June 28 at 1:12am

የሕወሐት የመጨረሻው መጀመሪያ የማፍረስ አጀንዳ ይከሽፋል

እንዲህ ይጀምራል። ታላቋ እና ገናና የነበረችው United Soviet Socialist Republic (USSR) አለምን ከምእራቡ እኩል ተካፍላ በሀያልነት ለ50 አመታት ገዝታለች። አለምን የኒውክለር ጦርነት ስጋት ላይ ያስቀመጣት እና ለሀምሳ አመታት የዘለቀው ጦርነት (The Cold War) የቀዝቃዛው ጦርነት ማለት ነው ለመከሰት የቻለው አለም በሁለት በአይዲዮሎጅ ልዩነት ባላቸው አገራት እኩል የኃይል አሰላለፍ ስር በመውደቋ ነበር። ሆኖም ምእራባውያኑ ከፊት ለፊቱ ፍጥጫ ጀርባም ወጣት ልጆችን አስልጥነው እና ኮትኩተው በማሳደግ የኋላ ኋላ የሃያሏን ተፎካካሪያቸውን የስልጣን ማማ ለመያዝ በቅተዋል። እናም የተባበሩት የሶቪየት ሶሻሊስት ሪፖብሊክ በትንሽ ስህተት ከምድር ገጽ ጠፍተው በቅስፈት የተለያዩ በጣም ብዙ አገራት ሆነው አረፉት። ዛሬ የተከበሩ ብዙ የሩስያን ነገስታትን ለታላቋ ሩሲያ ያበረከቱት ጆርጅያ እና ዩክሬን ሳይቀር ከአባት አገር ተለይተው ከዚህ ግቡ የማይባሉ ድኩማን መንግስታት ሆነው አርፈውታል። ለሶቪየት መፍረስ ዋናው ኃይል የውጩ ሳይሆን የውስጥ አገር ጠል መሪወች ለመሆናቸው በእድሚያችን አይተናል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ተዋልዶ እና ተከባብሮ እዚህ ደርሷል። ይህን ጠንካራ ትስሥር ለማፍረስ ሕወሐት ለአለፉት 26 አመታት ያላደረገችው አልነበረም። ከበደኖ እስከ ጉራ ፈርዳ እና መተከል የተሞከረው ሕዝብን የማጋጨት፣ የማፈናቀል፣ ዜጎችን አገር አልባ የማድረጉ ሁሉ የትልቁ አጀንዳ አንድ አካል ነበር። ያም ሆኖ ዜጎች እንደ ርዋንዳ እና ቡሩንዲ ቆንጨራ ይዘው አልተራረዱም። ይልቁንም የዚህችን ጠባብ እና ዘረኛ ክፉ ስራን እየሞቱም፣ እየተሰቃዩ እና ባገራቸው እየተሰደዱ/እየተሳደዱም አክሽፈውታል። በሃረማያ፣ በአዲስ አበባ፣ በባሕር ዳር፣ በመቀሌ ዩኒቨርስቲወች ያልተሞከረ አንዱን ዘር ከሌላው ለማጋጨት ሙከራ አልነበረም። ሁሉም የሕወሀትን ዘላቂ አጀንዳ አላሳካም። አክሽፎታል። ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ዛሬ የመጨረሻ በሚመስል ሌላ የጥላቻ ካርታዋን ስባለች። ይህ ሕዝብ ተቀምጦ እና መክሮ የሚተገብረውን በአዋጅ ብጤ ይህን ሰራሁ እናም እናንተ እርስ በእርሳችሁ ተባሉ ለማለት ሞከረች። ሕወሐት ከዚህ ቀደምም አገር በዘር ሸንሽና ፌደራሊዝም ሰጠኋችሁ ትበል እንጅ፤ ስልጣኑን ከእርሷ ፈልቅቆ ያወጣ እናዳልንበር 26ቱ የመከራ አመታት ዋቢ ምስክራችን ነው። ኢትዮጵያ በአለም ካሉት ሀገራት ሁሉ የላቀ እና የመጠቀ ስልጡን ሕዝብ ያላት፣ የአኩሪ ታሪክ ባለቤት፣ ክቡር የሆነ ባህል ያለው ሕዝብ አገር ናት። ይህችን ሀገር ቱርኮች፣ ደርቡሾች፣ ግብጾች፣ እንግሊዞች፣ ጣሊያኖች ሞክረዋታል። አልፈው ተርፈው እና ተባብረው እና ተጋግዘውም ከምድር ገጽ ለማጥፋት ከጅለው ተዋርደውባታል። ይህ ኩሩ እና የሰለጠነ ሕዝብ ግን ለሁሉም ሳይንበረከክ ማንነቱን እና ክብሩን ጠብቆ እዚህ ደርሷል። ዛሬም አይቀበሉ ፍዳ እያሸከሙትም የሕወሐትን አጀንዳ አክ እንትፍ አለው እንጅ አልተገበረውም።
ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ሕወሐት ይህ ዛሬ በአዋጅ ያወጣችው ቧልቷ የተጻፈበት ቀለም ሳይደርቅ ሕዝብ አይንህ ካፈር እዳለው ሁሉ። የሀገሪቱን ምሰሶ የሆኑትን ሁለት ዘሮችን ለማጋጨት የተሞከረው አገርን አጥፍቶ ወደትግራይ የሚል ሀሳብ ተይዞ እንደሆነ ግልጽ ነው። የሕወሀት ደናቁርት ያላወቁት ቢኖር ኢትዮጵያ ፈርሳ ትግራይን በፍራሿ ላይ እንገነባለን የሚለው ስራን እና ተሀስቦትን ሌላው ቢቀር የትግራይ ሕዝብ የሚቀበለው እንዳልሆነ መረዳት ይገባል። ኢትዮጵያ ስትፈርስ ሁሉም ፈራሽ ነው እና። እንዲህ ባለ ሰይጣናዊ ስራ አገርን እና ሕዝብን ያህል ክቡር የሆነን ለሙከራ ማቅረብ በመሬትም ሆነ በየትኛውም አለም ተቀባይ ያጣ እርግማን ነው የሚሆነው።

በነገራችን ላይ የሕወሐት መሪወች ነገር ሲጠብ የሚጠቀሙበት ቃል አለ እርሱም Interahamwe ነው። ብዙ ወገኖች ይህን ቃል ላያውቁት ይችላሉ። ቃሉ የተወሰደው ከርዋንዳ ሲሆን የርዋንዳን ፍጅት በግንባር የመራ ተቋም ነው። ይህ ተቋም መራሂ ሁቱ የሆነው መንግስት በሩዋንዳ በነበረበት ወቅት የመንግስ paramilitary group (militia group) ነበር። ሕወሐት ግን ከከተማ ሰላማዊ ነዋሪ መሀል የእኔ ዘር ነው የምትለውን ሳይቀር እያስታጠቀች ሌላውን የሌለ ስውር ወታደራዊ ሀይል ዘርን ለይቶ ሊያጠፋ የተዘጋጀ እንዳለ በማስመስል መሪወቿ ሕዝባዊ ንቅናቄ በጋለ ቁጥር ቃሉን ይጠቀማሉ። በእርግጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኦሮሞ ዜጋ እስከ አማራው ጎንደር እና ጎጃም በ Interahamwe (አጋዚ) ጦር ተጨፍጭፏል።

የሕወሐት ጠባብ እና ደንቆሮ መሪወች ያውቁት ዘንድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት 50 አመታት ያደረገው ተጋድሎ ለአንድ ዘር የበላይነት፣ ለሌላው ወገን የበታች የማድረግ አላማ ኖሮት ሳይሆን የተሻለች፣ እኩልነት እና ዴሞክራሲ ሰላም እና የህግ የበላይነት የተከበረባት ሀገር ለማድረግ ነው። የሕወሀት አዋጅ ሕዝብን አባልቶ አንባ ገነንነትን የማጠናከር አለያም የጀመሯትን እና ያፈረሷትን አገር እሳት ጭሮ ዶጋ አመድ አድርጎ የመሄድ ከሆነ አሁን ደግመን እና ተደጋግሞ ሊነገር የሚገባው ያላዋቂ ስራ እራስን ለማጥፋት የመጨረሻ ቢባል ጥሩ ስያሜ ይሆናል።

በሕወሐት መቃብር ኢትዮጵያ ታብባለች!!!

ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረገው ማንኛውንም ሕወሐታዊ እርኩስ መንፈስ ሊወገዝ ይገባል!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

መንግስቱ ሙሴ