July 12, 2017 04:59

የአቶ አርከበ ዕቁባይ ኢትዮጲያዊት ሲንጋፖር እቅድ!!!

አቶ አርከበ ኢትዮጲያ ከአስር አመት ቦሃላ በአፍሪቃ ውስጥ በኢንዳስትሪ የበለጸገች አገር እናደርጋታለን ይላሉ፣ ይህ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጲያ ከአስር አመት ቦሃላ የወደብ ባለቤት እንድትሆንም እናደርጋታለን ይላሉ። በአቶ አርከበ ስሌት ግብርናው አድገዋል፣ እስካሁን ድረስ ግን ራሳችንን መመገብ አቅቶናል፣ አቶ አርከበ ከአይጋ ፎረም ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ፣ በግብርና አለማደጋችንን ራሳቸው መስክረዋል፣ እስካሁን ድረስ ተርበን እርዳታ መለመናችን አሳፋሪ ነው ይላሉ። ግብርና ብቻ አደገ የተባለው የት ነው።ከድህንነት አርንቛ ስላልወጣን ብቻ ዜጎቻችን ወደ አረብ አገር መሰደዳቸውንም ያሳፍራል ብለዋል።

አቶ አርከበ በሚቀጥሉት አስር አመታት ማኒፋክቸሪክ በአራት እጥፍ ማደግ አለበት ይላሉ።በየ አመቱ ሃያ አምስት ከመቶ ማለት ነው በሳቸው ስሌት አስረግጠው ይናገራሉ። አስራ አንድ በመቶ አድገናል ካሉም ቦሃላ “አንድ አገር ፈጣን እድገት” አመጣ ማለት የሚቻለው በጣም ሰፊ “ኤክስፖርት የማመንጨት አቅም” ካለው ነው ይላሉ። እዚህም ፈረሰባቸው፣ አንድ አገር አደገ ከተባለ ኤክስፖርት ከኢምፖርቱ ሲበልጥ ነው፣ ስለዚህ ላለፉት አስራ አምስት አመታት አስራ አንድ ከመቶ የነበረ እድገት ውሸት ነው ማለት ነው። አደግን ከተባለ ኤክስፖርታችን ከኢምፖርታችን በለጠ ማለት ነው፣ ይህ ግን አቶ አርከበ በሚመርዋት አገር ሳይሆን ያለው በኢኮኖሚክስ 101 ብቻ ነው ያለው።

በኢትዮጲያ በየአመቱ ከመላው ዩኒቨርሲቲ ከመቶ አምሳ ሺ በላይ ተማሪዎች ይመረቃሉ፣ ከቴክኒክ እና ሙያ ትምርት ቤቶች በየአመቱ ከአንድ ሚልዮን በላይ ተማሪዎች ይመረቃሉ፣ ስለዚህ ምርጫ እስከሚደርስ ድረስ ብቻ; “ምርጫ ካለ” ማለቴ ነው ወደ አራት ሚልዮን የሚሆን ስራ አጥ ይፈጠራል፣ በ አቶ አርከበ ስሌት ለዚህም መፍትሄው ኢንዳስትርያል ፓርኮች መገምባት እና በአመት ውስጥ አንድ ሚልዮን ስራ መፍጠር ማለት ነው። አዋሳ ኢዳስትርያል ፓርክ ስድሳ ሺ የስራ እድል ይፈጥራል ተብለዋል፣ ይህ ማለት ከስራ አጡ ብዛት አንድ ሞቶኛ እንካን አይሞላም።

 http://aigaforum.com/interv…/mekelle-industrial-hub-2017.php

በአቶ አርከበ ኢኮኖሚያዊ ስሌት በሚቀጥሉት አስር አመታት ከኢንዳስትርያል ፓርኮች ለሚመረቱ ምርቶች ወደ ውጭ ለመላክ ዋናው ቁልፍ ነገሩ ወደብ ነው፣ ለዚህም ነው አቶ አርከበ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ፣ በሚቀጥሉት አስር አመታት የአሰብን ወደብ መጠቀም አለብን የሚሉን፣ ያኔ ኢንዳስትርያል ፓርኮቹ ተገምብተው ፣ የስራ አጡ ቁጥር እንደ አሜሪካ ከአስር በመቶ በታች ሆኖ፣ወደብ ኖሮን ሲንጋፖር ሊንሆን ነው ማለት ነው!!! የራሳችንን ወደብ አስረክበን ወደቡን ለማስመለስ አሁንም የድሃው ደም ልንገብር ነው። ጊዜ ትልቅ መምህር ነው እና፣ ከአስር አመት ቦሃላ የአቶ አርከበ ኢትዮጲያዊት ሲንጋፖር ለማየት ጓጉቻለሁኝ። ለመሆኑ የአቶ አርከበ የፊዊዳል ስርአት አስር አመት ይኖራልን? ቅድመ አያቶቻችን እንደዚህ ሲገጥማቸው ጊዜ ለኩሉ ይላሉ፣ጊዜ ለኩሉ።