June 17, 2017 07:52

3291ቀናትን ያለ ምንም ወንጀል በእስር ላይ 🙁 እማዋይሽ አለሙ አንቺ የሁላችንም እናት ነሽ!!!

ሚያዚያ 16 ቀን 2001 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ዋለች። ማዕከላዊ ተብሎ ወደ ሚጠራው የአገዛዙ የቶርቸር ቻምበር ተወሰደች። በ4 ወራት የምርመራ ወቅት ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባታል። በጡቶቿ ላይ የደረሰባት ግርፋት ዛሬም ድረስ ሕመም ጥሎባት አልፏል።

ከቶርቸር ቻምበራቸው እንደወጣች ተከሰሰች።

በ”እነ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ” መዝገብ ከግንቦት ሰባት ጋር በመተባበር መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ አሲራችኋል ተብለው ከተከሰሱት ውስጥ ብቸኛዋ ሴት ናት:- እማዋይሽ አለሙ!

8 ወራት ባስቆጠረ የፍ/ቤት ሂደት እማዋይሽ አለሙ ላይ የእድሜ ልክ እስራት ተበየነ። ይህን ውሳኔ ለማስቀልበስ ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ ቢኬድም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዲፀና ተደርጎባታል። በአሁኑ ሰአት በቃሊቲ ወህኒ ቤት ትገኛለች። የእማዋይሽ ጥፋት በሀገር ጉዳይ ያገባኛል ማለቷ ብቻ ነው። ሀገሩ የሁላችንም ነው፣ የእናንተ ብቻ አይደለም! ፍትሕ ለእናታችን፣ ፍትሕ ለእማዋይሽ አለሙ!

# justice4Ethiopia

#justiceEmawayesh

Muluken Tesfaw

እማዋሽ ዓለሙ፤ የጽናት ተምሳሌ!

 

ወይዘሮ እማዋሽ ዓለሙ ከሚያዚያ 16 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 9 ዓመታት በትግሬ ወያኔዎች ጉረኖ ውስጥ ናት፡፡ የእማዋሽ ወንጀል ዐማራነት ነው፤ እማዋይሽ ነጻ የምትወጣው መላው የዐማራ ሕዝብ ነጻ የሆነ ቀን ነው፡፡

አንዷለም አራጌ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ‹‹የአገር ፍቅር እዳ›› በሚል በጻፈው መጽሐፉ ከሚወዳት ሚስቱ እና ከሚናፍቁት ልጆቹ እንዴት የትግሬ ወያኔዎች ነጥለው ወስደው እንዳጎሩት በዝርዝር ይነግረናል፡፡ አንዷለም ከልጆቹ ፊት ጠመንጃ የደገነበት ሰው ትግሬ ነበር፤ ማዕከላዊ ጠባቂው፣ መርማሪው፣ አሳሪው ፈራጁ በሙሉ ትግሬዎች ነበሩ አለ፡፡ ቃሊቲ ወኅኒ ከወረደ በኋላም እግር ተግር የሚከታተሉት ቁንጣን ያስቸገራቸው ትግሬዎች ናቸው፡፡

እነ እማዋይሽ፣ እነ እስክንድር፣እነ አንዷለም፣ እነ አሳምነው ጽጌ፣ እነ ተፈራ ማሞ…. ነጻ የሚወጡት መላው የዐማራ ሕዝብ ነጻ የወጣ ዕለት ነው፡፡