July 7, 2017 – 

በጭፍራ ወረዳ በአፋርና በአማራ ተወላጆች መካከል በተነሳዉ ግጭት ሰዎች ሞቱ

ቢቢኤን ሰኔ 29/2009

በመሬት ይዞታ ይገባኛል ጥያቄ በአፋር ተወላጆችና በአማራ ተወላጆች መካከል በተፈጠረው ግጭት የሰዉ ህይወት መጥፋቱን የቢቢኤን ምንጮች ከስፍራዉ ገለጹ።

በትላንትናዉ እለት በጀመረዉ ግጭት ከአማራ ተላጆች በኩል 2 ሰዎች ሲሞቱ 2 ሰዎች መቁሰላቸዉ ታዉቋል። ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ከአፋር ተላጆች 4 ሰዎች ሲሞቱ 6 ሰዎ መቁሰላቸዉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢኤን ገልጸዋል።

ትላንታና የጀመረዉ የተኩስ ልዉዉጥ ዛሬ መቀጠሉን የሚናገሩት የአካባቢዉ ነዋሪዎች የአፋር ተዋጊዎችን ለማገዝ ከአሳይታ፣ ከአዳይቱና ከበዋኔ ድረስ ታጣቂዎች እየመጡ መሆናቸዉን የጭፍራ ወረዳ ነዋሪዎች ገልጸዋል።ምንም የሰዉ ህይወት ቢጥፋና ጉዳቱ የከፋ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ግጭቱን ለማብረድ የፌዴራል ፖሊስም ሆነ የመከላከያ ሰራዊት አለመግባቱ ተገልጿል።

በጭፍራ ወረዳ የቦታ ይገባኛል ጥያቄ ግጭት ከአመት በፊት እንደጀመረ የሚያስረዱት የአካባቢው ነዋሪች በባለፈዉ አመት በነበረው ግጭት ብዙ የሰዉ ህይወት እንዳለፈም ያስረዳሉ። ባለፈዉ አመት የነበረዉ ግጭት በሽምግልና የደም ካሳ ተከፍሎበት ሁለቱም ወገኖች መስማማት ላይ ቢደርሱም መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ ተገቢዉን እርምጃ በላመዉሰዱ ግጭቱ እንደገና እንዳገረሸ አሳዉቀዋል።

በዚሁ የአፋርና የአማራ ተወላጆች ግጭት የሞቱትን ሰዎች መቅበር የተጀመረ መሆኑን ያካባቢው ነዋሪዎች እያስረዱ የመሬት ይዞታ ይገባኛል በሚል ጥያቄ የተጀመረዉ ግጭት እየከፋ ሊሔድ እንደሚችል ስጋታቸዉን ለቢቢኤን ገልጸዋል። በግጭቱ በቀጥታ ከሚሳተፉት ተዋጊዎች ባሻገር ሴቶች ስንቅን ለተዋጊዎቹ እያቀበሉ መሆኑ ታዉቋል። በአካባቢዉ ላይ ያሉ ሴቶች በህብረት ለተዋጊዎቹ ስንቅን በማዘጋጀት ላይ መሆናቸዉ ስጋትን እንደፈጠረባችቸው አሳዉቀዋል።

በህወሃት የሚመራዉ መንግስት አገሪቷን በክልል፣በዞንና በወረዳ ከሸነሸነ በሗላ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ በተለያዩ ቦታዎች ግጭቶች የሚነሱ መሆናቸዉ ይታወቃል። መሰል ግጭቶችን ለማርገብ በማእከላዊ መንግስት በቂ ስራ ባለመሰራቱ ሳቢያ የዜጎች ህይወት እየተቀጠፈ መሆኑን የሚያስረዱት አስተያየት ሰጪዎች ህዝቡ ባለዉና በነበረዉ ባህላዊ የችግር አፈታት ዘይቤ በመጠቀም ችግሮቹን መፍታት እንዳለበት አብሮ የሚኖረ ህዝብ የጨቋኞች መጠቀሚያና የፖለቲካ ስልጣንን ማራዘሚያ እንዳይሆን ጥረት ሊያደርግ ይገባል የሚል ጥሪም ቀርቧል።