ከያኔ (Artist) ማለት ብዙዎቻችን በስሕተት ኪነጥበብ በምንለው ዘርፍ እና በሥነ ጥበብ (Fine art) ዘርፍ የተሰማራ ባለሙያ ወይም ጥበበኛ ማለት ነው፡፡ ቃሉ የአማርኛ ቃል ሲሆን ኪን (ጥበብ) ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ቃል ነው፡፡ ከያኔ የሚለው ቃል በቁሙ የግእዝ ቃል አይደለም፡፡ የዚህ ቃል የግእዝ አቻ ቃል ኬንያ የሚለው ቃል ነው፡፡ ከያኔ የሚለውን ቃል አንዳንዶች በዘርፉ ያሉ ባለሞያዎች ከያኒ ብለው ሲጽፉትና ሲናገሩት አያለሁ፡፡ ስሕተት ነው መታረም አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ሸማኔ እንላለን እንጅ ሸማኒ አንልም፣ ነጋዴ እንላለን እንጅ ነጋዲ አንልም፣ ገበሬ እንላለን እንጅ ገበሪ አንልም እንዲህ እያልን በርካታ የአማርኛ የሞያ ስሞችን ምሳሌ መጥቀስ እንችላለን፡፡

በስሕተት ኪነ ጥበብ የምንለውም ሆነ ሥነጥበብ የምንለው ሁለቱም ዘርፍ ባጠቃላይ ሥነኪን ይባላል፡፡ በመሆኑም ከያኔ ስንል አቀንቃኙን ወይም ዘፋኙን፣ ተወዛዋዡን ወይም ዳንኪረኛውን፣ መሣሪያ ተጫዋቹን፣ ገጣሚውን፣ አቀናባሪውን፣ የወግ አዋቂውን ወይም ወገኛውን (ኮሜዲያኑን) ፣ ተዋኙን፣ ደራሲውን፣ አዘጋጁን፣ ሠዓሊውን፣ ቀራጺውን ባጠቃላይ በሁሉም የጥበብ ወይም የኪነት ዘርፍ ላይ ያለውን ባለሞያ ማለታችን ነው፡፡

ማንኛውም ሞያ የራሱ ተግባርና ኃላፊነት ወይም የተጣለበት አደራ (Mandate) ዓላማና ግብ አለው፡፡ የሥነኪን ግን ሥነኪን የማትገባበትና የማትዳስሰው፣ የማታበረታው፣ የማታጎለብተው፣ የማትደግፈው የሞያ ዓይነት የለምና የአንድን ማኅበረሰብ ወይም ሕዝብ ሁለንተናዊ ጤና፣ ሰላም፣ እድገት፣ ብልጽግና፣ ደኅንነትና ህልውናን ለማሳደግ፣ ለመጠበቅና ለመንከባከብ የተጣለባት ኃላፊነት ዓላማና ግብ ከሌላው ሞያ ሁሉ የከበደ ነው፡፡

ምንጊዜም የትም ቢሆን ሥነኪን የሕዝብ ከሕዝብ ለሕዝብ ነች፡፡ ይህም ማለት ሥነኪን ሁልጊዜ የሕዝብ መብትና ጥቅም፣ የእውነት ወይም የሐቅ ተሟጋችና ጠበቃ ነች ማለት ነው፡፡ የተፈጠረችበት ዓላማና ግብ ሕዝብን ማገልገል ለእውነት መሟገት ብቻ ነው፡፡ ይሄ ሲባል ግን የሕዝብ ጠላት የሆኑት አንባገነንና አረመኔ ገዥዎች እጇን እየጠመዘዙ አስገድደው አይጠቀሙባትም ማለት አይደለም፡፡ አንባገነን ገዥዎች ከሀድያንና በሥነኪን ላይ የመነፈቁ ከያኔያንን ይዘው ለራሳቸው ፀረ ሕዝብ የጥፋት ዓላማና ተግባር እጇን ጠምዝዘው ሲጠቀሙባት ቆይተዋል እየተጠቀሙባትም ይገኛሉ፡፡ የዛኑ ያህል ደግሞ ዓለማችን በርካታ ብርቅየ ከያኔያን ለዚህ ሕዝባዊ አገለግሎትና ለእውነት ታምነው በማገልገል የሕዝብና የእውነት ጠላቶችን በጽናት ሲታገሉ ከባድና የሕይዎት ዋጋ የከፈሉባት ምድርም ነች፡፡ ከያኔያን ከያኔ ወይም የጥበብ ሰው ነኝ!” ለማለት ለዚህ ሕዝባዊ አገልግሎትና ለእውነት የታመኑና የጸኑም መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

የሕዝብ መበደልና ብሶት የማይሰማው፣ የማይገደው፣ የማያሳስበውና የሕዝብን ፈተናዎች ለማስወገድ የሚበጅ መፍትሔ ለማመንጨት የማይጥር ሰው በምንም ዓይነት ተአምር ቢሆን የበቃና የነቃ ከያኔ (Artist) ሊባል አይችልም፡፡ ይሄንን ሰብእና (ስብእና አይባልም ስሕተት ነው) ሳይላበስ ከያኔ ነኝ የሚል ካለ አስመሳይ ወይም አታላይ አጭበርባሪ ነጋዴ እንጅ በፍጹም ከያኔ አይደለም፡፡ ከያኔያን ስስ ቆዳ ነው ያላቸው!” የሚባለውም ለዚሁ ነው፡፡ በሕዝብ ላይ የሚደርስ ጉዳትና በደል ሁሉ ከማንም ቀድሞ ክፉኛ የሚሰማቸውና እረፍት የሚነሳቸው እነሱኑ ስለሆነና የሚከፍሉት ውድ ዋጋ ወይም መሥዋዕትነት ሳያሳስባቸው ሥነኪንን በመጠቀም የሕዝቡን ብሶት ስለሚተነፍሱ፣ ችግሩ ሊቀረፍ የሚችልበትን መላና ምክርም ለሕዝብ ስለሚጠቁሙ ነው፡፡

እርግጥ ሁሉም ሰው አንድ ዓይነት ወይም እኩል የብስለት ደረጃ፣ የማሰብ አቅም፣ የማገናዘብ ችሎታ፣ የሀገር ፍቅርና የተቆርቋሪነት ስሜት አለው ማለት አይቻልም ሊሆንም አይችልም፡፡ እነኝህ እሴቶች ቢጠበሱ የማይሸቷቸው ያለሆዳቸው ምንም ሌላ የማይታያቸው ግለሰቦች ጥቂት ቢሆኑም በሥነኪናችን ዘርፍም አሉ፡፡

እነ ሰሎሞን ተካልኝ፣ እነ ነዋይ ደበበ፣ እነ ፍቅረአዲስ ነቅዓጥበብ፣ እነ አስቴር አወቀ (ለወያኔ ያላትን ቅርበት በሚያሳዩ ተግባሮቿ በተጨማሪ ወያኔ እንዳይነካ ካላት የቅጥረኝነት ፍላጎቷ የተነሣ ከዓመታት በፊት ከሸገር የነጋሪተወግ ጣቢያ ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ ላይ ዘፋኝ በፖለቲካ ጉዳይ ላይ መግባት የለበትም! ብላ መናገሯ ይታወሳል) ፣ እነ ኩኩ ሰብስቤ፣ እነ ሠራዊት ፍቅሬ፣ እነ ሙሉዓለም ታደሰ፣ እነ ሸዋአፈራው ደሳለኝ እና ሌሎች አሁን ያልታወሱኝ ግለሰቦች መስሚያችን ጥጥ ነው!” ብለው ጆሯቸውን ደፍነው ለሕዝብ ጀርባቸውን ሰጥተው ከሕዝብና ከሀገር ጥቅም በተፃራሪ በ21ኛው መቶ ክ/ዘ የዘር ማጽዳትና ማጥፋት ወንጀልን የዚህች ሀገር የጀርባ አጥንት በሆነ ሕዝብ ላይ (በአማራ ሕዝብ) በሰፊው እየፈጸመ ካለ ከወያኔ ጎን ቆመው እየሠሩ፣ ለወያኔ ህልውናና ጥቅም የበኩላቸውን እያበረከቱ ያሉ ሐሰተኛ ከያኔያንን ስናይ ሁሉም ሰው አንድ ዓይነት የብስለት፣ የተጠያቂነት፣ ኃላፊነትን የመሸከም አቅም፣ የማገናዘብ ችሎታ፣ የሀገርና የወገን ፍቅር ስሜት፣ የሕሊና ወቀሳና ከሰሳ ስሜት፣ የሞራል (የቅስም) ስሜት የሌለው መሆኑን የሚያሳዩ የሚያረጋግጡ ተጨባጭ ማረጋገጫዎች ናቸው፡፡

ለእነኝህ ግለሰቦች ከያኔ ማለት ማንም እንደ ሱቅ ዕቃ እያነሣ እንደፈለገ የሚጠቀምበት፣ እስከተከፈለው ጊዜ ድረስ ለማን? ለምንና ምን? ብሎ ሳይጠይቅና ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም አንጻር ሳይለካ ማንም ቢያሠራው ታዛዥ ሆኖ መሥራት ያለበት ተናጋሪ ዕቃ ወይም ለሆዱ ብቻ ያደረ እንስሳ ማለት ነው፡፡ እንደ ዜጋና እንደ ከያኔ (Artist) ከሀገርና ከሕዝብ የተጣለበት ግዴታና ኃላፊነት እንዳለ ከዚህም የተነሣ በሀገርና በሕዝብ ጥቅም ላይ ለድርድር የማይቀርብ አቋም ሊይዝ እንደሚገባው ጨርሶ አይረዱም መረዳትም አይፈልጉም፡፡ የሚኖሩትና የሚለፉት የማይሞላ ሆዳቸውን ለመሙላት ብቻና ብቻ ነው፡፡

በጣም የሚገርመኝ ነገር እነኝህ ግለሰቦች በዚህ የወረደ የብስለትና የሰብእና ደረጃ ላይ ያሉ ሆነው ሳለ ከርሳቸውን ለመሙላት ለሚያደርጉት ጥረት የሚረዳቸውን የብልጣብልጥነት ችሎታን እንዴት ለመላበስ እንደቻሉ ነው፡፡ ለነገሩ ብልጥ ማለት ብልህ ማለት አይደለምና የሚያስደንቅ አይደለም፡፡ ሕዝቡ በእንደነዚህ ዓይነት ግለሰቦች የተነሣ ዘፋኝነትን ምንም ዓይነት ኃላፊነትና ተጠያቂነት የማይሰማው አጭሉግ፣ የሞራል ዋጋው የወረደ ስድ፣ ትምህርት የማይገባው ደደብ ሁሉ ሔዶ የሚታጎርበት ክፍት የሥራ ቦታ አድርጎ ለማሰብ የተገደደውም ለዚህ ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ግለሰቦች በመስኩ ገነውና ከብረው ስለሚመለከት፡፡

ሌላው በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ የሕዝብ ገዳይ የወያኔ መጠቀሚያ ሆነው፣ ከሕዝብና ከሀገር ገዳዮች ጎን ተሰልፈው እያሉ እኛ የሕዝብ አገልጋዮች ነን! ሕዝብን ማስደሰት ነው ሥራችን!” የሚሉ መሆናቸው ነው፡፡ ለመሆኑ የሕዝብ አገልጋዮች ነን ማለት ምን ማለት ነው? የትኛውንስ ሕዝብ ነው እያገለገሉ ያሉት በሞቴ?

ነብሰበላውና ነጋዴው ወያኔ በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸመውን የመጨረሻ ወንጀል የዘር ማጥፋት ወንጀልን በሕዝባችን ላይ በመፈጸም እጁን በወገናችን ደም ደጋግሞ በመታጠቡ፣ የበርካታ ንጹሐን ወገኖቻችንን ደም በግፍ በማፍሰሱ ሕዝቡ ዳሸን ቢራ የተባለው የንግድ ድርጅቱን ቢራ መጠጣት ማለት በግፍ የፈጃቸውን የወገኖቻችንን ደም መጠጣት ማለት ነው!” የሚል የጸና አቋም ይዞ አድማ በማድረጉ ምክንያት ዳሸን ቢራ ለከፍተኛ ኪሳራ በመዳረጉ ስሙን ቀይሮ ለመምጣት ተገዶ አዲሱን ባላገሩ ቢራሲል የሠየመውን ምርቱን ለማስተዋወቅ በቅርቡ ባሕር ዳር ከተማ ላይ በፍንዳታ የታጀበን የሙዚቃ ኮንሰርት (የዘፈን ትዕይንት) አዘጋጅቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህ የዘፈን ትዕይንት ዝግጅት ላይ ከተፈጸመው የፈንጅ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ዝግጅቱን ለማድመቅ በቦታው የነበረችው ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ከአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ ላይ እኛ የሕዝብ አገልጋዮች ነን! ሕዝብን ማስደሰት ነው ሥራችን!” በማለት በሕዝብ ላይ ተሳልቃለች፡፡

እርግጥ እውነት ነው ከያኔያን የሕዝብ አገልጋዮች ናቸው፡፡ የሚሠሩትም ሕዝብን ለማስደሰት ብቻ ሳይሆን ለማንቃት፣ ለማስተማር፣ ለማሳወቅ፣ ለማጀገን፣ ለማጽናናት፣ ለማነፅ ወዘተረፈም ነው፡፡

የሀገርና የሕዝብ ጠላት የሆነውን ወያኔን እያገለገሉ ግን ያውም አሁን በቅርቡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን መብታቸውን ጠያቂ ወገኖቻችንን በእሩምታ ቶክስ በፈጀባት ባሕር ዳር ከተማ አደባባይ ላይ ገና በግፍ የፈሰሰው ደማቸው ከመሬቱ ላይ ሳይለቅ ሳይጠፋ እንደቀለመ ባለበት የወያኔን የንግድ ድርጅትን ምርት ለማስተዋወቅ ከወያኔዎችና ደጋፊዎቹ ጋር እየጨፈሩ እኛ የሕዝብ አገልጋዮች ነን!” ብሎ ማለት ግን በሕዝባችን ደም ላይ ማፌዝ መቀለድ ብቻ ሳይሆን ይቅር የማይባል ዘለፋና ስድብም ነው፡፡ ይህችው ደንቆሮ የሥነኪን መናፍቅ በዚሁ ቃለምልልስ ላይ ጨምራም “…ከዳሸን ቢራ ጋር ችግር ያለባቸው ካሉ ጉዳያቸውን መጨረስ ያለባቸው ከዳሸን ቢራ ድርጅት ጋራ ነው እንጅ ከእኛ ጋር አይደለም!” በማለት በሕዝብ ላይ ምን ያህል ከባድ በደል እንደፈጸመች እንኳ መረዳት ተስኗት የባንዳነት ተግባሯን ለመከላከል ሞክራለች፡፡

ይህች ሰው የወያኔ መሣሪያ ከሆነች በጣም የቆየች ናት፡፡ ቴዎድሮስ ካሳሁንን አዛኝና አሳቢ መስለው አሳች ምክር በመምከር ለማወየን፣ ከሕዝብ አገልጋይነቱ ለማንጠብ፣ ሕዝብን ለማስካድ ከተላኩት ሥውር ተኩላዎች አንዷ ይህችው ኩኩ ሰብስቤ ነች፡፡ ቴዲን እግዚአብሔር ታደገውና ተጠልፎ ከመውደቅ ተረፈልን እንጅ በተላኩት በነኩኩ ሰብስቤ ውስወሳ ተንሸራቶ ለመውደቅ ተቃርቦ ነበር፡፡ ከእስር እንደተፈታ ገቢው ከትግራይ ለመጡ ለማኞች ብቻ የሚሆን ኮንሰርት (የዘፈን ትዕይንት) እንዳደረገ፣ በዚያው ሰሞንም ወያኔ ለዓባይ ግድብ መቀስቀሻ የተጠቀመበትን አዲስ ቴዲ ስለ ዓባይ ያቀነቀነውን ዘፈን በኢቴቪ እስከመስማት ደርሰን እንደነበረ ወዘተ ወዘተረፈ. በእነዚህ ነገሮችም ቴዲ ወደቀብን ብለን ደንግጠን እንደነበረ የሚታወስ ጉዳይ ነው፡፡

ከያኔያን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእነሱ ምን እንደሚጠብቅ የማያውቁ ሆነው ማወቅ ካሻቸው ምንም ማብራሪያና ትንታኔ መስጠት ሳያስፈልገኝ ቴዎድሮስ ካሳሁን ምን ስለሠራ ሕዝቡ ለእሱ እንዲህ ዓይነት የሞቀ ምላሽ እንደሰጠውና እንደሚንሰፈሰፍለት በማየት ብቻ ከበቂ በላይ ትምህርት ይሰጣቸዋልና ከዚህ ይማሩ፡፡

እናም ከያኔያን ሆይ! ብትችሉ እንደ ቴዎድሮስ ካሳሁን ሁኑ፡፡ ባትችሉ ግን እባካቹህ ፈጽሞ በምንም ዓይነት ሁኔታ ቢሆን የወያኔ መጠቀሚያ ሆናቹህ የገዛ ሀገራቹህንና ሕዝባቹህን አትጉዱ አታጥቁ? ወያኔ እኮ ነገ ጠዋት ጠፊ ነው፡፡ ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ያኔ የት እንገባለን? ምን ይውጠናል?” ብላቹህ አስቡ እንጅ ጃል!

እርግጥ ነው ወያኔ እናንተን ለማሳሳት ለማርከስ እንደ ዳሸን ቢራ ባሉ ድርጅቶቹ አማላይ ክፍያ በማቅረብና ለተለያዩ የሥነኪን ሥራዎች ስፖንሰር (ደጋፊ) በመሆን፣ ማስታወቂያ በማሠራት እናንተን በጥቅም ደልሎ መጠቀሚያ ሊያደርጋቹህ ይጥራል ሲያደርግም ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ እንደ የማለዳ ኮከቦች ዓይነት የትወና ውድድር ዝግጅት፣ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን (የዘፈን ትዕይንቶችን) እና ከያኔያን የሚሠሯቸውን የወያኔ የንግድ ድርጅቶች ማስታወቂያዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

በእርግጠኝነት የሥነኪን ዓላማ ምንነትና ግብ የገባው ከያኔ ወይም የሥነኪን ሰው ምንም ዓይነት መደለያ ቢቀርብለት በምንም አይደለልም፡፡ እሱን የሚያረካው ለሕዝብ በሚያቀርበው የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር በሚሞክሩና ለሕዝብና ለእውነት ጥብቅና በቆሙ ሥራዎቹ ነው እንጅ ሥነኪንን አርክሶ ከሕዝብ ጥቅም በተፃራሪ ተጉዞና ወስልቶ በሚያገኘው የረከሰ የግፍ ገንዘብ አይደለም፡፡ ሥነኪንን መጠቀሚያ አድርጎ በአቋራጭ ለመክበር የሚቋምጥ የሥነኪንን ምንነት ዓላማና ግብ የማያውቅ የማይረዳና መረዳትም የማይፈልግ አስመሳይ ከያኔ ነኝ ባይ ነጋዴ ግን ዓላማው በየትኛውም አማራጭ ቢሆን አወናብዶ ገንዘብ ማግኘት ብቻ በመሆኑ እንኳንና አማላይ መደለያ ቀርቦለት ይቅርና በአምስት ሳንቲምም ቢሆን የሚደለል ነው፡፡ የማለዳ ኮከቦች የትወና ውድድር ዝግጅት፣ የወያኔ የንግድ ድርጅቶችን በስፖንሰርነት (በደጋፊነት) የሚጠቀሙ የሙዚቃ ኮንሰርቶች (የዘፈን ትዕይንቶች)፣ የቴሌቪዥን ድራማዎች (የምርዓየ ኩነት ትውንተ ኩነቶች)፣ የወያኔ የንግድ ድርጅቶች ማስታወቂያዎችን የያዙ ጥቂት የማይባሉ የቪዲዮ ፊልሞች (የትዕይንተ ኩነት ምትርኢቶች) እነዚህ ሁሉ ሆዳቸው አምላካቸው በሆኑ ጥበብን በርቀት እንኳ በማያውቋትና ለሀገርና ሕዝብ ቅንጣት ታክል ደንታ የሌላቸው ከያኔ ነኝ ባይ ሆዳም ነጋዴዎች የሚዘጋጁና የወያኔ መጠቀሚያዎች ናቸው፡፡

ይህች ሀገር በወያኔ አገዛዝ ምን ዓይነት ምስቅልቅል ውስጥ እንደገባች፣ በዘር መጥፋት የወንጀል ተግባሩ ወገን ደብዛው እየጠፋ መሆኑ ከማንም የተሠወረ አይደለም፡፡ ሀገራችን ከዚህ ምስቅልቅል እንድናወጣት፣ ራሳችንን እንድናድን ደጋግማ ላሰማችው የድረሱልኝና የንቁ ጩኸት ምላሽ የሰጡና መብታቸውን የጠየቁ ንጹሐን ውድ ልጆቿ ትናንት በየአደባባዩና በየጎሬው በሩምታ ቶክስ ተፈጅተዋል፣ አሁንም ድረስ በየወኅኒ ቤቱ ታጉረው በአረመኔው አገዛዝ ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው ይገኛሉ፣ ለብዙ ዓይነት ተነግሮ ለማያልቅ ሰቆቃ ተዳርገዋል፡፡

ሀገራችን ከገጠማት ከዚህ እጅግ አሳሳቢ ችግር ለመውጣት የሁሉንም ዜጋ ርብርብ የግድ ይጠይቃል፡፡ በዚህ ርብርብ የዳር ተመልካች ወይም ገለልተኛ የሚባል ዜጋ ሊኖር አይችልም፡፡ አንድ ዜጋ ወይ ከጠላቷ ከወያኔና ግብረ አበሮቹ ጋር ነው ወይ ደግሞ ከሕዝብ ወገን ነው፡፡ ማንም ሰው ከሁለቱ ውጭ ሊሆን አይችልም፡፡ የዜግነት ግዴታውን ወርውሮ ጥሎ ስንቶቹ ዋጋ እየከፈሉ ባሉበት ጊዜ በእኔ ካልደረሰብኝ ምን ቸገረኝ!” በሚል በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን ኢሰብአዊ ግፍ በዝምታ የሚመለከት ዜጋ ካለ ይሄ ከወያኔ ተለይቶ አይታይም ወያኔ ነው፡፡ ሕዝብን ፍዳና ሰቆቃ እያሳየ እያበላ ያለው የወያኔ መጠቀሚያ ሆኖ በግልጽ እያገለገለ እየታየም እኔ ገለልተኛ ነኝ!” ማለት ሕዝብን እንደማያስብ መቁጠርና መናቅም ነው፡፡ ይሄ ነውረኛነት የተሞላበት ንቀት ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍል ሁሉም ሊያውቅ ይገባል፡፡

ይህ አቋም የዜጎችን በነጻ የማሰብ ነጻነትንና የመሰላቸውን የመደገፍ ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) እና ሰብአዊ መብትን መጻረር መገደብ ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን በፍጹም አይደለም፡፡ የየትኛውም ሀገር ሕግ ቢታይ በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸመውን የመጨረሻው የወንጀል ጥቃትን ማለትም የዘር ማጥፋትን በግልጽና በስውር በሚፈጽመው አረመኔያዊ ጥቃት ሕዝብን እያጠፋ ያለን እጅግ አደገኛን የጥፋት ኃይል መደገፍ የሚያስጠይቅ የሚያስቀጣ አደገኛ ወንጀል ነው!” ይላል እንጅ ለዜጎች የተፈቀደ መብት ነው!” የሚል አንድም ሕግ በዓለማችን የለም፡፡

የሀገርንና የሕዝቧን አንድነት አጥፍቶ ለመበታተን ሌት ተቀን የሚያሴርን ከዚህም በላይ ለርካሽ ቡድናዊ ጥቅሙ ሲል ሕዝብን ከሕዝብ ጋራ በማጋጨት እስከወዲያኛው እንዳይስማሙ አድርጎ በሚፈጥረው ሐሰተኛ ታሪክ ተቂያቂመው እየተባሉ እንዲኖሩ የሚጥርንና ወደፊት እሱ የማይገዛበት ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜ ልትፈራርስ በምትችልበት ሁኔታ ላይ ያስቀመጠ በሽተኛ የወንበዴ ቡድን መደገፍ፣ ለሕልውናዋ ተነግሮ የማያልቅ መራር መሥዋዕትነት የተከፈለባትን ሀገር ገንጥሎ የሚያስረክብና ለርካሽ ቡድናዊ ጥቅሙ እየቆረሰ ለባዕድ የሚሸቃቅጥን እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባይ የአህዮችን የጥፋት ኃይል መደገፍ፣ ዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) መብታቸውን ስለጠየቁ ብቻ በዜጎች ላይ ኢሰብአዊ ግፍ የሚፈጽምን አረመኔ የግፍ አገዛዝን ፣ የአማራንና ኦርቶዶክስን አከርካሪ እንዳያንሰራራ አድርገን ሰብረናል!” በማለት በሕዝብ ላይ ከሚፈጽመው የዘርማጥፋት ወንጀል በተጨማሪ ለዚህች ሀገር ሁለንተና የማይተካ አስተዋጽኦ ያበረከተችውን የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን መጫወቻ መቀለጃ አድርጎ ያዋረደ የሰበረና እያጠፋት ያለን የአጋንንት ውላጆች የጥፋት ኃይልን መደገፍ የሚያስጠይቅ የሚያስቀጣ አደገኛ ወንጀል ነው!” ይላል እንጅ ለዜጎች የተፈቀደ መብት ነው!” የሚል አንድም ሕግ በዓለማችን የለም፡፡ ከዚህም በላይ በነፍስም የሚያስኮንን፣ የገሃነም ፍርድ የሚያሰጥ የከፋ ኃጢአት ነው፡፡

ስለሆነም የዜጎችን ነጻነትና መብት መገደብ ወይም መጻረር አይደለም፡፡ በመሆኑም እነኝህን አስከፊ ወንጀሎችን የፈጸመውንና እየፈጸመ ያለውን ወያኔን መደገፍ የሚያስጠይቅ ወንጀል እንጅ መብት አይደለም፡፡ ይሄንን ሀቅ ሁሉም ሊያውቅ ይገባል፡፡ ወያኔ እነኝህን በገሀድ እየፈጸማቸው ያሉትን ወንጀሎች ስለመፈጸሙ የማያውቅ አንድም ዜጋ የለም! ይሄ ሆኖ እያለ የዚህ ግፈኛ የጥፋት ኃይል ደጋፊ በመሆኑ እርምጃ የሚወሰድበት ግለሰብ ቢኖር ኃላፊነቱን እራሱ የሚወስድ ይሆናል፡፡ ወያኔ እንዲህ ዓይነት የጥፋት ኃይል መሆኑን እያወቀ እንደዜጋ ይሄንን የጥፋት ኃይል በተለያየ መንገድ መታገልና መቅበር ሲኖርበት የወያኔን አገዛዝ የደገፈ ሁሉ የሀገርና የሕዝቧ ጠላት ነውና ወያኔ ዕድሜ እንዲያገን ተጨማሪ አቅም ሆኖለታልና ፈጽሞ ምሕረት አይደረግለትም!!!

በአሁኑ ሰዓት ማንም ሊገነዘበው እንደሚችለው የሀገርንና የሕዝብን ህልውናና ደኅንነት ከወያኔና መሰሎቹ የጥፋት ኃይሎች እጅ ታድጎ የሀገርንና የሕዝብን አንድነት ህልውናና ደኅንነት ለማስጠበቅና ለማስቀጠል የሚደረገው ሕዝባዊ ትግል በአንድ ደረጃ ከፍ ብሏል፡፡ ከወያኔ ጋር እየረከሱና አረመኔ የጥፋት ኃይሉን ወያኔን እያገለገሉ እንደትናንትናው ሁሉ ዛሬም በሰላም ከርሳችንን እየሞላን እንኖራለን ብለው የሚያስቡ ባንዳና ከሀዲ ሐሰተኛ ከያኔያን ወይም የሥነኪን መናፍቃን ካሉ እጅግ መሳሳታቸውን ልነግራቸው እወዳለሁ፡፡

ባለኝ ግንዛቤ በአሁኑ ጊዜ ሐሰተኛ ከያኔያኑ በየትኛውም ቦታ ይሁኑ፣ በማንኛውም ሰዓት ቢሆን ለዚህ ክህደታቸውና እርኩሰታቸው የሚገባቸውን ቅጣት ሊወስድባቸው የሚችል ሕዝባዊ የነጻነት ኃይል ከአጠገባቸው እንዳለ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ባላሰቡት ሰዓት፣ ባልጠበቁት ቦታና ባልገመቱት ሰው እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚችል ጠንቅቀው ይወቁት፡፡ የመጸጸቻ ዕድልም አያገኙምና ከዚህ በኋላ ባለው እርምጃቸው ካልታረሙ በሚወሰድባቸው ነጻ እርምጃ በሌላ በማንም ሳይሆን በራሳቸው ይዘኑ፡፡ ጨዋታ ወይም ቀልድ አይደለም የተያዘው፡፡ ብዙ ሀገር ወዳድ ወገን ውድ ዋጋ እየከፈለበት ያለ መራራ የነጻነት ትግል ነው የተያዘው፡፡

አሁንም በድጋሜ በርካታ ወገኖችን መራራ ዋጋ እያስከፈለ ያለውን ይሄንን የነጻነት ትግል ቀልድ አድርጎ የሚመለከትና እንደትናንትናው ሁሉ ዛሬም ለከርሱ ሲል የወያኔ መሣሪያ መጠቀሚያ ሆኘ ከሕዝብ ጥቅም በተፃራሪ እቆማለሁ የሚል የሐሰት ከያኔ ካለ ለሚወሰድበት እርምጃ ኃላፊነቱን እራሱ የሚወስድ ይሆናል፡፡

ባንዳ ከያኔያን በአንድ በሁለቱ ላይ እርምጃ ተወስዶ ካላዩ በስተቀር የነጻነት ኃይሉን ማስጠንቀቂያ የምር አድርገው መውሰዳቸው የሚያጠራጥር ይመስለኛል፡፡ በመሆኑም በባንዳነት ተግባራቹህ ቀጥሉና እርምጃው በማንኛቹህ ላይ ሊወሰድና ማንኛቹህ መማሪያ ልትሆኑ እንደምትችሉ ጠብቃቹህ የምታዩት ይሆናል ከማለት ውጭ ምንም ማለት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ አንድ ነገር ግን አስቡ እንደ ወያኔ ባለሥልጣናት በወታደር ተከባቹህ እየተጠበቃቹህ የምትኖሩ ባለመሆናቹህ እናንተን ማጥቃት ባስፈለገ ሰዓት በቀላሉ እርምጃው ሊወሰድባቹህ የሚቻል መሆኑን አስባቹህ ብትሰበሰቡ ወይም ብትታረሙ ጥሩ አይመስላቹህም? በነገራችን ላይ ይህ የነጻነት ኃይሉ ማስጠንቂያ በዋናነት በከያኔያን ላይ ያተኩር እንጅ ሁሉንም ዜጋ ይመለከታል፡፡ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ (የእምነተ አሥተዳደር ቡድን) ስም ተቋቁመው ወያኔን እያገለገሉ ያሉ ቆሻሾችን ጨምሮ፡፡

በዚህ አጋጣሚ በሕዝብ መጠላት አልፈልግም!” በሚል ምክንያት ከወያኔ ጋር ከመነካካት ራሱን የጠበቀውን ወይም ያራቀውንና በዚህም ምክንያት ዋጋ ለመክፈል ተገዶ ዋጋ ለከፈለውና እየከፈለ ላለው ለሰፊው የሥነኪን ማኅበረሰብ ከዚህም በላይ ደግሞ የዜግነት ግዴታቸውንና የሥነኪን ሐዋርያነታቸውን ተረድተው በሥነኪን ሥራዎቻቸው ሕዝባዊ የነጻነት ትግሉን እያገዙ ላሉ ብርቅዬ ከያኔያን እንደዜጋ በግል ላቅ ያለ ምስጋናየን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመጨረሻውን ድል እስኪቀዳጅ ድረስ ከያዘው የወያኔ የንግድ ድርጅቶች ምርት የሆኑ ሸቀጦችን ያለመጠቀምና ያለመገብየት አድማ በተጨማሪ የወያኔ መጠቀሚያ የሆኑ ሐሰተኛ ከያኔያንን ሥራዎችንም ባለመጠቀም፣ ባለመመልከት፣ በአነዚህ ባንዳ ሆድ አደር ሐሰተኛ ከያኔያን የሚተዋወቁ ሸቀጦችንና አገልግሎቶችን ባለመጠቀም ትግሉን አጠናክሮ ይገፋል!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com