Yonatan Tesfaye Regassa

July 12, 2017

(.ኤም.ኤፍ) ዮናታን ተስፋዬ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነበር። ረጋ ያለና ቁጥብ ወጣት ነው። በ2017 በተደረገው ምርጫ ጭምር ተወዳድሮ ነበር። ሆኖም ገና በ31 አመቱ፤ በአመለካከቱ ምክንያት የስድስት አመት እስር ተበይኖበት፤ ለአገሩ መልካም ነገር ማበርከት የሚችል ወጣት፤ በአሁኑ ወቅት በዝዋይ ማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛል። ባለፈው አመት በኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች፤ ንጹሃን ዜጎች በግፍ ሲገደሉ ድርጊቱን በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ተቃውሟል። ይህ ተቃውሞው ነው ዮናታን ተስፋዬን ለእስር የዳረገው።

ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ በታሰረበት ወቅት፤ “ጎዳና ላይ ያለርህራሄ ለተገደሉት ዜጎች መናገሬ ወንጀል ከሆነ፤ መታሰሬን በክብር እቀበለዋለሁ። ፍርድንም ከታሪክ እና ከእግዚአብሔር አገኛለሁ” ብሎ ነበር። ዛሬ በቃሊቲ፣ በቅሊንጦ፣ በዝዋይ፣ በየክልሉ እና በማይታወቁ እስር ቤቶች ውስጥ ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት በእስር ላይ ይገኛሉ። ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳም ከነዚያ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች አንደኛው ነው።

ባለፈው አመት ልክ በዚህ ወር ታላቅ የህዝብ ንቅናቄ የተፈጠረበት ወቅት ነው። ብዙዎች ይህንን ቀን እና ሰማዕታቶችን እየዘከሩ ነው። ስለነዚህ ሰማዕታት በመናገሩ ምክንያት የታሰረውንና አሁን በእስር ላይ የሚገኘውን ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳንም ልናስበው ይገባልና፤ ከዝዋይ እስር ቤት የላከውን ማስታወሻ ለህትመት አብቅተነዋል።
ዮናታን አሁን የሚገኘው በዝዋይ የፌደራል ማ/ቤት የስድስት አመት ከስድስት ወር የእስር ቅጣት ተፈርድቦት ነው ያለው። ለእስር የተዳረገውም በግል ፌስ ቡኩ ላይ “ሽብርተኝነትን የሚያበረታታ ጽሁፍ ጽፈሃል” በሚል ነው፡፡

እንዲህ ይላል ዮናታን ተስፋዬ።

በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡– መጀመሪያ የጸረሽብርተኝነት አዋጁን አንቀጽ 4 መተላለፍ የሚል ነበር፡፡ በኋላ ግን በብይን ወቅት አንቀጹ ተቀይሮ የአዋጁን አንቀጽ 6 መተላለፍ የሚል ሆኗል፡፡ በዚህ አንቀጽ ጥፋተኛ ተብዬ የ6 አመት ከ6 ወር ቅጣት ተወስኖብኛል፡፡

በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል፡፡


. በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ለአራት ወራት በቆየሁባቸው ጊዜያት

  1. ሳይቤሪያ በሚባለበሚባለለማለማ ስፍራ ታስሬያለሁ፡፡
    2.
    ቤተሰብና የሐይማኖት አባትን ጨምሮ ጠያቂ ተከልክያለሁ፡፡
    3.
    በግል የጻፍኋቸው የፌስ ቡክ ጽሁፎቼ ላይ ለማስረጃነት እንድፈርም ተደርጌያለሁ፡፡
    . በቂሊንጦ እስር ቤት በቆየሁባቸው ጊዜያት
    1.
    ከሌሎች እስረኞች ተነጥየ እንድታሰር ተደርጌያለሁ፡፡
    2.
    ለሦስት ቀናት ቀንና ሌሊት እጅና እግሬን በሰንሰለት ታስሬ ነበር፡፡

3. ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡

4. ዛቻና ማስፈራሪያ ደርሶብኛል፡
5.
የጠያቂ ገደብ ተጥሎብኛል፡
6.
የመጠየቂያ ሰዓት ገደብ ተደርጎብኛል፡
7.
ጠበቃየን እንዳላናግር ተከልክዬ ነበር፡፡

በመጨረሻም፣ ስለእኔ ትንሽ ለማለት ያህል፣ ከ1ኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ የተማርሁት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ነው፡፡ ትውልዴና እድገቴም አዲስ አበባ ነው፡፡ ለቤተሰቦቼ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ፡፡ በተማርሁት የውጭ ቋንቋና ሥነጽሁፍ ትምህርት ዘርፍ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋን አስተምሬያለሁ፡፡

1997 .ም ጀምሮ በተለያዩ ደረጃዎች ሰላማዊ የፖለቲካ ስራ ስሰራ ቆይቻለሁ፡፡ በግልም ሀሳቤን ከመግለጽ ወደኋላ ያልሁበት ጊዜ የለም ማለት እችላለሁ፡፡ ከ2005 .ም ጀምሮ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቅያለሁ፡፡ በፓርቲው ውስጥ ከተራ አባል እስከ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊነት ተሳትፎ አለኝ፡፡ በ2007 ሀገራዊ ምርጫም ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እጩ ተወዳዳሪ ነበርሁ፡፡ሰላማዊ ትግልና በህጋዊ አሰራር የማምን ሰው ነኝ፡፡ በእውነቱ ህገመንግስታዊ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ መብቴን ተጠቅሜ በመፃፌ ረጅም እስር እና ፍርድ ቤት መንላታ ሳያንስ በእስር ወቅት ከላይ የጠቀስኩት ከፍተኛ የመብት ጥሰት ደርሶብኛል፡፡