የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን ሰሞኑን  በአነስተኛ ነጋዴዎች ላይ እየጣለ ያለው አዲሱ የግምት የገቢ ግብር ተመን ከፍተኛ መደናገጥን የፈጠረ ሲሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ውስጥ ከዚሁ የቀን ገቢግምት ጋር በተያያዘ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡