34ኛው የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል ሰሜን አሜሪካ ፌስቲቫል እሁድ ማምሻው ላይ በሲያትል በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ:: በመክፈቻው ስነ ስርዓት ላይ ከምን ግዜውም የበለጠ ቁጥር ያለው አኢትዮጵያዊ ስብሰብ የታየ ሲሆን- ሜዳው በኢትዮጵያ ባንድራ አሸብርቆ ነበር:: በእለቱ ልዩ ልዩ ለአይን የሚማርኩ ትርኢቶች የታዩ ሲሆን ከሲያትል ማዘጋጃ እና ከኡበር የመጡትን ጭምሮ በርካታ የክብር እንግዶች ስለ ዝግጅቱ ንግግር አድርገዋል::