By ሳተናው

June 25, 2017 00:12

የአቤና የሙሉቀን ውይይት ዋነኛው ሀሳቤ እንጂ ሌሎች ጉዳዮችንም አነሳለሁ፡፡ ስለ ሰዎች ማንነት መረዳት ስንችል ለመተቸትም ለማመስገንም ብቃቱ ይኖረናል፡፡ አንድን ሰው የምንወቅሰው ወይም የማመሰግነው እኔ የማስበውን አይነት አስተሳሰብ ስላለውና ስለሌው በሚል መሆን አልነበረበትም፡፡ ይልቁንም በሀሳብ የሚስማሙበትና የማይስማሙበት ከልብ በሆነ አስተሳሰብ ይሁን እንጂው፡፡ እንዲህ ከሆነ በሀሳብ አንድ ከሆነን መልካም ከአልሆንም ግን ወይ እኛን የሚቃወሙን ሰዎች ሀሳብ ሲገባኝ ወይ የእኛ ሀሳብ ሲገባቸው የመለወጡ እድል ከፍተኛ ነው፡፡ ከዛም ጭራሽ በልዩ መተማመን ሀሳብን መጋራት እድል ይፈጥራል፡፡ እሰከ ወዲያኛውም የሚያስማማ ነገር ከሌለም መልካም ነው፡፡ ብቻ ከውስጥ በሆነ አመለካከት ይሁን እንጂ፡፡ በአብዛኛው ያለው መስማማትም በሉት መቃረን ግን ከዚህኛው አይነት የተለየ ነው፡፡ አብዛኛው የሚጠላም የሚወድም ስለደገፉትና ስለተቃወሙት ነው፡፡ ሌላው ብዛት ያለው ከእነጭርሱ የሚያምንበትን እውነት ክዶ በአድርባይነትና ለሆድ ሕልናውን የሸጠ ነው፡፡ ዛሬ አቤ ቶክቻው ሙሉቀን ተስፋውን ጋብዞ ሲወያዩ ብዙ ነገሮችን ነበር የታዘብኩት፡፡ አቤና ሙሉቀን በእርግጥ በሀሳብ እምብዛም የሚለያዩ ሆነው አላገኘኋቸውም፡፡ በአንድ ነገር ላይ ግን ሙሉ በሙሉ የተሰማሙ አልመሰለኝም፡፡ እኔ ደግሞ ከሙሉቀን ጋር በዚሁ ጉዳይ አልተሰማማሁም እሱም ትግሬ ሁሉ የወያኔ አይነት ጸባይ አለው የሚለውን፡፡ ይህን ስል ግን ሙሉቀን የተናገራቸውንና ያመነባቸውን ጉዳዮች እያቃለልኩ አደልም፡፡ እግረ መንገዴን ግን ሙሉቀን እንደውም ዛሬ በተናገረውና በአለው አቋሙ እንድወደው ነው ያደረገኝ፡፡ ከዚህ በፊት በአንዳንድ በሚጽፋቸው ነገሮች ምክነያት በጣም እጠራጠረውና የወያኔ ውዥምብረ ፈጣሪ እስኪመስለኝ አስቤው ነበር፡፡ ቢያንስ ከልቡ ስለሚያስበው ነገር እየተናገረ እንደሆነ በመረዳቴ አሁን በሀሳብ ልሞግተው የምችልበት እድሉ ተፈጥሯል ብዬ አምናለሁ፡፡

ወደ ጉዳዩ ልመልሳችሁ፡፡ በትክክልም ሙሉቀንም አቤም በአንድ ነገር ተስማምተዋል፡፡ የወያኔ የበላይነት ሳይሆን የትግሬ የበላይነት በሚለው፡፡ በወይይቶቻቸው ያነሷቸው ጉዳዮችም ግልጽና በማያሻማ ሁኔታ ነው፡፡ አዎ እንዲህ ፍርጥርጥ ሲደረግ ለውዥምብር ፈጣሪዎም እድል አይሰጥም፡፡ ይህ አይነት አቋም ያለው ከውስጥ በሆነ የሚደረግ ውይይትም በሉት ሀሳብ መፋጨት አለመኖሩ የውሸት እርስ በእርስ እየተላላሱ መኖር ይሄው ዛሬ ነቀርሳ ሆኖ አገርን ሳይቀር ለማፍረስ ስጋት ሆኗል፡፡ እኔና ሙሉቀን ምን አልባትም በተወሰነ አቤ የማንሰማማው ነገር ትገሬ ሁሉ በሚለው እንጂ አብዛኛው ትግሬ ቢባል እንኳን እኔ መከራከሪያ የሚሆነኝ መረጃ ስለማይኖረኝ ሊሆን እንደሚችል ከመቀበል በቀር እድል የለኝም፡፡ ግን ከወያኔ ጋር ጥቂትም ቢሆኑ እንማንኛውም ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ያሉ እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ ይን ስል ግን እንደ አቤ የአረና አባላትን አይነቶቹን አደለም፡፡ የአረና አባላትን አስመልክቶ ከአቤ ይልቅ ወደ ሙሉቀን የቀረበ እምነት አለኝ፡፡ በወያኔ ስርዓት ተቃዋሚው(ትክክለኛ) እስካልሆነ ድረስ የትኛውንም ጥቅም ከፈለገ ትግሬ መሆን ሁሉንም ያሟላ መስፈርት እንደሆነም አምናለሁ፡፡ አብዛኛው ሊባል የሚችል ትግሬም የተከተለው ይሄንኑ ነው፡፡ ይሉኝታ፣ ሀይማኖት፣ ሕሊና ሁሉም ነጥፈውበት አብዛኛው ሊባል የሚችለው ትግሬ የዚህ አስተሳሰብ ሰለባ በመሆኑ ይህን እያየ ያለው ሌላው ኢትዮጵያዊ ትግሬን ሁሉ በአንድ ለምልክት እንኳን ሳይቀር እነድ እንደሆኑ እንዲያስብ እየተገደደ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ዛሬ ላይ  ኧረ እነዚህ (ትግሬዎች) ምን ፍጡሮች ናቸው የሚለው እየበዛ ነው፡፡ ከጊዜ ወደጊዜ ሁኔታዎችን ቢያንስ ለራስ ከማሰብ ይለወጣሉ ተብሎም ሲታሰብ ጭራሽ የባሰ የከፋ ባህሪ እያመጡ ነው፡፡ ድሮ ትግሬ ሀይማኖተኛ ነው ሲባል የሰማ ዛሬ ላይ ቀድሞ የነበረውን አመለካከት ሊያቆየለት የሚችል አንድም ምልክት ማየት ይቸገራል፡፡ ስለዚህ ኧረ እነዚህ ምን ፍጡሮች ናቸው ከሚሉት መደባለቁ ግድ ይሆንበታል፡፡

ለሙሉቀን ከአየው ነገር አንጻር ከትግሬ ደህና ለመገኘቱ ምንም ምልክት ያለው አይመስለኝም፡፡ ሙሉቀን ከልቡ እንደዚያ ማሰቡ ስህተት አልነበረም፡፡ አቤም ሀሳቡን ይጋራዋል፡፡ አንድ ነገር ግን አቤም ሙሉቀንም የዘነጉ ይመስላል፡፡ ቢያንስ ሊሆን ይችላል የሚለውን እድል ላለማጣት፡፡ እንደ እውነቱ ደምጻቸው ከፍ ብሎ የሚሰማውና ድርጊታቸውም በይፋና በአደባባይ ዛሬ የሚታየው ኧረ እነዚህ ምን ፍጡሮች ናቸው የምንላቸው አይነት ትግሬዎች እንደሆኑ አንዘንጋ፡፡ ሌሎቹ ቃል ቢተነፍሱ ምን እንደሚገጥማቸው እኛም እንገምታለን እነሱ ደግሞ በበለጠ ያውቁታል፡፡ ሌላው ምን አልባት እድሉን አግኝተው ቢደመጡም የሚያምናቸው የለም፡፡ ትግሬ ሁሉ በአንደ ኧረ ምን ፍጡሮች ናቸው በሚባሉት ተመስሏልና፡፡ በአጋጣሚ ሆኖ ከምርም የወያኔ ሥርዓት ያማረራችን ትግሬዎች ለማወቅ ግን እድሉ ነበረኝ፡፡ ይህም በሌላ ቦታ የሚኖሩ ትግሬዎች ሳይሆኑ እዛው ትግራይ የሚባለው ክልል የሚኖሩ፡፡ እንደ እውነቱ ለእነዚህ ከእነዚህ ሰዎች ሌላው (ትግሬ ያልሆነው) ኢትዮጵያዊ የተሻለ ነፃነትም እድልም አለው፡፡ እነዚህ አይነት ትግሬዎች ግን ከትግራይ ውጭ አንደም ቦታ አልገጠመኝም፡፡ በቅርብ የማውቃቸው ከዛም በላይ ከወንድም ያልተናነሰ ጓደኝነት የነበረን ትግሬዎች በሚያሳዝነኝ ሁኔታ ኧረ ከሚባሉት ምድብ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ፡፡

በጣም ይከብዳል! አብዛኞቹ አነሰም በዛም ፊደል የቆጠሩ እንደሆኑና አንዳንዶቹም ሌላውን የውጭውን ማህበረሰብ ሳይቀር ለማየት እድል የገጠማቸው እንደሆኑ ሳስብ በዚህ አይነት አስተሳሰብ አረንቋ መግባታቸው ተስፋ የሚቆርጡባቸው መሆኑ ይበልጥ ያሳዝነኛል፡፡ ይህን ሊሆን የቻለው ደግሞ ከላይ የጠቀስኳቸውን ሕሊናን፣ ባህላዊና ሀይማኖታዊ እሴቶችን በአጠቃለይ ሰውኛ ማንነትን በመካድ እንጂ እውነቱ ጠፍቷቸው ወይም ሁሉም ከልብ የመሰላቸው ስልሆነ አደለም፡፡   በሌላው ጽንፍ የሚገኙት ሕሊናቸውንና እምነታቸውን ሰብዓዊ ማንነታቸውን ላለማጉደፍ በጽናት የቆሙትን ትግሬዎች ሳሰብ እጽናናለሁ፡፡ ብዛታቸው ምን ያህል እንደሆነ መገመት ያስቸግራል፡፡ ሁሉም በውስጡ ማንነቱን ጠብቆ ይኖራል እንጂ ምንም ነገር መናገር አይችልምና፡፡ ምን አልባትም በመቶኛ ቢሰላ ይበልጠው ትግሬ ከዛም በላይ 80ና 90 በመቶ የሚሆነው ትግሬ አሁንም ድሮ የሚነገርለት የእምነትና ባሕል እሴቶች የሆነው ሊሆን ይችላል፡፡ ከመቶ 10 ሁሉም ነገር በእጃቸው ስለሆነ ሰው እነሱን እየሰማ ትግሬ ሁሉ እንደነሱ ነው ብሎ ሊያምን የሚችልበት እድል እንደሚኖር ማሰብ ስህተት አደለም፡፡ በሌላ አገር ያሉትን እድል ያገኙትን አሁን አሁን እየሰማን ነው፡፡ አገር ቤት ያለው ትግሬ ቃል ቢተነፍስ ምን እንደሚገጥመው ብዙም አያጠያይቅም፡፡ በሌላ አገር የሚኖሩትም አገር ቤት ስላለው ወገናቸው መናገሩ አደጋ አለበት፡፡ ሌሎቹ ደግሞ የወያኔን እኩይ ሴራ መቃወም የአማራ ወዳጅ ምናምን በሚልና ሌሎች ትግሬን እንደመክዳት እንዲቆጠርባቸው በማድረግ እንዲሸማቀቁና በሌሎች ዘንድ አመኔታ ስለማያገኙ ዝም እንደሚሉ እናስባለን፡፡ እንግዲህ መልካሞቹ ትግሬዎች በእነዚህ ሁሉ ተጋርደው ኧረ እነዚህ የምንላቸውን ብቻ እያየንና እየሰማን ትግሬ ሁሉ በሚል በአንድ መፈረጁ ልክ አይደልም የሚል ነው የእኔ አቋም፡፡ ሙሉቀን አቤም ይህን አስበውት አይ ይህን ሁሉ አስበን ነው አሁን ያለው እምነት ከአሉ ምን አልባት ወደፊት እውነታው እየተገለጠ ከሄደ ተሳስተን ነበር ለማለት አይቸገሩም ባይ ነኝ፡፡ አሁን ያመኑበትን እንጂ ለማንምና ለምንም ብለው አላሰቡትምና፡፡

የሙሉቀንን አቋም የምጋራውና የማምነበት ነው፡፡ እኔ እስካለኝ መረጃ ያመንኩበትን እንጂ ለመመሳሰል እንደሁኔታው በሚል ዲፕሎማሳዊ አካሄድ አልቀበለውም፡፡ ይህ እድል እየሆነ ያለው ለክፉዎች ነው፡፡ ሕሊና ያላቸው ለነገሮች ሲቆጠቡ ሕሊና በሌላቸው እየተቀደሙ ይሄው አሁን ያለንበት ደርሰናል፡፡ ምን አልባት ስለ ግንቦት 7ና ኢሳት ሙሉቀንም ዲፕሎማሳዊ መልስ ለመስጠት የቃጣው መሠለኝ፡፡  ኢሳትም ሆነ ግንቦት 7 ጽንፈኛ የሆነ አቋም ይከተሉ አደለም፡፡

ከምንም ነገር ከጸዱ ግን ለቆሙለት አላማ ብቻ እንጂ እስኪ እናስታመው በሚል የሚሄዱበት አካሄድ ብዙ ችግር ፈጥሯል አሁንም እየፈጠረ ነው፡፡ የግንቦት 7 እንቅስቃሴ እንደ እውነቱ እጅግ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ ዝም ብሎ ብዙ ሰው እየተከተለው ነው በሚል በጅምላ እኔም እሱን ልደግፍ ከአልሆነ ከመሪዎቹም ሆነ ከደጋፊዎቹ በአሳማኝ ሁኔታ ይህና ይህን እየሰራ ነው ብሎ የሚናገር የለም፡፡ ብቻ ሁሉም ማስታወቂያ ነጋሪ ነው፡፡ ግንቦት 7 ሰራኋቸው የሚላቸው “ገድሎችን” ስንሰማ ደግሞ ይበልጥ የሚያበሳጭ ነው፡፡ ከመጀመሪያው ጀምሮ የምንጠይቃቸውን ጥያቄ አንደም አይመልስም ብቻ ተዓምር ሊሰራ እንዳቀደ ያወራል፡፡ የግንቦት 7 እድሜ አሁን 10 ዓመት ሳይሆነው አልቀረም፡፡ ያ ሁሉ የሕዝብ አመፅ አገሪቱን ባናወጠበት ወቅት አይደለም አገር ቤት አለኝ የሚለው ሰራዊት ውጭም አለወሁ ሲል የነበረው እንቅስቃሴ ጸጥ ነበር ያለው፡፡

ሌላው ንቅናቄ በሚል ግንቦተ 7 ሌሎች ቀድመው የነበሩ የኦሮሞ ቡድኖች በመሪነትና እናንቀሳቅሰዋለን የሚሉት የቡድኖች ስብስብ ነው እንቆቅልሹ፡፡  አሁንም አንድነቱንና ሕብረቱን ከልብ ከሆነ እደግፈዋለሁ፡፡ ግን በብዙ መልኩ አላማው ግልጽ ያልሆነ ነው፡፡ አንድነቱም የጠላቴ ጠላት ወዳጄ በሚል እንጂ አንድ የሚያደርግ እሴት ኖሮ አይመስልም፡፡ ኢትዮጵያዊነትና አንድነት ከሆነ አዎ በትክክለም ከልብ አምነበታለሁ! ሆኖም በዋናነት ንግናቄውን የሚመሩት ግለሰቦች የዚህ አምነት ባለቤቶች መሆናቸውን መጠራጠር ብቻም ሳይሆን ቢያንስ አንዳንዶቹ በኢትዮጵያ አንድነት እንደማያምኑ አውቃለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ ሲያወናብዱን ለየት ያለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ይሉናል፡፡ ምን አይነት ለየት የለች; ለሁሉም የምትመች ምናምን፡፡ እንደ እውነቱ ይሄ ዝም ብሎ ተራ ወሬ እንጂ በተግባር ሊገለጥበት የሚችል አንደም ፊንጭ ያላቸው መሪዎች አደሉም ይህን ያወሩት፡፡ ኢትዮጵያን የመንግስተ ሰማያት ያህል እንደሆነች አድርጎ ለመፍጠር እንደሚቻል ማውራት ይቻላል ግን ወሬው ጭራሽ እኛም በተሰፋ ስንጠብቅ እጅግ እያዘገየን እንጂ መፍትሄ እያመጣ እንዳልሆነ ልብ ሊሉት ይገባል፡፡ ሲጀምር አዲሲቷን ኢትዮጵያን የሚለው አስተሳሰብ ስህተት ነው፡፡ ሁል ጊዜ እኮ ችግራችን ይህ ነው፡፡ እኛ ሁሉንም ፈጣሪና የሁሉ ነገር መጀመሪያ መሆናችን፡፡ ደርግም እኮ አዲሲቷ ኢትዮጵያ የሚል ነገር ነበረው፡፡ ኧረ አሁን አገሪቱን የወንበዴዎች መናህሪያ ያደረጋትም እንደዛው ነው የሚለው፡፡ ሕዳሴ ምናምን ጆሮአችን እስከሚደነቁር አደል የምንሰማው;

አሁን ኢትዮጵያውያን የሚያስፈልጋቸው ቢያንስ አሁን ከአሉበት ቆመው ወደፊት የተሻለ ነገርን እያስተካከሉ መሄድ ነው፡፡ ዛሬ በብዙዎች የአጼዎቹ ሥርዓት እየተባለ እንደማስፈራሪያና ለሥርዓት ሥር ነቀል ለውጥ ምክነያት የሚጠቀሰው ያ የኣጼዎቹ ሥርዓት ጋር ተመልሰን ስናስብ በቀላሉ ሊስተካከሉና በእርግጥም በንጉሱ ሳይቀር እየታሰበባቸው የነበሩ ጉዳዮች በነበረው መሠረት ላይ በሂደት ሊለወጡ የነበሩ ችግሮችን አሁን ከገባንባቸው ውስብስብ ሁኔታዎች አንጻር ስናይ ብዙ የሚያስቆጩ ነገሮች አሉ፡፡ አገርና ሕዝብ የሚመራው ከየትም በሚለቃቀሙ በይመስለኛል የግልሰቦች አስተሳሰብ አደለም፡፡ አገር ለመምራት ብዙ ሕዝባዊና አገራዊ መሠረት ያላቸው እሴቶች ሊኖሩን ይገባል፡፡ የአጼዎቹ ሥርዓት ምን ጉድለት ምን በጎ አንዳለው አናውቅም፡፡

የደርግም እንዲሁ፡፡ ሁሌ የሚነገረን የአለፈው ሥርዓት ሲኦል የሆነው ክፍል ነው፡፡ እሱም በእርግጥ የሆነ ሳይሆን በፈጠራ ወሬ የተቀነባበረ ጭምር፡፡ በዚህ መልኩ የአገርና የሕዝብ መሠረት እየተናጋ ዛሬ ለሴረኞች እድል ፈጥሯል፡፡

ዛሬ ንቅናቄ ብለው የተሰባሰቡትን ቡድኖች ስናይ እንደእውነቱ ራሳችንን የሚያስተዛዝብ ነው፡፡ ከቡድኑ ውስጥ አንድም በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ ጥርት ያለ አመለካከት ያለው የለም፡፡ ይበልጠውን እድሚያቸውን ሙሉ ለኢትዮጵያ መፍረስና ኢትዮጵያዊነት መጥፋት ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦች የተሰበሰቡበት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማንንም መለማመጥ ያለበት አይመስለኝም፡፡ ለመመሳሰል በሚል የኦነግ ባንዲራና የኢትዮጵያ ባንዲራ አንድ ላይ እንዲውለበለቡ ማድረግ ትልቅ ስልት ሆኗል፡፡ አዝናለሁ የኦነግን ባንዲራ ከኦነጋውያን ውጭ ማንንም አይወክልም፡፡ ሌላውም እንደዛው፡፡ ምን አይነት አስተሳሰብ እንደሆነ አላውቅም፡፡ የኦነግ ባንዲራ እኮ ኦሮሚያ የተባለች አገር ስትመሰረት ሊውለበለብ የታሰበ እንጂ የፓርቲም ብቻ አደለም፡፡ አሁንም ማንንም መለማመጥ አያስፈልግም፡፡ ኦሮሚያም የሚባል አገር እንፈጥራለን የሚሉ ይሞክሩት፡፡ ታሪክም ቢሆን የብዙ ሕዝብ ተሳትፎ የኖረ ኢትዮጵያዊነት አለ፡፡ ይህን ከሚክዱ ጋር በመላላስ የሚጠፋው ጊዜ ለበለጠ ውድቀት የሚዳርግ ነው፡፡  ኦነግና ኦነጋውያን የኦሮሞን ሕዝብ ወኪል ሆነው እስከዛሬ የሸወዱን ይበቃል፡፡ ልክ ቅድም ለትግሬዎቹ እንደተናገርኩት ነው፡፡ ኦነግና ኦነጋውያን ጩኸታቸው ትልቅ ነው፡፡ ሌላው ሰኚ ጎበና ዳጬ ላለመባልና ኤርገምቱ ነፍጠኛ ላለመባል አንገቱን ደፍቶ ዝም ብሏል፡፡ ለኦሮሞ ኢትዮጵያዊነትን በልበሙሉነት አደባባይ ወጥቶ መናገር እንዲህ ቀላል አልነበረም ለአለፉት 26ዓመታት፡፡ አሁን አሁን ብዙ ኦሮሞዎች በድፍረት እየተጋፈጡት ይገኛሉ፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥም ብዙዎች እየተቀላቀሏቸው ነው፡፡ 40 ዓመት ሙሉ በፈጠራ ወሬ ህዝብንና አገርን ከመሠረታዊ እሴቶችና ማንነት አምክነው ዛሬም የከሰሩበትን ውሸት ሊጭኑብን ይሞክራሉ፡፡ አሁን ላይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ለመታደግ ግልጽ አቋም መያዝ ግድ ይላል፡፡ ያኔ ሚዛኑ ወዴት እንደሚደፋ በግልጽ እናየዋለን፡፡ 26 ዓመት ዝም ያሉ አንደበቶችና አእምሮዎች ጉልበታቸው እየበረታ ሲመጣ እንደ ደራሽ ውሃ ኢትዮጵያዊነት ዳግም በኢትዮጵያ ጠላቶች ላይ እንደሚመጣ አልጠራጠርም፡፡ ኢትዮጵያ ስለምታስፈልጋቸው እንጂ ኢትዮጵያ ስለምትፈልጋቸው አደለም ዛሬ ኢትዮጵያውያን መታገል ያለባቸው፤፡ ያለ ኢትዮጵያ እንኳን አሁን በአለው ሁኔታ ለየብቻ ሆኖ ይቅርና በሰላሙም ቀን የተለዩት አፍረው እንጂ አሁን እንደምትናፍቃቸው እናውቃለን፡፡

ኢትዮጵያን የሚል ደግሞ አንድ ምልክት ያስፈልገዋል፡፡ አንድ ሰንደቅ አላማ፡፡ ሥምምነት ላይ ከተደረሰ አረንጓዴ ቢጫ መሆኑ ቀርቶ ሌላም ይምጣ፡፡ እስኪ ታሪክ እንጀምር ለሚሉትም እድሉ ይሰጣቸው ሕዝብ የሚቀበላቸው ከሆነ፡፡ ታሪክና አፍሪካዊ ምልክትነቱ ግን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ምልክት ጉልበቱ የበረታ ነው፡፡ በእርግጥም ለዚች ባንዲራ የቀደሙ አባቶች የሆኑ የሑሉም ኢትዮጵያ ሕዝብ ወኪሎች ተሰውተዋል፡፡ ይህን እውነት ክዶ በየትኛውም መልኩ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት እታገላለሁ የሚል ከአለ ጥርት በአለው አቋማችን ሁላችንም ያለመሸማቀቅ ስንቆም እናየዋለን፡፡ በቃ አንድ አገር አንድ ባንዲራ የሚለው የፅና እምነቴ ነው፡፡ አንድ ቋንቋ አንድ ሀይማኖት ድሮም አልተባለም ወደፊትም ሊባል አይችልም፡፡ አለም በእምነት በምክነያት ስንቶቹን በሚጨፈጭፍበት በዛ በኋላ ቀር በነበረው ጥንታዊ ዘመን ሳይቀር እኮ ነው ይህች አገር የእምነት ነጻነት የነበረባት፡፡ ቁራኑም፣ ክርስትናውም ምስክር ነው ለዚህ! ግድፈቶች ማስተካከልና አዲስ መፍጠር የተለያዩ ናቸው፡፡

ሰሞኑን የኦሮሚያው ፕሬዘዳንት አቶ ለማ መገርሳ ትልቅ መነቃቃትን የፈጠሩ ይመስላል፡፡ አዎ እንዲህ ነው ሕዝቡ አንድነቱን ተነጥቆ እንጂ አንድነት የሚለውን ቃል ጠልቶት አደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ ነኝ ስለአለ አሮሞነቱን እንደካደ እንዲቆጠር በማሸማቀቅ ነበር ኢትዮጵያዊነቱን ኦሮሞ የተነጠቀው፡፡ ለማ ጭራሽ አንዲት አገር እያሉ ነበር ለአድማጮቻቸው ሲናገሩ የነበሩት፡፡ ለማን ከመጀመሪያው ጀምሮ እየተከታተልኳቸው ነው፡፡ እስከሁን ጥሩ ነው፡፡ አንዳንድ ቦታ እንደልባቸውም መሆን እንደማይችሉ እረዳለሁ ግን በዚሁ ከቀጠሉ ለውጡን ሊያመጡት እንደሚችሉ አልጠራጠርም፡፡ እንደ አለማየሁ አቶምሳ ለማም አደጋ ላይ እንዳይወድቁ ግን መስጋቴ አልቀረም፡፡ ይህን የምለው እስካሁን በአየሁት ለማ እየሄዱበት ያለው አካሂድ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት እድል እየፈጠረ እንደሆነ ስለተሰማኝ ነው፡፡ ለማ ድብቅ የሆነ ሴራ አላቸው የሚለውን እስካሁን በአየሁት ምልከት የለም፡፡ በእርግጥም ለማ ብቻም ሳይሆኑ አሁን ያለው ኦሮምያን የተረከበው ቡድን በብዛት አባላቶቹ ከዚህ በፊት ከአየናቸው ይለያሉ፡

፡ የሕዝባቸውንም ጉዳይ በግልፅ፣ በድፍረትና በቁጭት ሲናገሩት እናያለን፡፡ የቀደሙ አባቶችን ታሪክ፣ የአገርን አንድነት፣ የሕዝብ እሴቶችን እስካሁን ኦሮሚያን ከመሯት ከአንዳቸውም አልሰማንም ነበር፡፡ በዚህ ከቀጠሉ ለማና ቡድናቸው በኦሮሞ ብቻም ሳይሆን በላው ኢትዮጵያ የሚኖራቸው ድጋፍ ትልቅ ይሆናል፡፡ ያኔ እንደማስፈራሪያ የተነገረን አገሪቱን ለኦሮሞዎች አሳልፈን እንሰጣታለን ለሚሉን አገሪቱ ጥንቱንም የኦሮሞ አባቶች የመሠረቷትና አሁንም የአባቶቻቸውን አገር ለማዳን ለተነሱ ኦሮሞዎች ወያኔዎች ሳይሆኑ ኢትዮጵያውያን በክብር እንዲመሯት ኢትዮጵያን ያስረክቧቸዋል፡፡ ግን አሁን ላይ ገና ነን፡፡ በያዙት እያበረታታን እናያቸዋለን፡፡ ሕዝብም በተቻለው ሁሉ ሊተባበራቸው ይገባል፡፡ እነሱም ተቀዳሚ ሥራቸውን በተለይ በግፍ በማጎሪያ ታጉረው ለሚሰቃዩ ዜጎች መድረስን መሆን አለበት፡፡ በዚህ ማንነታቸውንም እንለካዋለን፡፡ እውን እውነተኛ ከሆኑም ለማና መረራን የሚያቃርን አንድም ምክነያት አይኖርም፡፡ ኦብኮ መሆንና ኦፒዲኦ መሆን አደለም የሚሆነው ቁምነገሩ፡፡ ለሕዝብና አገር አንድ በሚያደርግ አላማ እንጂ፡፡ ያኔ በቀለ ገርባ የኦፒዲኦ ሊቀመንበር  ቢሆን ችግር የለብንም ለማም የኦፕኮ ሊቀመንበር፡፡ ለጌቶች በሎሌነት ከማደር ነጻ የሆነ በአላማ አንድ የሆናቸውን መሰሎቹን ማወቅ አያዳግተውም፡፡ ይህ አይነቱ እንቅስቃሴ በሌሎችም ክልሎች በተለይ የአማራውን ክልል እየመራ ባለው በአዴን ቢጠናከር ያኔ ወያኔን በቀላሉ አለሁ ሲል እናከስመዋለን፡፡ ግንቦት 7ንም ንቅናቄ ምናምን የሚሉትንም አንጠብቅም፡፡ በአዴን ከትግሬዎችና ለትግሬ ከሚያደሉ ግለሰቦች ሁሉ መጽዳት አለት፡፡

በተረፈ የምሰጣቸው አስተያየቶች የግሌ ቢሆኑም ብዙዎችን የሚያስማማ እንደሆነ ይገባኛል፡፡ በዛው ልክ በእኔ ሀሳብ ከልብ የማይሰማሙ ይኖራሉ፡፡ እነሱ መልካም አሳቢዎች ናቸው፡፡ የራሳቸውን አስተሳሰብ የሚከተሉ ናቸውና፡፡ በብዙ በምንሰጣቸው አስተያየቶችና መረጃዎች ግን ያላመኑበትን ስለተገዙ ብቻ ሊያጣጥሉ የሚሞክሩ አሉ፡፡ ከሚሰጡት አስተያየቶች እናያለን፡፡ እኔ ለሚሰጡ አስተያየቶች መልስ መስጠት አልፈልግም፡፡ አንድ እውነት ግን አለ መረጃ የሚያስፈልገውን በመረጃ ያመንኩበትን ደግሞ አመክኒዮዋዊ (ሎጂካል) በሆነ መልኩ በማብራራት ነው፡፡  እንደምሳሌ በቅርብ በሰጠሁት ሀሳቤ ሁለት አስተያየት ሰጭዎች ተችተዋል፡፡ መልካም፡፡ አንዱ እንደውም በኢትዮጵያ የተደበቀ አፓርታይድ የሚባል መጻፍ እንዳነብ ጋብዞኛል፡፡ ሲጀምር እንዲህ ያሉ መጻፎችን ለማንበብ ጊዜው የለኝም፡፡ ለእንደእኔ ያለው መጻፉ ከርዕሱ የተበላሸ ነው፡፡ አፓርታይድ የሚባል ቃል ብቻ ስለሰሙ በምናብ መድረስና እውነትኛ አፓርታይድ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደነበረ ማስረጃ ማቅረብ የተለያዩ ናቸው፡፡ እኔ ደግሞ ከልጅነቴ (ከወላጅ አባቴ) ጀምሮ ስለኢትዮጵያ ክፉውንም ደጉንም እየተማርኩ ያደግሁ ነኝ፡፡ ለእንደዚህ አይነት አስተያየቶች የማልጠቀማቸው የታሪክ ስህተቶች እንዳሉ ባውቅም ከነበረው በጎ ጥረቶች አንጻር ኢምንት የሚሆኑ ናቸው፡፡ በሌሎች አገሮች ተሰሩ ከሚባሉ ስህተቶች አንጻር ደግሞ ስናይ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ መሪዎችን እጅግ እናደንቀለን፡፡ በቀላሉ ዛሬ በጀርመናውያን እንደ ትልቅ  ባለውለታቸው የሚታሰበው ኦቶ ቢስማረክ አገርን አንድ ለማድረግ የወሰዳቸው እርምጃዎች የከፉ ነበሩ፡፡ ከዛም በኋላ  ገዥዎች በተራው ሕዝብ ላይ ትልቅ በደል ይፈጽማሉ፡፡ በዘርም አንዱን ከአንዱ በከፋ ሁኔታ ያበላልጡ ነበር፡፡ በጥቁሮች ላይ የሚደረገው የዘር መድልዖማ እስካሁንም አለ፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን በአገራቸው በዘራቸው ምክነያት አብዛኞቹ አልተገፉም፡፡ የዘር መገፋት የደረሰባቸው እንደሉ ዘንግቸው አደለም፡፡ ግን ኢትዮጵያን አንድ አድርገው በመሯት መሪዎች ይህ በደል አልነበረም፡፡ ኢትዮጵያን አንድ ያደረጉት ታላቁ ሚኒሊክ ደግሞ ከሌሎችም ኢትዮጵያዊ መሪ ሁሉ ለብዙዎች የተገፉ ሰዎች ነጻ መውጣት ምክነያት ነበሩ፡፡ ታሪኩ ዛሬ ስለሚኒሊክ ተጠልሽቶ እንደሚነገረን አደለም፡፡ በአለፉት 1000 ዓመት ሚኒሊክን የመሰለ መሪ በዓለም ላይ ተነሳ ከተባለ ከ ሁለትና ከሶስት አይበልጡም፡፡ ችግሩ በእጅ የያዙት ወርቅ ሆነና እኛን አልገባንም፡፡

 

ኢትዮጵያ እንደዛሬው በብሔረሰብ ሳትሸነሸን መሪዎች ይበልጥ ድጋፋቸው በአካባቢያቸው ነበር እንጂ በብሄረሰብ ማንነታቸው አልነበረም፡፡ ለዛም ነበር የሚኒሊክ ይበልጠው ሠራዊታቸው የሸዋ ኦሮሞ የነበረው፡፡ በእርግጥም እንዚህ መሪዎች ትውልዳቸውም ውስብስብ ያለ ነው፡፡ ራሳቸው ሚኒሊክ በእናታቸው በኩል ከጉራጌ አንደሚወለዱ ይነገር እንጂ ጥርት ብሎ ብሄር በዛ ዘመን ስለማይታወቅ አልተገለፀም፡፡ ራስ መኮንን (የኃይለሥላሴ አባት) ወልደመስቀል ጉዲና በግልጽ በአባታቸው ኦሮሞ እንደሆኑ እናያለን፡፡ ለእነዚህ ዘመን ሰዎች ትንሽ ሀይማኖት ገደብ ቢሆን እንጂ እንደዛሬው ብሄረሰብ የማንነት አጥር አልነበረም፡፡  መሪዎቹ ደግሞ ጋብቻቸውን ሆን ብለው ከሌላ ሕዝብ ጋር ማድረግ የተለመደ ነበር፡፡ አላማውም ሕዝብን ከሕዝብ ማስተሳሰር ነበርና፡፡ ዛሬ ያለው ትውልድ ይህን እንዲክድ ተደርጎ ያደገ ስለሆነ ባይረዳው አይገርምም፡፡ እና ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው አፓርታይድ እንግዲህ እንዴት በዛሬዎች ጸሀፊዎች እንደተፈጠረ ልብ ይበሉ፡፡

ይሄው በኢትዮጵያ ድብቅ አፓርታይድ ይሚለውን እንዳነብ የሚጋብዘኝ አስተያየት ሰጭ አንተ ስለ ዲንኤ የምታውቀው የለም ይላል፡፡ እኔ አኮ አውቃለሁ አላልኩም ነበር ያነበብኩትን ሰነድ ራሱን አጋራሁ እንጂ፡፡ በእርግጥም ስለምረዳው ነው ያነበብኩት፡፡ በሙያም ቢሆን ለዛ የምቀርኩ ነኝና፡፡  ማንም ሰው ቢሆን በአመነበትና በእውቀቱ ልክ መናገሩን እቀበላለሁ፡፡ ግን በማያውቁት ጉዳይ ሆን ብሎ ውዥንብር የሚፈጥርን ወይ ለሆድ ወይ ደግሞ ለሴር ስለሚሆን ሀሳቡን ፊት ለፊት መቃወመን እመርጣለሁ፡፡ ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ የሚባል ቀልድ እዚህ ጋር አይሰራም፡፡ የአገርርና የሕዝብ ጉዳይ ሰጥቶ መቀበል በሚል ስሌት የሚታሰብ አደለም፡፡

አመሰግናለሁ!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ

አሜን!

ሰርጸ ደስታ
0