ባጠቃላይ ምኞት ሲሸነፍ ፍላጎት ምሉዕ ሆኗል ማለት ሲሆን የፍጹም ሰላም መገኛዋ ነጥብም እርሷ ናት። አዳም ሰላሙን አስረክቦ ስደት የወጣው ከዚህ አይነት አለም ነው።

እንግዲህ አዳም ወደ ተረገመችው መሬት ሲመጣ ይዞ የመጣው ደግሞ የሞት እዳ ብቻ ቢሆን እዳው ገብስ ነበር። ነገር ግን የነበረውን ፍጹም ሰላም ተገፎ ክፉ ምኞት ተጭኖበት መውረዱ ነው ሰላማችንን ወስዶ ጣዕራችንን ያበዛው።

በምኞት ውስጥ መሬት ላይ መኖር ምን ማለት ምን ማለት ነው ፤

ከዘፍጥረት (ቢግ ባንግ) ጀምሮ እስከ ምጻት( ዘቢግ ክራንች) ድረስ ኢንፋይናትሊ የተለጠጠና አሁንም ድረስ በየሰከንዱ ያለማቋረጥ ከብርሃን ፍጥነት በላይ በሆነ ፍጥነት እየተለጠጠ በሚሄድ ዩኒቨርስ(ህዋ) ውስጥ በዚያው ልክ ያልተገደበ ምኞት የተጫነብን ነገር ግን ደግሞ በጣም ውሱን የሆነ አቅም ብቻ ገንዘብ ያደረገ ስጋ ለባሽ ይህን ፍላጎት እንዴት ማስታረቅ እንደሚፍል አለማወቁ ነው ትልቁ ሰላሙን የሚነሳው ነገር። ህይወታችንን ሙሉ እርካታ በተለየው የማያቋርጥ ሲቃ ውስጥ እንድንኖር የሚያደርገንም ይዅው ነው። ነገር ግን በምንፈልገውና ፈልገን በምናሳካው መካከል ያለው ልዩነት በጣም ትልቅ በመሆኑ የተነሳ በሁለቱ መሃል ያለችውን ልዩነት ማስታረቅ (ባላንስ) ማደርግ የቻለ፤ በሌላ አነጋገር አንጻራዊ በሆነ መልኩ ምኞቱን ለመገደብ አቅም ያደረገ ሰው ማለት የተሻለ ሰላም ያለው ሰው እርሱ ነው ።

እንግዲህ አንድ ሰው ከላይ ወደ ገለጽነው የሰላም አገር ለማዝገም አንዱ አቋራጭ መንገድ (ዲስፕለስመንት) የህይወት ዘመን ስኬቱ አንጻራዊ የሆነ ሰላም ያለበት እንዲሆን ታሳቢ ያደረገ ከሆነ ነገሩ መለካት ያለበት በሚያከማቸው ሰፊ የሃብት ክምችት ሳይሆን በዋናነት በሚከተለው የህይወት ሲምፕሊሲቲ ነው ማለት ነው።ለዚህም ቀላሉ ምሳሌ ሱስ ካለበት ሰው ይልቅ ሱስ የሌለበት ሰው ቀላልና የተሻለ ሰላም ያለው ህይወት እንደሚገፋው ማለት ነው።

ሌላው ሰላማችንን ከሚያናጋው የአይምሮ ጠንቅ ውስጥ በዋናነት ለራሳችን በምንሰጠው ግምት እና ሰዎች ስለኛ ያላቸው ሚዛን አለመግጠም ነው። ለምሳሌ እየሱስ ክርስቶስ በስጋ ማርያም በተገለጠ አንድ ጌዝ እራሱን ባዶ አደረገ ስንል የዚህ አለም ትናንሽ የሆኑ ነገሮችን መምረጡን ለማሳየት ነው፤ በበረት ከመወለድ ጀምሮ፣ ከደሃ ወገን መወለዱ፣ በዚህች ምድር ላይ ዛኒጋባ እንኩዋን ሳይኖረው በተናቀ ሞት መሞቱና የተቀበረበት መቃብር እንኩዋን የሌላ ሰው መሆኑን ሁሉ ለማለት ነው።። ስለሆነም እራሱን አንድ ግዜ በዚህ ደረጃ ዝቅ አድርጓልና እርሱን በሰደቡትም፣ በተፉበትም፣ በተሳለቁበትም ግዜ ሁሌ በለበሰው ስጋም ቢሆን ክብሬ ተነካ ብሎ ሲናደድ የታየበት አንድም አጋጣሚ የለም።ሁሉንም ነገር በጽትታ ውስጥ ያልፈው ነበር። ይኽ እንግዲህ ስለ ቤተክርስቲያኑ ቅናት የታየበትን ንዴት ሳይጨምር ማለት ነው።የክርስቶስ መዋዕለ ስጋዌ የሚያሳየው ማንም ቢሆን አንድ ግዜ ከሰዎች ከበሬታን ሳይሻ እንዲሁ በጥትና መኖርን ገንዘብ ቢያደርርግ ሌላኛውን ወደ ሰላም አገር መድረሻውን ጫፍ አግኝቶታል ማለት ነው። እራስን ከማንም ሳያወዳድሩ በት ሁት ሰብዕና የመኖር ዘይቤ ከህይወት ሲምፕሊሲቲ ጋር የሚገናኙበት ነጥብ ዘኳዋተም አንደርስታንዲንግ ኦፍ ፒስ ማለት እርሱ ይመስለኛል።