በኢትዮጵያችን ከሰማንያ በላይ ብሔር ብሔረሰቦች አሉ ተብሎ ይታመናል፣ አገራችን የነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ነች። በዚህች መሬት የተፈጠሩ ብሔር  ብሔረሰቦች የራሳቸው ቋንቋ አላቸው፤ ከነዚህ ውስጥ አገርኛ የሆነ ከግእዝ የመነጨ ፊደል ያለው አማርኛ አንዱ ነው። በዚህ ቋንቋ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ መገናኛ እና መግባቢያ አድርገው ተጠቅመውበታል። በጊዜው የነበሩ የኢትዮጵያ ነገሥታትም ሆኑ እስካሁን ድረስ ያሉት አስተዳዳሪዎች የመንግሥት የሥራ ቋንቋ ኣድርገው ለዘመናት ሠርተውበታል። የአማርኛ ቋንቋ፤ ኢትዮጵያዊያን የሚግባቡበት፣ አገር በጠላት ስትወረር አገናኝና አስተባባሪ መሪ ሆኖ ያገለገለ ከአንድነታችን ጋር የተሳሰረ ቋንቋ ነው። ያለ አማርኛ ቋንቋ እንደ አንድ አገር፣  እንደ  አንድ  ህዝብ  ሁነን  ታሪክ አይኖረንም ወይም ልንሠራ አንችልም ነበር። ከብዙ በጥቂቱ ከአፄ ቴዎድሮስ እስከ አፄ ዮሐንስ፣ ከአፄ ምኒልክ እስከ ንግሥት ዘውዲቱ፣ ከአፄ ኃይለሥላሴ  እስከ     ፕረዚደንት መንግሥቱ  ከዚያም  እስከ  ጠ/ሚኒስትር  መለስና እርሳቸውን  የተኳቸው ጠ/ሚኒስትር

ኃይለማርያም ደሳለኝ ድረስ፤ከፋም ጠቀመም በነኝህ ስርአቶች  ስር  ሁነን  ታሪክ እየሠራን ያለነው በአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት እንደሆነ ታሪክ ራሱ ምስክር ነው። አገራችን ኢትዮጵያን ከማንም ጠላት ለመከላከል ወላጆቻችን  ባማርኛ  ቋንቋ ተግባብተው ሦስት ቀለማት ሰንደቅ አላማችንን በማውለብለብ፤ ተርበው፣ ተጠምተው፣ ደክመውና ቆስለው፣ ሞተውና ደማቸውን  አፍስሰው፣  ነፃነታችንን  ጠብቀው አኩሪ ታሪክ እንዳስረከቡን ሁላችን የምናውቀው ነው።

—-[ሙሉውን  በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ]—-