July 17, 2017 More 

አዲስ አበባ

(አብነት)

ይህች የመላው ኢትዮጵያዊና አፍሪካዊ ዋና ከተማን ለወያኔ የስልጣን የመጨረሻ መቆናጠጫ አድርጎ ለመጠቀም ብቻ ሲባል በማን አለብኝነት፤ ታሪክን፤ የሕዝብ አሰፋፈርን፤ ወዘተ. ችላ ብሎ በጠባብ የፖለቲካ አባዜ ተወጥሮ ለኦሮሞ አክራሪ የኦነግ ተኩላዎች አሳልፎ መስጠት ማለት የራስን መቃብር እየቆፈረ እንደ ደሆነ ሕወሐት ለምን ሳይገነዘበው ቀረ? ለመሆኑ በአዲስ አበባ ምስረታና ከስር መሰረትዋ ቅንጣት ያህል ታሪካዊ ሚና ያልነበረው አምባገነኑ የትግሬዎች መንጋ በከተማዋ የማንነት ጥያቄ ላይ ምንስ ያገባዋል? ላም ባልዋ ለበት ኩበት ለቀማ በሆነባት በዛሬይቱ የተጎሳቆለችው ኢትዮጵያ ጠባቦችና በውሸት አፈ ታሪክ እያወናበዱ ለ ስልጣን ሽሚያ የሚሩዋሩዋጡት ወያኔና ኦነግ እውን ፀበኞች ናቸውን? በትኩረት ከተመለከታችሁት ኦነግና ወያኔ ከሻቢያ ጋር ሆነው ከተማዋን የዛሬ 26 ዓመት ሲቆጣጠሩ በተማማሉት መሰረት አስቀድመው ሻቢያን በአስመራ አነገሱት፡ ከዛ በሁዋላ የውስጥ አገር የማፍረስ አጀንዳቸው እንዳለ ሆኖ ኦነግ ሆን ተብሎ ራሱን እንዲያገልና ከውጭ ሆኖ በተቃዋሚነት ቀሚስ ለብሶ እንዲንቀሳቀስ ተደረገ።

ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ እንደሚሄደው ወያኔና የተለያዩ ካባዎችን ያጠለቁት የኦሮሞ ድርጅቶች ተደብቃ ከዚህም ከዚያም ዓለምዋን እንደምትቀጭ ኮረዳ ኦህዴድ ተብሎ በተሰየመው ኦነግ ስር በመሽሞ ንሞንና ከወያኔ ጋር ተባብረው አገሪቱ የዘረኞች መፈንጫ እንድትሆን ከማድረጋቸውም በተጨማሪ በመሰረተ ልማት ትግራይና ኦሮሚያ ከተቀሩት አካባቢዎች የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፈር ቀደዋል። አሁን ላይ ሁለቱን ቡድኖች የሚያጣላቸው አንድ ነገር ብቻ ነው፡ እርሱም የስልጣኑ ዙፋን ላይ እኔ ብቻ ልቀመጥ የሚ

ለው ስግብግብ ፀባያቸው፡ አለበለዚያ ከድርጊታቸው ስንገነዘብ የቆየንው ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ገጽታ መ ሆናቸውን ነው። በዚህ ሽፍንፍን ፖለቲካ ግን የኦሮሞ ወጣቶች ተጠቂዎች መሆናቸውን ማንም አይክደውም የኦሮሞው ወጣት ቢያልቅስ እነርሱን ምን ግድ ይላቸዋል? አንዱ ካንዱ ለመብለጥ ሕዝብን ችቦ አድርጎ ማቅረቡን የኦሮም ድርጅቶችም ሆኑ ወያኔ ተክነውት የለምን? ዞሮ ዞር መዝጊያው . . . ሆነና የጎጥ ፖለቲከኞቹ ጉድና ሸፍጥ እርስ በራሳቸው ቢያነታርካቸውም አሁንም ቢሆን አንድ በሚያደርጋቸው የፀረ አማራ ልክፍታቸው ተባብረው ከመስራት ወደ ሁዋላ እንዲሉ አላደረጋቸውም። በነርሱ እርኩስ ዓላማ ምክንያት አምስት ሚሊዮን አማራ ጭዳ ሆኖ የለምን? የአማራው አንጡራ መሬቶችን እንደቅርጫ ስጋ ተከፋፍለውት የተረፈውንም የሚመኩባቸውን አጼ ዮሐንስን አንገታቸውን ቆርጥ እስከዛሬ በኦምዱርማን አስቀምጦት ላለውስ ሱዳን እጅ መንሻ ያለሀፍረት ሰጥተው የለምን? ሻቢያ፤ኦነግና ሕወሐት ሀፍረት የማያውቁ ከሀዲዎች ናቸው።

የዛሬዋ አዲስ አበባ በተጨባጭ መሬት ላይ አርፎ ከሚገኝ ፍርስራሽ በጥናት እንደተረጋገጠው የተቆረቆረችው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በሺህ አራት መቶዎቹ ዓ/ም ነበር። እኛ ተማሪዎች ሆነን የተነገረን ማለትም አጼ ሚኒሊክ መሰረትዋት የሚባለው ትክክል አይደለም። እርሳቸው ስልጣን ላይ ከመጡ ግዜ አንስቶ የቅም ቅም አያቶቻቸው ከተማን ፍለጋ ተያይዘው ቆይተው በሺህ ስምንት መቶ ሰማንያ አንድ ዓ/ም ባለቤታቸው አዲስ አበባ ያልዋትን ጥንታዊትዋን የነ አጼ ዳዊት ባራራን አግኝተው ህልማቸውን ካሳኩ በሁዋላ ዛሬ ላይ የምና ውቃትን ከተማ እንደገና የመገንባቱን ስራ እውን አደረጉት። ሚኒሊክን ብልህና አስተዋይ ከሚያደርጉዋቸውም ስራዎቻቸው አንዱ ይሄው የጥንታዊቱን ባራራን ከተማ ከትቢያ አውጥቶ ታሪክን ለመድገም የነበራቸው ቁርጠ ኝነት የተሳካላቸው መሆኑ ነው። እቺ ከተማ ከስድስት መቶ ዓመት በላይ ተመስርታ የኖረች ናት። የቬኒስ ነጋዴዎች በሺህ አራት መቶ ሀምሳዎቹ ዓ/ም በሳሉት ካርታ ላይ ባራራን ቁልጭ አድርገው አሳይተዋታል።

ለመሆኑ ኦሮሞዎች በዛን ግዜ ባካባቢው ነበሩን? መልሱ ፈጽሞ አልነበሩም ነው። እነርሱ እኮ አዲስ አበባ የመጡት ግራኝ አህመድ በከፈተው ቀዳዳ ዘው ብለው ባራራ ከተቆረቆረች ሁለት መቶ ዓመት በሁዋላ ነው። ታዲያ ይህ ሀቅ በማይፋቅና በማይደለዝ ማስረጃ እያለ ወያኔና ኦነግ ከተማዋን ለመሸጥና ለመግዛት ድርድር  እንዴት ሊቆሙ ቻሉ?

የዚች ከተማ ጉዳይ ሶስቱ ሴጣኖች የምላቸው ሻቢያ፤ሕወሐትና ኦነግ አማራውን ገዝግዘው ከስር መሰረቱ ገርስሶ በመጣል ልክ እንደ ባራራ ትቢያ ለማልበስ በየመመሪያ ዳዊታቸው ላይ የጻፉትን ጥላቻ ተግባራዊ አድር ገው አማራ የሚባል ነገድ ከምድር እንዲጠፋ የጀመሩት ማለቂያ የሌለው የጉንጉን ስራቸው ዋነኛው አካል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ለምን የሀይለስላሴና ደርግ መንግስቶች የባራራን ፍርስራሽ ቅርስና ታሪክ ደብቅወት ኖሩ? ወያኔስ በየቦታው ይሄ ታሪክ ያኛው ታሪክ ወዘተ. እያለ ቱሪስቶችን ለማማመል ብሎም ዶላር ለማጋበስ ሲሮጥና ሲራወጥ እዛው አገር ከሚገዛባት አራት ኪሎ በትንሽ ርቀት ያለችውን ባራራ ጉዳይ አድበስብሶ የያዘበት ምክንያት ለምንድር ነው ብሎ የጠየቀ አለ? የአማራ ምሁራንስ ልብና መንፈስ ይህን ሀቅ እያወቁ ባገር ቤትም ሆነ በውጪ ያሉት ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው እስከዛሬ አማራው የጠባብ ጎጠኞች መፈንጫ ሲሆን ምን አስችሎዋቸው ጭጭ አሉ? ለማንኛውም በዚህ አጋጣሚ በአማራ ስም የተደራጃችሁና የአማራው ጉዳይ አንገብግቦናል የምትሉ ባደባባይ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ታሪክን ያገናዘበ ትንተና በመስጠት ያላችሁን አቁዋም እየተረገጠ ላለው አማራ አሳውቁት። እስከመቼ ይሉንታን ተሸክማችሁ ትዘልቃላችሁ?

መጨረሻም ለዚች መልዕክት መነሻ የሆነኝን የፕሮፌሰር ማርኮ ቪጋኖን የጥናት ውጤት የሚያሳዩትን በዩ ቲዩብ ያሉ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ወልቃይትና ኢትዮ ፓትሪዮትስ እንዲሁም ሌሎች ያገባናል ወይም ሀቁን በሚዲያችን ለሕዝብ እናቀርባለን የምትሉ ሁሉ በድህረ ገጾቻችሁ ብትለጥፉት ተጨባጭ የታሪክ ማስረጃ ማለት ምን እንደሆነ ፍንትው አድርጎ በማመልከት የአዲስ አበባን የስድስት መቶ ዓመት አመሰራረት ብዙዎች ሊማሩበት ይችላሉ የሚል ሀሳብ አለኝ። በአጠቃላይ ታሪካዊ ማስረጃዎችን አሰባስቤ ስጨርስ በጉዳዩ ሰፋ ያለ ጽሁፍ ለንባብ እስከማበቃ ደረስ አብነት ሁነኛው ነኝ! ሰላም!

*******************

BARARA / Addis Ababa

Professor Marco Vigano

Published on Jun 22, 2014

Thirty hectares of medieval ruins, with an amazing pentagonal citadel surrounded by twelve protruding towers. The biggest archaeological discovery in Ethiopia since many years.

Is this Barara, the Capital of Abyssinia of the XV and early XVI century, visited by many, artists, traders, from Aragon, Turkey and above all Venice?

The missing link between early Christian Ethiopia and the Gondar Castles, the main siege of a trade power based on contact with the sea ports, controlled by Islamic states.

There, the source of its power and destruction, well exemplified in its standing ruins, at the hand of Ahmed ibn Ibrahim al Ghazi, the “left handed”, in 1530 AD.

BARARA light

Professor Marco Vigano

Published on May 20, 2014

Sequel to the “Pentagonal fortress and Town” Youtube video we used to break news on the findings of a medieval capital of Ethiopia up the Entoto ridge, Addis Ababa.

This video relates the find to the Fra Mauro Map, and documents some of the unexpected structures uncovered.

Pentagonal fortress and Town. Medieval Ethiopia recovered.

Professor Marco Vigano

Published on May 20, 2014

The surprise find of a medieval fortress just up from Addis Ababa University, A major one, with twelve towers, loopholes, deep and wide trenches, inner structures. In the context of a whole complex town, easily datable to the XV and the very first years of the XVI centuries, as the consequent decline of Ethiopia and occupation by mainly nomadic Oromos exclude any other more recent origin.

Rock hewn churches, steps, palace bases, and a spring cut in the rock. Ornate stones of all sorts, including an unseen feline head protruding an horrible tongue. Paved roads and wall sided alleys, a residence of Royal standing and dozens and dozens of stones structures. A capital city of Abyssinia, re-discovered, after Minilik claimed discovery in 1881. Re-lost and long forgotten, covered in moss and bush. The missing link between the South expansion of Christianity at the slow fall of Axum and the Gondar Castles. The centre of a developed area Europeans respected as the fief of a mythic alley King, Prester John. Is this, then Barara, the quasi mythical Capital of Abassia or Abyssinia known to European medieval trevellers?

Barara to Addis Ababa. An ancient capital rapidly grows.

Professor Marco Vigano

Published on Jul 5, 2014

A minute and a half spot-like presentation of how Addis Ababa, once a famed medieval capital, Barara, booms in the second millennium.

A call to action to a potential sponsor, Ethiopian Airlines, to investigate and save a major archaeological find.