ክፍል አንድ

ታምራት ይግዙ

” አሜሪካ ያላቹሁ ኑ ጠላ ቅመሱ
አፍሪካም ያላቹሁ ኑ ጠላ ቅመሱ
እንድ ሻላቃ ዳዊት እንድትጠነስሱ
አውሮፓ ያላቹሁ ኑ ጠላ ቅመሱ
ኢሲያና አውስትራሊያም ያላቹሁ ኑ ጠላ ቅመሱ
እንደ መምህሩ እንደ ጌታቸውም  እንድትጠነስሱ

እንደሚታወቀው ሁሉ የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነትን ከጠነሰሱት ግምባር ቀደም ግለሰቦች ውስጥ ፕ/ር ጌታቸው እና ሻለቃ ዻዊት መሆናቸውን እነርሱ በተጋበዙበት የሚዲያ አውታርም ሆነ ህዝባዊ ስብሰባላይ እየተገኙ ስለ አገራዊው ንቅናቄ አስፈላጊነት አበክረው ሲናገሩ ተደምጠዋል:: በሌላ በኩል ደሞ በአገራዊ ንቅናቄ ውስጥ ያሉት የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች እና በቶሮንቶ ህዝባዊ ስብሰባዎችን አካሂደዋል::  የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ የሲያትሉን በመግናኛ ቡዙህን አማካኝነት የተከታተለ  ሲሆን የቶሮንቶውን በአካል በመግኘት ተከታትሎታል: ከመከታተልም አልፎ ጥያቄም ለመጠየቅ ሰልፍም ይዞ ነበር:: ተቀምጦ ይከታተል  የነበረው ስብሰባ ለጥያቄ ተነስቶ ከአምስት እስከ አስር  ደቂቃ በቆመበት ቦታ የተመለከተውን  የተስብሳቢው ሁኔታ በመመልከት ያሰበውን ጥያቄ ሳይጠይቅ እንድቀመጥ አድርጎታል:: : ምክንያቱም ለጥያቄ በሚቆምበት ስፍራ ያሉ ወንድሞች ከነ ፕ/ር ብርሃኑ ከነ ዶ/ር በያና እና ከዶ/ር  ኮንታ አንደበት የሚወጣውን ፖለቲካዊ ንግግር በማድመጥ ግማሹ በተቀመጡበት ውንበር ላይ ሆነው በስሜት ቁጭ ብድግ ሲሉ: አንዳንዶቹ ፉጨት ሲያፎጩ: ሌሎቹ ደሞ በጣም ከመደሰታቸው የተነሳ ግንባራቸው ላይ ያለው ወዝ ያብረቀርቅ ነበር::  ይህ በእንዲህ እያለ ፕ/ር ብርሃኑ በ2012ዓ/ም ላይ ተመስርቶ የነበርው ጥምረት የሚባለው ስብስብና በ2017 የተመሰረትው የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ልዩነቱ በይዘት ነው ወይስ በቅርጽ ብሎ መጠየቅ አሊያም? ፕ/ር ብርሃኑ ወያኔን አሳንሶ የማየት ባህሪያቸውን በተመለከተና ከዚህ በፊት የወያኔ ባለስልጣናቶችን  የሰፈር ዱሪዪዎች; የወያኔ መሪዎች የሰፈር ጎረምሶች ብሎ መጥራት   እውነት ከልቦህ ነው ብሎ መጠየቅ?::  ሌላው ደሞ የገንዘብ ነገር ሲነሳ ፕ/ር ብርሃኑ ድርጅታቸው አርብርኞች ግንቦት ሰባት ከማንም ሰው እንደሚቀበል ከሰው አይደለም ቀንድ ካለው ሴጣንም ቢሆን እንደሚቀበል በልበ ሙልነት ሲናገሩ ይህ አነጋገሮት ከምሮት ነው? ብሎ ጠይቆ  በደስታ ውስጥ ያሉትን እድምተኛ ወንድሞችን ከማሳዝን ይልቅ በማለት ነው ጥያቄ ከመጠየቅ እራሱን የገታው ::

 

  • ሌላው ጥያቄ ደሞ ለዶ/ር በያን ነበር ዶ/ር ቢያና በሲያትል በተደረገው ስብሰባ ላይ ሲናገሩ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ለአኦሮሞው; ለአማራው; ለደቡቡ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያ ከዛም አልፎ ለአፍሪካ ክዛም ከፍ ሲል ለዓለም ሁሉ ሲሉ ተደምጠዋል:: እውነት ይህንን ሲሉን ሒሊነቸው ያመነበትን ልባቸው የተቀበለውን ነው አንደበታቸው የሚናገረው ለማለትም ነበር የተነሳሁት::

 

  • በሌላ በኩል ደሞ ዶ/ር ኮንቴ በሲያትል ንግግራቸው “ሰለ ባህር እና ሰለ አሳዎች” ተናግረው ተሰብሳቢውን አይደለም እኔንም አድማጩን ከለሁበት ሆኜ አስቆኛል:: የኔ ጥያቄ ለዶ/ር ኮንታ  እርሳቸው ከየትኛው ናቸው ከባህሩ ወይስ ከአሳዎቹ?

ይህንን ከላይ የጠቀስኩትን ጥያቄዎች ለምን ለመጠየቅ እንደተነሳሳው እንደሚከተለው አቀርባለው::

በ2012 ዓ/ም የተቆቆመው ጥምርትና በ2017 ዓ/ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ልዩነቱ በይዘት ነው ወይስ በቅርጽ? የሚለውን ስመለከተው ቡዙም ልዩነት አላየሁበትም  ለምሳሌ በ2012 ዓ/ም ጥምረትን የመሰረቱት ድርጅቶች

1ኛ በዶ/ር ብርሃኑ ይመራ የነበረው ግንቦት7 2ኛ በአቶ ነዓምን ዘለቀ ይመራ የነበረው ድርጅት 3ኛ በአቶ አሎ ይመራ የነበረው የአፋር ህዝብ ንቅናቄና 4ኛ በጀ/ል ከማል ገልጁ ይመራ የነበረው  የኦሮሞ ድርጅት ጥምረት ውስጥ ገብቶ ለመስራት በሂደት ላይ የነበር ሲሆን::   የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄን የመሰሩት ድርጅቶች ደሞ የሚከተሉት ናቸው::

1ኛ በፕ/ር ብርሃኑ የሚመራው ያርበኞች ግንቦት7  2ኛ በዶ/ር ሌንጮ የሚመራው የአኦሮሞ ዲሞክራት ፌደሪሽን 3ኛ በዶ/ር ኮንቴ የሚመራው የአፋር ህዝብ ንቅናቄና  4ኛ የሲዳማ ህዝብ ንቅናቄ (የሲዳማ ህዝብ ንቅናቄ ተወካይ በቶሮንቶ ስብሰባ ላይ በአካል ያልተገኙ ሲሆን አርማቸውን ግን ልከዋል) እንግዲህ ይህንን የሁለቱን ስብስብ ስመለከተው   በ2012 ዓ/ም የተቆቆመው ጥምርትና በ2017 ዓ/ም ከተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ልዩነቱ ጥምረትን ከመሰረቱት ውስጥ የአቶ ነአምን ድርጅት  በ2017 ዓ/ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ውስጥ አለመካተቱ ሲሆን ምክንያት ሊሆን የሚችለው በአሁኑ ሰዓት አቶ ነዓምን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር በመሆናቸው  ነው::   በ2012 ዓ/ም የተቆቆመው ጥምርት ውስጥ የሌለው  በ2017 ዓ/ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ውስጥ ያለው የሲዳማ ህዝብ ንቅናቄ ሲሆን የኔ ፍራቻ የሲዳማ ህዝብ ንቅናቄን የሚመሩት አቶ ኤፍሬም ማንዴቦ እንዳይሆኑ ነው :: ይህን ያልኩበት ምክንያት” እንሰት የሚለውን ዊብ ሳይት ለተከታተለ ሰው ግምቱን ከፍ ያረግበታል”

ይህ ሆኖ ከተገኘ ደሞ አንዱ የግንቦት ሰባት አባል በበር ሲወጣ ሌላው የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባል የሆነው ግለሰብ አይኑን በጨው አጥቦ በመስኮት መግባቱ ብቻ ነው;;  አልያም በአዲስ ዓምት ንጋት ላይ እናቶቻችን ” የገንፎ ምንቸት ውጣ የጎመን ምንቸት ግባ” እንደሚሉት መሆኑ ነው::  ይህ ለምን እንዲሆን ተፈለገ ቢባል ቡዙ ምርምርና ጥናት አሊያም የፖለቲካ ሳይንስ ሊቅ መሆን አያስፈልገውም ያው አርበኞች ግንቦት ሰባትን አውራ ድርጅት አድርጎ የማውጣት አቤዜ ውስጥ እንዳለን የሚጠቁም ነው:: እውን እኛ ኢትዮጵያውያን የአውራ ድርጅትን መጥፎነት ከወያኔ አልተማርንም ማለት ነው ወይስ !? እዚህ ላይ እኔን የሚያሳስበኝ ነገር  ቡዙዎቻችን ፍርሃትን ፈርተን መኖር ከጀመርን አመታት ያስቆጠርን ስለሆነ ፊት ለፊት የመናገር ብቃታችንን ፍርሃታችን ስለተቆጣጠርው የወጣልን ፈሪዎች ሆነናል  ብል ከእውነት የራኩ አይመስለኝም::  በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳዝነው ፍርሃትን  እየፈራነው  እኛን ኢትዮጵያውያንን በየእለቱ ወንጀል እየሰራን እንገኛለን በፈራን ቁጥር ወንጀላችን እየበዛ ይሄዳል: ወንጀላችን በበዛ ቁጥር ደሞ የአገራችን እጣ ፋንታ ከድጡ ወደ ማጡ እየሆነ እንደሚገኝ ምስክር መጥራት አያስፈልገውም::  ፍረሃት ወንጀለኛ እንደሚያደርግ ቡዙ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል እስቲ አንድ ሁለቱን ጠቅሼ ልለፍ::  የምናገረው በግልጽ ነው፤ ይሉኝታና ፍርሃት  መጥፎ መሆኑን ከሂደት እና ከእድሜ እየተማርኩ ነው፡፡ በትንሽ በትልቁ መኮራረፍና የሸሚዝን እጄታ መሰብሰብ ባህል በሆነባት ሀገር  ውስጥ ለተወለድን ህብረተሰቦች ሃሳብን እንደወረደ ማቅረብ ቁም ስቅል እንደሚያስከትል ብረዳም ምርጫ የለኝም፡፡

ፍርሃት ወንጀለኛ እንደሚያደርግ ማስረጃ ከሚሆኑኝ ውስጥ ፕ/ር ብርሃነ ነጋ አንዱ ናቸው:  ሁላችንም እንደምናውቀው  ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን ሕወሃት ፍርድ  ቤት ከአንድም ሁለት ግዜ ይሙት በቃ የተፈረደባቸው ኢትዮጵያዊ ናቸው: እወነት በፕ/ር ብርሃነ ነጋ ላይ ይሙት በቃ የፈረዱባቸው ዳኛ በፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ላይ ያንን ፍርድ የፈረዱት ጥፋት አግኝቶውባቸው ነው? እኔ እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ነገር ቢኖር  ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለአንድ ደቂቃ ፍርድ ቤት ችሎት ላይ የሚያስቆም ጥፋት የለባቸውም ባይ ነኝ:: ታዴያ እኛ የተከበሩ ዳኛ እንዴት ነው በፕ/ር ብርሃነ ነጋ ላይ ይሙት በቃ የፈረዱባቸው ስል መልሱ ከፈርሃትታቸው የተነሳ ብቻ ነው ባይ ነኝ::እኝህ የተከበሩ ዳኛ  የፈሩት ከስራቸው እንዳይባረሩ ሊሆን ይችላል አሊያም ከድርጅት አባልነታቸው ወ.ዘ.ተ ብቻ ከፍርሃታቸው የተነሳ ይሙት በቃ ፈረዱ ይህ ፍርሃታቸው እኝህን ዳኛ ምን አደረጋቸው? ወንጀለኛ:: ወንጀለኝነታቸው በሀገርም ; በህዝብም; በሒሊነቸውም::  ሌላው ደሞ በፍርሃት ወንጀል እየተሰራ ነው የምለው በነጻ አገር እየኖርን አርብርኞች ግንቦት ሰባት ህዝባዊ ስብሰባ በጠራ ቁጥር የመጀመሪያው ማስጠንቀቅያው  የራሳችን ድምጽና ምስል ቀራጭ ስላለ ድምጽም ሆነ ምስል መቅረጽ አይቻልም   የሚሉት ማሳሰቢያ ነው :: ይህን ማሳሰቢያ በተጠሩ ስብሰባዎች ሁሉ   ተደጋግሞ የሰማነው ሲሆን በ June 3/2017 ደሞ ሊቀመንበሩ ፕ/ር ብርሀኑ ባሉበት ማስነገር በነጻው አገር እየኖሩ  ፍርሃትን በጀርባቸው ትሸክመዋት እንደሚዞሩ  ያመለክታል::  ከዚህ ፍርሃታቸው የተነሳ ድምጽና ምስል ቀራጭ ስላለ ድምጽም ሆነ ምስል መቅረጽ አይቻልም በማለት  ወንጀል እየሰሩ ነው ማለት ነው :: የሚገርመው የግንቦት ሰባት አመራሮች ሰባዊ መብትን; የመናገር ነጻነትንና ዲሞክራሲን ለማስከበር “ከኛ ወዲያ ላሳር” ባዮች ሆነው ሳለ:  ከተግባራቸው እንደምንረዳው ግን እነዚህ የግንቦት ሰባት አበላቶች የመናገር ነጻነትንና ዲሞክራሲን ከሕወሃት ባላነሰ ሁኔታ እየተፈታተኑት እንደሚገኙ ነው::  ለምን ብንል ከፈረሃታቸው  የተነሳ ::  የግንቦት ሰባት ፍርሃት ደሞ “ግመል ሰርቆ አጎንብሶ” መሆኑ ነው የሚገርመው::  በላያችን ላይ ስላለው ፍርሃት ከመጨሬሴ በፊት አገራችንን ኢትዮጵያን ከሕወሃት ነጻ ልናወጣ የምንችለው መጀመሪያ ሁላችንም “ፍርሃትን መፍራት ስናቆም ብቻ ነው” የሚል አቆም ሁላችንም መያዝ ያለብን ይመስለኛል:  ይህ ካልሆነ ግን………..!?

ሲወለድ ያጠለቀውን

ሲሞት አወለቀው

ይህን የአባቶች አባባል ያስታወሱኝ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው ምክንያቱም ግንቦት 7 ከመሰረቱበት ግዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የወያኔ መሪዎች የሰፈር ዱሪዪዎች ነቸው; የወያኔ መሪዎች የሰፈር ጎረምሶች ናቸው;ሲሉን ኖረው   በ June 3, 2017 ስብሰባ ላይ ደሞ የወያኔ መሪዎች የሰፈር ጢቦዎች ነቸው በማለት ሲናገሩ ተደምጠዋል: እውነት ለወያኔ መውሪዎች ይህ ስም ይመጥናቸዋል? እውነት የወያኔ መሪዎች ከጣሊያኑ ማፍያ የሚበልጡ እንጂ የሚያንሱ ሆነው ነው በሰፈር ጢቦ ያስመሰላቸው::  እነዚህ የህወሓት መሪዎች በሃገራችን በኢትዮጵያ ላይና በህዝቦቾ ላይ ያደረሱት ግፍና መከራ ይቅርና በፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በመሰረቱትና ላለፈው ስምንት ዓመታት በመሩት ድርጅት በግንቦት 7 ላይ ያደረሱትን መጥፎ ተግባር ሰፈር ጢቦዎች ተርታ ያስመድባል::  በእኔ እይታ አንኮን ሶስት አንኮር ነገሮች ሳቀርብ   የህወሓት መሪዎች የሰፈር ዱሪዪዎች;የሰፈር ጎረምሶችና; የሰፈር ጢቦዎች አለሞሆናቸውን ያሳብቃል::

ይኽውም የግንቦት ሰባት አመራሮች በሰሩት ስህተት 1ኛ በ2010 ዓ/ም የግንቦት ሰባት በመባል የታሰሩት ጀነራሎች እና ግለሰቦች 2ኛ በ2013 ዓ/ም በራሳቸው በፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ይመራ የነበረው የስልክ ስብሰባ ( Tel-confers) ተጠልፎ በመገናኛ ቡዝሃን የተሰራጨባቸውና በላፈው ደሞ የድርጅታቸው ቀኝ እጅ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሌላ አገር ማገት ነቸው:: ታዲያ በምን ሚዛን ቢለኮቸው  ነው ፕ/ር ብርሃነ  የህወሓት  መሪዎች የሰፈር ዱሪዪዎች;የሰፈር ጎረምሶችና; የሰፈር ጢቦዎች የሚሎቸው? በሌላ በኩል ህወሓትን ብንመለከተው  በበርሃ እያለ ጠላቱን ንቆ አያውቅም: ኢሕአፓን ለመበተን በርትቶ የሰራ; ኢዲዩን ለማጥፋት ተግቶ የደከም; ኦነግንም ጭዳ ያደረግ ነው::  በእኔ አመለካከት ፕ/ር ብርሃኑ ስለወያኔ ያላቸው አመለካከት መለውጥ ያለበትና ተስብሳቢውም ህብረተሰብ ማዳመጥ የሚፈልገውን ማወቅ የሚገባቸው ይመስለኛል:: ታዳሚው ንግግራቸውን በጽሞና አዳመጠ ማለት አባባላቸው በሙሉ ትክክል ነው ብሎ ተቀበለ አይደለም: ወደ ፊትም እርሳቸው ያሉበትን የስልጣን እርክርን የሚመጥንና ታዳሚውንም ግምት ውስጥ ያስገባ ንግግር ይጠበቅባቸዋል::  ሌላው ደሞ እንዳለመታደል ሆኖ ስድብና ዘለፋ የምናበዛ ሰዎች ሞልተናል፡፡ ይህም የአሸናፊነት ሳይሆን የተሸናፊነት ምልክት ነው፡፡ ዘለፋ፣ ስድብ፣ ዛቻና ፉከራ የሚቀናው ሰው ሊያደርግ በሚያስበውና ሊያደርግ በሚችለው መካከል ያለው ክፍተት የሚፈጥርበት የአቅም እና የአመራር ውስንነት የሚያንገላታው አሳዛኝ ፍጡር ነው ብል ማጋነን አይመስለኝም፡፡  ካልተሳሳትኩ የግንቦት ሰባት ከፈተኛ አመራሮች ከፕሮፖጋንዳ ውጪ ሕወሃት የሚፈታተን አቅም የገነቡ አይመስለኝም ምክንያቱም ድርጅታቸው ሕወሃት አሳንሶ ማየትና አቅመቢሲ አድርጎ መቁጠርን እንደ አሸናፊነት የቆጠረው ይመስላል:: ይህን ዓይነት አመለካከት ይዞ አንድ እርምጃ መሄድ እንደማይችሉ ከወዲሁ መግንዘብ ያለባቸው ይመስለኛል ሌላው ደሞ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲሉ ጋሪውን ከፈረሱ ማስቀደሙ ክጥቅሙ ጉዳቱ እያመዘነ ስለሆነ  ሊያስቡበት ይገባል ባይ ነኝ::

 

የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም

ይህንን  አባባል በተለያየ ግዜ እንዳስታውስ ያደረጉኝ ፕ/ር ብርሃኑ ናቸው ይህውም የገንዘብ ነገር ሲነሳ ፕ/ር ብርሃኑ ድርጅታቸው አርብርኞች ግንቦት ሰባት ከማንም ሰው እንደሚቀበል ከሰው አይደለም ቀንድ ካለው ሴጣንም ቢሆን እንደሚቀበል በልበ ሙልነት ሲናገሩ ተደምጠዋል ይህንን በተመለከት ወደፊት እመለስበታለው

አሁን ያለው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ውጪ አገር ከሚንቀሳቀስት 

የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ አውራ ሆኖ ወጥቶ የሚመራው ድርጅት ያስፈልገዋልን?

አውራ የሚለው ስም ሲነሳ የህወሓት አገር አጢፊነትና; የሻቢያ መሰሪ ተንኮል በሒሊነው የማይመላለስ ኢትዮጵያዊ ይኖር ይሆን”? አውራ ሆኖ ለመውጣት ያሰበ ድርጅት ማን ይሆን? ይህንን ጥያቄ ያነሳሁበት ምክንያት የተለያዩ ወንድሞች  በድርጅት ጉዳይ ሳያወሩ  የሰማሁት ፍንጭ አለ እሱም በዊጪ አገር ከሚገኙት ድርጅቶች ውስጥ አንዱን አውራ ድርጅት አድርጎ የማውጣት ተልኮ ነው:: ይኽውም ቀደም ብሎ በነበሩ አመታቶች በተለያዩ ሙህራኖች ታስቦ የነበረና የተጠነሰሰ  ጉዳይ ለማሳካት በ2015ዓ/ም በቭዥን ኢትዮጵያ ስም ስብሰባ የጠሩት  ግለሰቦች እና ስብስቦች   የአውራ ድርጅት የማውጣት ጉዳይ ላይ ደፋ ቀና ሲሉ መክረማቸው አካሄዳቸውን በጥሞና ለተከታተል ሰው ለማወቅ የሚከብድ አይደለም:: እነዚህን ታዋቂ ግለሰቦች እና ታዋቂ ሙህራኖችን መጠየቅ የምፈልገው ነገር ቢኖር ስለ እውነት ብለን ስለሀገር ጉዳይ እንወያይ ከተባለ ሃገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ውጪ ካሉ ድርጅቶች ውስጥ አውራ ሆኖ ወጥቶ እኔ አውቅልሻለው የሚላት የፖለቲካ ድርጅት ያስፈልጋታልን? ይህንን ጥያቄ ታዋቂ ግለሰቦችና ታዋቂ ሙህራኖችን እንዲመልሱልኝ በአክብሮት እጠይቃለው በተለይ የተከበሩ ፕ/ር ጌታቸው በጋሻው እና የተከበሩ ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊ::

ይህንን የአወራ ድርጅት የማውጣት ጉዳይ ከአንድ ወንድም ጋር ሳወራ እንዴህ ብሎኝ ነበር ” በአሁኑ ሰዓት ውጪ ካሉ ድርጅቶች ውስጥ አንድ አውራ ድርጅት ሆኖ የሚወጣ ያስፈልጋል አለኝ”

እኔም ስመልስለት አይ ወንድሜ የአወራ ድርጅትን መጥፎነት ከህወሓት የተማርን ይመስለኛል ህወሓት ለ25 ዓመት  አገራችንን ከድጡ ወደ ማጡ ሲከታት እያየን እንዴት ነው ስለ አውራ ድርጅት የምታወራኝ ስለው የመለሰለኘን እዲህ በማለት ነበር

” አይ አንተ ሰው ከአሁን ቦሃላ ማን መጣ ማን  የኢትዮጵይ ህዝብ የሚታለል አይለም አለኝ”

ለዚህም ስመልስለት አይ የኔ ወንድም የኢትዮጵያ ህዝብ ከ2005 ዓ/ም ቦሃላ ተታሎ አያቅም ያለበት ችግር የአቅም ችግር ነው አቅም ስለሌለው ነው እንጂ ሕወሃት እየገዛው ያለው ተታሎ እይደለም::  እንደምናየው አቅም አለኝ ብሎ ሲነሳ የሕወሃት አቅም አይሎ በመነሳት የተቀጣጠለውን ሰላማዊ ትግል በመቶዎች የሚቆጠሩትን  በመረሸን በሺዎችየሚቆጠሩትን በየጣቢያው በማጎር   ትግሉን ያኮላሸዋል እውነት እኛ በውጪው  አለም የምንገኝ ኢትዮጵያኖች የሃገራችንን ህዝብ የስልጣን ባሌቤት የማድረግ ህልምና ምኞት ካለን የአገር ቤትን ትግል በገንዘብ; በእውቀትና በጉልበት ከመርዳት ውጪ አውራ ድርጅት ለመፍጠር ጎንበስ ቀና ማለቱ አባቶች እንደሚሉት ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ ነውብዪ ስመልስለት እሱ የሚያስበውን የአውራ ድርጅት ቀፍቅፎ ማውጣት  ስላልተቀበልኩት አርእስት ለውጠን ሌላ ወሬ ጀመርን::

በስያትል ከተማ የተካሄደው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ጉባዔ እድምታው ይቀጥላል