July 4, 2017

1~ ታሪክ ምን ይላል?

ታላቁ የፍልስፍና ራስ ሶቅራጠስ ከሺህ አመታት በፊት “እኔ የማውቀው አለማወቄን ነው” በማለት አለማወቅን ለማወቅ የሚታትር የብርቱ ሰብዕና ባለቤት እንደሆነ አስተምሮን አልፏል።
የኦሮሞ አንዳንድ ልሂቃንን ስመለከት እንደው የማያውቁትን ለመናገርና ለመፃፍ ድፍረታቸውና መጣደፋቸውን ስመለከት ሶቅጥራስን ዘልዬ ” አለማወቅ ደፋር ያደርጋል” የሚሉት ሃበሻዊ ብሂል ትክክል ነው እላለሁኝ ።

ይሄ ፅሁፍ የአድስ አበባ ጉዳይን ከታሪክ አንፃርና ከህግ አንፃር ለመዳሰስ ይሞክራል ። የዚህ ፅሁፍ መነሻው ደሞ ታሪክንና ህግን ለራሳቸው የፖለቲካ ፍጆታ የሚያውሉ ሳያውቁ የሚያውቁ የሚመስሉ የኦሮሞ ልሂቃን እንደ አሸን እየተፈለፈሉና ብዙውን ሰው እያወናበዱ ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ አንዳንድ ነገሮችን ለመዳሰስ ነው ።
መጀመሪያ በታሪክ ጉዳይ ላይ ትንሽ ልበልና ወደ ህጉ ጉዳይ እመለስበታለሁኝ።

ከሁለት ቀን በፊት የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚኒኬሽን ሚ/ር ነገሪ ሌንጮ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በአገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ
<<ኦሮሞ በአዲስ አበባ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም የሚደነግገው አዋጅ ለማርቀቅ አስፈላጊ የሆነበት አንዱ ምክንያት ያለፉ የታዘቡ ታሪኮችን ለማስተካከል ሲባል ነው> > የሚል አስገራሚ አረፍተ ነገር ጣል አድርገዋል ።
አቶ ነገሪ ሌንጮ በአለማወቅ ይሁን በድፍረት ከአንድ ሚኒስትር የማይጠበቅ አረፍተ ነገር ከአፋቸው አፈትሎኮ አምልጧቸዋል ።

ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ ማወቅ ያለባቸው ነገር የታዛባ ታሪክ የሚስተካከለው ከታሪኩ ከመሰረቱ በመነሳት ነው እንጅ ታሪክን ከወገቡ በመጀመር አይደለም ። ዶክተር ሌንጮ የግዛት ባለቤትነትን ለማመልከት ታሪክን ጠቅሰዋልና መራራውን ሀቅ ይውጡት ዘንድ ታሪካዊ መሰረቱን ማሳየት አለብን ።
ኦሮሞዎች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ማስረጃን ሲጠቅሱ ወደ ኋላ መቶ አመታትን ብቻ መሄድ ይፈልጋሉ ። ከመቶ አመታት ገፋ ካደረጉ ቅርቃር ውስጥ እንደሚገቡ ያውቋታል። ታሪክ የባለቤትነት ማስረጃ ሆኖ የሚቀርብ ከሆነ መቶ አመታት ብቻ መጓዙ እርባና የለውም ከዛም በፊት ተጉዞ የ300 እና የ400 አመታትን ታሪክ ማጣቀስ አስፈላጊ እና ግደታም ነው።

አዲስአበባንና ሌሎች ቦታወችን ባለቤት ነኝ ለማለት ታሪክ እንደ ማስረጃ ከተጠቀሰ ኦሮሞዎች ከቤናድር ከመነሳታቸው በፊትና ወላቡ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት ዛሬ የሰፈሩባቸው ቦታዎች ሁሉ በአማሮችና በሌሎች ነባር ህዝቦች የተያዘ ምድር ነበር ።
ኦሮሞዎች እኮ እስከ 1520 ድረስ ለአገሩም እንግዳ ለሰውም ባዳ ነበሩ ። የ 16ኛው ክፍለ ዘመነ የጋላ ወረራ እና ነባር ህዝቦችን የማፈናቀሉ የማፈራረሱ አሰከፊ ታሪክ አሁንም አዲስ አበባ ላይ ሊደገም ይመስላል ። ዶክተር ተወልደ ትኩእ ኢትዮጵያ በኦሮሞዎች ከደቡብ ወደ ሰሜን ወረራ ምክንያት ከእነ ህዝቦቿ ከባድ ውድቀት ደርሷባታል ይላሉ።
በ16ኛው ክፍለዘመን ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ፖርቱጋላዊ ተጓዥ ቤርሙዴዝ የኦሮሞዎችን መሬት ሽሚያ በአይን ከተመለከቱ ሰዎች አንዱ ነበር… ይሄንም የኦሮሞዎች ፍልሰት ዘመን በማይሽረው ምስክርነቱን ሲገልፅ…
“They are fierce and cruel people, who make war on their neighbours, and on all, only to destroy and depopulate their countries. In the places they conquer they slay all the men, cut off the private parts of the boys, kill the old women, and keep the young for their own use and service ”
በማለት ተረጋግተው በአገራቸውና በመሬታቸው ላይ ይኖሩ በነበሩ በነባር ህዝቦች ላይ ያደረሱትን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ዘግቧል ።
በኢትዮጵያም በዳዋሮ ፣ በቢዛሞ ፣ በፈጠጋር ይኖሩ የነበሩ ነባር ህዝቦች ዘላን እና ከብት አርቢዎቹ በነበሩት የኦሮሞ ወራሪዎች አስከፊ በደል ደርሶባቸው ከመኖር ወደ አለመኖር ጠፍተዋል ።

የአዲስ አበባን ጉዳይ ከታሪክ አንፃር አጠር አድርገን እንመልከተው ።
አፄ ምኒልክ የአገሪቱ ዋና ከተማ እንድሆን ቦታ ለመምረጥ ሲዘጋጁ ከፍተኛ የሆነ የአዋቂዎች ምክክር ከተደረገ በኋላ ለዋና ከተማነት የሚመረጠው የድሮ ነገስታት መቀመጫ የነበረ ቦታ እንድሆን የተወሰነ መሆኑን የተለያዩ የታሪክ ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል ። ታዋቂው አለምአቀፍ የታሪክ ተመራማሪ የነበሩት ሪቻርድ ፓንክረስት እንደገለፁት… ” የመንግስት መቀመጫ አስፈላጊነት እንደታመነበት ከ1878_ 79 ከኢማም አህመድ እና ከኦሮሞ ፍልሰት በፊት የአፄ ልብነ ድንግል ዋና ከተማ የነበረችውንና ከፍል ውሃ 8ኪሎ ሜትር ያክል የምትርቀውን እንጦጦ የመንግስታቸው መቀመጫ እንድትሆን ወሰኑ ። ከ50 አመታት በፊትም በ1843 የምኒልክ ቅድመ አያት የነበሩት ንጉስ ሳህለ ስላሴ አሁን አዲስአበባ የሚጠራውና ከፍልውሃ በስተምእራብ የ 10 ደቂቃ ጉዞ ርቀት ላይ በድሮ ጊዜ የተሰሩ የቤተክርስቲያን ፍርስራሽ አግኝተው ነበር”  ይላል ።
ከመፅሃፉ የተወሰደው እንግሊዚኛው እንደሚከተለው ይነበባል…
“Menilik determined to found a capital on one of the sites occupied by his ancestors in the day before Gragn Ahmed invasion and the subsquent advance of the Gallas . In 1878_79 Menilik decided on Lebna Denegel’s old capital which according to one tradition had been situated at Entoto i.e 8 KM north of Filwuha. Almost half a centurey in 1843 his grandfather, Sahel Sellassie had discovered a ruined church ten minute ride to the west of Filwuha (the site of present day Addis Ababa)
Menelik and the foundation of Addis Ababa.
Richard Pankhurst.
Cambridge University press.
Page 105
Lefebvre T, Petit and Vangaud, Voyage to Abyssinia.
Page, 240.

2 ~ አዲስአበባ ከህግ አንፃር ስትዳሰስ
………………

የህውሃት የጫካ ዶኪመንት የሆነውን ህገመንግስት መሰረት አድርጌ ለመፃፍ ፍላጎቱ አልነበረኝም ። ዛሬ በህግ ጉዳይ ላይ ለመፃፍ የገፋፋኝ በሌላ ጊዜ ታሪክን ለፖለቲካ ፍጆታ ሲበልቱና ሲከታትፉ የሚውሉት የኦሮሞ ልሂቃን ከታሪክ ተሻግረው በግልፅ የተቀመጠውንም ህግ በአላዋቂነት ሲዘነጣጥሉት ስለተመለከትኩኝ ነው ።
ህግን ለራሳቸው አላማ እንድስማማ አድርገው ጠምዘውና አጣመው ቢያቀርቡትም ከመሰረታዊ ሀቅነቱ የጋት ያክል ውልፍት አይልም ።
የኦሮሞ መብት ከህግ አኳያ ሊስተናገድ የሚችልበትን መስመር ከመጠቆምና ይልቅ በግርድፍ ችሎታቸውና አላዋቂነታቸው የህግ ተንታኝ የሆኑት የቁጭበሉ የህግ ባለሙያ ነን የሚሉና የሚፅፉት የትየለሌ እየሆኑ ነው ።

የልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ እንደእናት ህግ የሚጠቅሰው የህ/መንግስቱን 49 (5) ሲሆን ያ የህ/መንግስት አንቀጽ በራሱ ማሻሻያ የሚፈልግና ኦሮሚያ በፊንፊኔ ላይ ያለውን ባለቤትነት በግልፅ በሆነ አቀራረብ ውድቅ ያደረገ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህም ሲባል 49 (5) ፊንፊኔ በኦሮሚያ መሀል እንደሚገኝ ቢገልጽም በተጨማሪም ይኸው አገላለጽ የባለቤትነት ማረጋገጫ ተደርጎ ይቆጠራል ቢባል እንኳን ከ(2-4) ያሉ የንኡሳን አንቀጾች የጥግግት ንባብ የሚነግረን አብይ ቁምነገር ኦሮሚያ በከተማው ላይ የበይ ተመልካችና ምንም እንደማያገባው ይገልፅልናል ።፡
ስለዚህ 49 (5) አዲስአበባን የገለጻት ኦሮሚያ መሃል እንደተቀመጠች እንጂ እንደማንኛውም በዙርያዋ እንደሚገኝ አካባቢ የኦሮሚያ መሬት እንደሆነች እውቅና እንደማይሰጥ መረዳት ቀላል ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የህ/መንግስቱ አቋም ለዘመናት የተደረገውን ትግል አፈር ከድሜ የሚያስግጥ እንደመሆኑ ኦህዴድ እውነት ከልቡ ለክልሉ ቢቆረቆር ኖሮ በማያሻማ ሁኔታ ኦሮሚያ በፊንፊኔ መሬት ላይ ያላት ባለቤትነት እንዲረጋገጥ የህ/መንግስታዊ ማሻሻያ እንጂ ረቂቅ ትርጉም አልባ አዋጅ ማቅረብ አልነበረበትም ።

በህገመንግስቱ አንቀፅ 51 የፌደራል መንግስቱን ስልጣን በሚደነግገው ስርም ቢሆን
ክልሎች በመሬትና የተፈጥሮ ሀብት ጉዳይ የተነጠቁት መብት አለ። የገጠሩ ኢኮኖሚ ወሳኝ በሆነበት ህብረተሰብ ውስጥ መሬት የመንግስት ሀብት ተብሎ ተደንግጓል ። ክልሎች የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነፃነት የተነፈጉት መሬት የመንግስት ሀብት ተብሎ በመደንገጉ ብቻ አይደለም።
የአንድ ክልል መንግስታት በተወሰነ ደረጃ ስለመሬትና የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም ዝርዝር ህግና ፖሊሲ የማውጣት መብት እንኳን የላቸውም።
ክልሎች በመሬት ጉዳይ ላይ ያለቻቸው መብት የፌደራሉ መንግስት በሚያወጣው ህግ መሰረት መሬትንና የተፈጥሮ ሃብትን የማስተዳደር ሃላፊነት ብቻ ነው። በዚህም መሰረት ከህግም ሆነ ከታሪክ አንፃር ኦሮሚያ በአዲስአበባ ከተማ ላይ ከተደነገገለት ኢምንት ጥቅም ውጭ ምንም ባለቤትነት እንደሌለው መረዳት ይቻላል ።

መደምደሚያ

እነ ቤኒቶ ሞሶሎኒ እና ሩዶልፎ ግራዚያኒ የተጠቀሙበት የፋሽስት ኢጣሊያ ዘመን የነበረው የአገዛዝ ዜደና ከ 50 አመታት በኋላ በአገር በቀሉ ፋሽስት መለስ ዜናዊ ሲደገም አይተናል ።
ወያኔ በመጀመሪያ ስልጣን ሲይዝ የተጠቀመው ካርታ እና የፌደራል አወቃቀር ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮፕያን ሲይዝ የተገበረውን ካርታ ነበር ። በብሔር የተከፋፈለች ኢትዮጵያን ካርታ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራው የፋሽስት ጣሊያን ወራሪ በ1936 እ.ኤ.አ ሲሆን፤ አላማውም የጎሳና የብሔር ግጭትንበማነሳሳት ሰላም አልባ ኢትዮጵያን መፍጠር ነበር፡፡ ጣሊያኖች ለገዛ አገራቸው ለእነ ሮማ እና ቬነስ ያላደረጉትን የብሔር ክፍፍል ካርታ ለእኛ ለመስጠት ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቶ ነበር፡፡

ከ50 ዓመት በኋላ ግን በአቶ መለስ ዜናዊ አማካኝነት የጣሊያኖች ምኞት ሊሳካ ችሏል፡፡ ልዩነቱ የጣሊያን ካርታ በዚህ ሰሞን ግራና ቀኛቸውን መለየት የተሳናቸው
የኦሮሞ ፅንፈኞች የሚሟገቱበትን የአዲስ አበባንና አካባቢዋን የኦሮሞ ሳይሆን የአማራ ግዛት አካል ማድረጉ ነበር፡፡ጣሊያን አማራን የሚባለውን ብሄር አምርሮ ቢጠላም አዲስአበባ እና ሸዋ የዚህ ብሄር ታሪካዊ ግዛት መሆኑን ተቀብሎ ነበር ። መለስ ዜናዊና ኦነግ የአማራን ብሄር ከጣሊያን የበለጠ ይጠሉት ስነበር አዲስአበባን ከአማራ ክልልነት ካርታ ላይ ሊፍቅ ችሏል።

በዛሬይቷ የኦሮሞ ፅንፈኛ ፖለቲከኞች የተሳሳተ እና የተዛባ ተረት ተረታቸውን በጠቅላላው ህዝብ ላይ ለመጫን የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ ለአላማቸው መሳካት የተዛባና የተሳሳተ ታሪክ ትርክት ትምህርት በመንግስት ት/ቤቶች እንዲሰጥ
ፖለቲከኞች የማባበል ስራ (Lobbying) ተሰማርተዋል። በተቃራኒው ሌላው ህዝብ ዝም ብሎ በትዝብትና በበቸልተኝነት እየተመለከተ ነው ። ይሄ ቸልተኝነት አደገኛና የኢትዮጵያን ህዝብ አገር አልባ የሚያደርግ ስለሆነ ሁሉም መታገል አለበት።