July 12, 2017

የባሪያ መፈንገሉን ስራ ለብዙ መቶ አመታት አጣጥማ ስ ትሰራ የኖረችው አውሮፓዊቷ ፈረንሳይ፤ እራሷን የስልጣኔ፣ የፍልስፍና፣ የስነጥበብና የፍቅር ተምሳሌት አርጋ ስትቆጥር የኖረችው ፓሪስ፣ ጡንቻዋንና ወታደራዊ ብቃቷን ከናፖሊዮን ተነስታ ስትሰፍር የኖረችው ፈረንሳይ በቻርለስ ደጎል ዘመን እጇን ለጀርመን ጦር የሰጠችው በሶስት ቀን ውስጥ ብቻ ነበረ። ደጎልም እንደኛው ሃይለስላሴ መናገሻውን ለጀርመን ጦር አስረክቦ ዘፋኑን ወደ እንግሊዝ አዛውሮ በሎንዶን ተቀመጠ። የናዚ ጦር በቀዩ ጦር እስኪሰበር ድረስ ከሎንዶን ሳይወጣ ኖሯል።

ምንም እንኩዋን እኛም ሆንን ፈረንሳዮች በትሪፕል አሊያንሱ ጦር ለአምስት አመታት የተያዝን ብንሆንም መሬት ላይ ያለው ልዩነታችን ግን የሰማይና የመሬት ያህል ግዙፍ ነበር። የጀርመን ጦር አንድም ቀን ሳይቆረቁረው ፈረንሳይን ላይ ባዲራውን ሰቅሎና እግሩን ዘርግቶባት ሲኖር የኛዎች ሸለቆዎችና ተራሮች ግን የማይሞሉ የፋሽቶች መቀበሪያዎች ሆነው ነበር። ዱርቤቴ ብለው ብለው በረሃ የገቡት የኛዎች አርበኞች ወራሪውን ጦር ኑሮውን የዛፍ ላይ እንቅልፍ እንዳደረጉበትና አንድም ቀን አፉን ሞልቶ ይህችን አገር እየገዛሁ ነው ብሎ እንዳይናገር አደረጉት። አገራችን በቅኝ ግዛት ያለተገዛች የሚያሰኛት ዋነኛውም ነጥብ ይኼው ህዝቡ ፤ለአንድም ቀን እጁን ለመስጠት ፈቃደኛ ሆኖ ባለመኖሩ ነበር።

በአንጻሩ ፈረንሳይ በጀርመን መያዟ በተነገረበት በበነጋታው የፓሪስን ገጽታ የሚያሳዩ የቪዲዮ ምስሎች ለማየት እድሉ ገጥሞኝ ነበር። አገሪቱ ከጠላትም ጠላት በናዚ ጦር ስለመያዟ ቅንጣት ታህል ምልክት ነበር ማለት አያስደፍርም። እንደ ማንኛውም ግዜ ሁሉ የፓሪስ ጎዳናዎች በቆነጃጅቶቻቸው ተሞልተው፣ ከፊቴሪያዎችን የሞዛርትና ቤቶቨን ሲምፎኒ እየተንቆረቆረባቸው ህዝቡም የናዚ ዩኒፈርም ከለበሱ የጀርመን ወታደሮች ጋር አብሮ ሻይ ቡና ሲል፣ አብሮ ሲያጨስ፣ በየአደባባዮቻቸው ካርታ ሲጫዎትና አንዳንዶቹም አልፈው ተርፈው አብረው “ቢዝነስ ሲሰሩ” የነበሩበት ሁኔታ ነው የነበረው። ለዚህም አንዱ ምሳሌ የፈረንሳይ የህትመት ቤቶች ናዚን የሚያወድሱና የሂትለር ፎቶ ያለባቸውና በጀርመንኛ ቋንቋ የተጻፉ ጋዜጦችን ወደማተም ደረጃ ተሸጋግረው ነበርና።ፈረንሳዮች ይህንን ያለምንም ተጋድሎ አገራቸውን ያስረከቡበትን እና ባርነትን እንደ ኒሻን አጎንብሰው የተቀበሉበትን አሳፋሪ የታሪክ ምእራፍ ለመሸፋፈን ዛሬ የሚጠቀሙባት አንዲት ማሳበቢያ አለቻቸው። “ያልተዋጋነው ከተማችን ፓሪስን ስለምንወዳት እንዳትፈርስብን ፈርተን ነው” የምትል ናት።የአንዲት አገር ህልውናና ብሄራዊ ማንነት ከዲንጋይ ክምር ያነሰበት ኩነት መሆኑ ነው።

በኛ አገር ግን አንድ ዘይቤ አለ። ከተማ ጭር ሲል የተወረረ ከተማ መሰለ ይባላል። ከስሙ ጀርባ ያለው ምክንያት ግልጽ ነው። ወራሪው ባእድ ነው ለማለት ነው። የበረታው ወደ በረሃ ለግዳይ ሲወጣ ህጻናቱ ሴቶቹና አረጋውያኑ ቤታቸውን ዘግተው ይቀመጣሉ ማለት ነው። ምናልባት ለምልክት ያህል በሩን ከፍቶ ከነዚህ ከወራሪዎቹ ለአንዱ በሩን ከፍቶ ጥርኝ ውሃ ያቀበለ ቢኖር “ጥቁር ውሻ ውለድ” ተብሎ የተረገመ ብቻ ነው። ሰው ለማንነቱ ክብር ሲሰጥ ወራሪን የሚያስተናግደው እንዲህ ነው። ዛሬ በጎንደር የሆነውም ይሔው ነው። ከተከዜ ማዶ ለመጡ ተኩላዎች መልስ የሰጠው እንዲህ ነው።ሳይነጋገር እንዲሁ በደመነፍስ በአንድ ቋንቋ ፤ወመኑ ዘይደምሮ ብርሃን ውስተ ጽልመት ነበር ያለው፤ ብርሃን ከጨለማ ህብረት የለውም እንደ ማለት ነው።ይኽ ማለት አማራውንና ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነትን ጠላታችን ብለው ደደቢት ለወረዱት ባንዶች ለአላማቸውን ሙሉ እውቅና ሰጥቶላቸዋል እንጅ ባለፈ ታሪክ ታስሮ “ወንድሞቸ” አላለም። በዜግነት ሽፋን ከማይመስሉት አውሬዎች ጋር የኖረበት ያላፉት ዘመናት የማያዋጣው መቻቻል ሞቶ የተቀበረ መሆኑን በግልጽ ያሳየበት፣ ይልቁንም የቀጣይዋን አገራችንን ሙሉ ገጽታ ምን እንደምትመስል አሻራዋን ከወዲሁ ቀድሞ ያሳየበት በሌላ አነጋገር ከራስ ስሁለ ሳጥናኤል ዝርያዎች ጋር እትብቱን የተባጠሰ መሆኑን በግልጽ ያሳየበት ኩነት ሆኗል ማለት ነው።