June 22, 2017 –

 ቆንጅት ስጦታው 

የአንበጣው መንጋ የወረራቸው አካባቢዎች የመንግሥት እገዛ ተነፍጓቸዋል፤

በምዕራብ ጎጃምና አዊ ዞኖች የገበሬውን ሀብት ንብረት የሚያወድም አደገኛ አንበጣ ተከስቷል፡፡ አንዱ የአንበጣ መንጋ በቀን 16 ኪሎ ሜትሮችን መጓዝ የሚችል ሲሆን ባሕር ዛፍን ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት ሰብልና እጽዋት መድምዶ በመብላት ያወድማል፡፡ በምዕራብ ጎጃምና በአዊ ዞኖች ከአራት ወረዳዎችና ከ50 በላይ ቀበሌዎች በአንበጣው መንጋ ተወረዋል፡፡

አንበጣው የሚመርጠው የለም፤ ገበሬዎች ‹‹ሁሉን በይ አንበጣ›› ይሉታል፡፡ የግብርናና የልማት ባለሙያዎች ለክልሉ መንግሥት ግብርና ቢሮ አንበጣው መጥፋት የሚችልበትን መድኃኒት ወይም ማንኛውም ዓይነት እገዛ ቢጠይቁም በአገር ውስጥ ለዚህ ዓይነት አንበጣ መከላከያ የሚሆን መድኃኒት የለም የሚል መልስ እንደተሰጠ ሰምተናል፡፡ አስቸኳይ ርብርብ ተደርጎ መከላከል ካልተቻለ በስተቀር አጠቃላይ የምዕራብ ጎጃምንና የአዊ አካባቢዎች ያለውን ሰብልና እጽዋት አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሊያወድም ይችላል ተብሏል፡፡

እስካሁን ድረስ ባለው ከሃምሳ በላይ ቀበሌዎች በበልግ ዝናብ የበቀለ ሰብልና በአካባቢው ያለውን እጽዋት ሁሉ እንዳወደመ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Muluken Tesfaw