JULY 19, 2017

– “የካቲት 16 ቀን 1994 .ም የገዳሙን መታረስ በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፃፍነው ደብዳቤ ነው የተከሰስነው”መነኮሳቱ
የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ዳንኤል ሺበሺ በድጋሜ ለብይን ተቀጠሩ፣አቶ አብርሃ ደስታ ዛሬም አልቀረቡም !

(በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)

**የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸውን ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሁነው እየተከታተሉ የሚገኙ ሁለት የዋልድባ ገዳም መነኮሳትን ጨምሮ 35 ሰዎች ዛሬ ሀምሌ 11 ቀን 2009 .ም ፌደራል ከፍተኛ ፈርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ችሎት ቀረቡ ፡፡33ቱ ተከሰሾች የክስ መቃዎሚያቸውን አቅርበዋል፡፡ሁለቱ መነኮሳት መቃወሚያ እንደሌላቸው ገልፀው የሽበር ድርጊት እንዳልፈፀሙ ጥፋተኛም አይደለንም የተከሰስነው የዋልድባ ገዳም ለልማት በሚል መታረሱ አግባብ አለመሆኑን ከሌሎች ሰዎች ጋር በጋራ በመሆን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቲት 16 ቀን 1994 .ም በፃፍነው ደብዳቤ ነው ይህ ደግሞ በእምነቱም ተቀባይነት ያለው ነገር ነው በማለት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መዝገብ ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች፡ተሻገር ወ/ሚካኤል ላቀው፣ ነጋ ዘላለም መንግስት፣ ተስፋሁን ማንዴ ሰላምሰው፣አባ ገ/እየሱስ ኪ/ማርያም ካሴ ፣አባ ገ/ስላሴ ወ/ሀይማኖት ፣ሰኢድ ኑርሁሴን ኑርሰይድ፣ በለጠ አዱኛ መንግስቱ ፣ተስፋሚካኤል አበበ ላቀው፣ እንዳለው ፍቃዴ አበበ፣ስለሽ ግርማይ ነጋሽ፣ ይታይ ክብረት አታላይ፣ አዛናው ሲሳይ ገዛኸኝ፣ዮሃንስ አየሁ ዘለቀ፣ አለማየሁ መኳንንት ካሴ ፣አሸናፊ ዮሃንስ ዘሪሁን፣ እዮኤል በሪሁን ይማም፣ዓለምሰገድ ዋኛው በሪሁን፣ አበበ አበጀ ሽመልስ፣ መንግስቴ ተስፋሁን አረጋ፣ሰለሞን ፀኃይ እንግዳ፣ አዝመራው ተሰማ አዕምሮ፣ ከበቡሽ ደሳለኝ መንግስቴ፣ታደሰ ይግዛው ገብሬ፣ቢራራ ልጃዓለም አብርሃም ፣አብርሃም ድረስ አለሙ፣አማረ ገ/ሚካኤል ገ/ስላሴ፣ሲሳይ ተስፋ ደሴ፣ አራጋው እንዳለ አሰፋ፣ፍቅሬ ግርማይ ምትኩ፣ ደጀኔ ደምሴ ወርቅነህ፣ሙላቱ ፍስሃ ገብሩ፣ማርሸት አሰፋ ባዬ፣ ክንድሽ ሀጎስ ታዬ፣መንግስቴ አማረ ያዜ እና ተስፋሁን ሙሌ መኮንን ሲሆኑ የዓቃቢ ህግ በመቃወሚያው ላይ ያለውን መልስ ለመጠባበቅ ለሀምሌ 21 ቀን 2009 .ም ተቀጥሯል፡፡

**በሽብር የተከሰሱት ሁለት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አባላትን ጨምሮ አስር ተከሳሾችም ዛሬ ሀምሌ 11 ቀን 2009 .ም ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4 ወንጀል ችሎት ቀርበው የክስ መቃወሚያቸውን ያቀረቡ ሲሆን አቃቢ ህግ በመቃወሚያው ላይ ሀምሌ 20 ቀን 2009 .ም መልስ እንዲያርብ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡በዚህ መዝገብ ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች ክንዱ ዱቤ፣ዘመነ ጌቱ፣ደበበ ሞገስ ፣ዘርዓይ አዝመራው፣ገብረስላሴ ደሴ፣መርጌታ ዲበኩሉ ሰማረ፣ሀብታሙ እንየው፣ብርሀኑ አያሌው፣መላኩ አለም እና ለገሰ ወልደሀና ናቸው፡፡

**በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ ለዛሬ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቶ የነበሩ የዓቃቢ ህግ ምስክሮች ዛሬም አለቀረቡም፡፡
ዓቃቢ ህግ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው የጠየቀ ሲሆን የተካሰሾች ጠበቆች በበኩላቸው ተደጋጋሚ ጊዜ በመቀጠሩ የደንበኞቻቸውን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታቸውን የሚያሰጣ በመሆኑ ዓቃቢ ህግ ምስክሮችን ማቅረብ እንዳልቻለ ተቆጥሮ በቀረበው ማስረጃ ብይን እነዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡
ታጋይ ንግስት ይርጋ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ለአራት ወራት ያህል መቆም እስኪያቅታቸው ድረስ ድብደባ ደርሶብኛል፣አሁንም ቤተሰብ እንደይጠይቀኝ እየተደረኩ ነው፣እኔ በሰው ሀገር እየተሰቃየሁ ነበር ቤተሰቤን የማስረዳድረው ቤተሰቦቼ ደካማ ናቸው፣ዓቃቢ ህግ እየሰራው ያለው ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ነው ምስክር ቢኖረው እስካሁን ማቅረብ ይችል ነበር ስለዚህ ቀጠሮ ሊሰጥ አይገባም በማለት በችሎት ተናግራለች፡፡ ፍርድ ቤቱም በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ለነገ ለሀምሌ 12 ቀን 2009 .ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡በዚህ መዝገብ ክስ የቀረበባቸው ንግስት ይርጋ፣በላይነህ አለምነህ፣ቴድሮስ ተላይ፤አለምነው ዋሴ፣ያሬድ ግርማ እና አወቀ አባተ ናቸው፡፡

**በተመሳሳይ የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ዳንኤል ሺበሺ ዛሬ ሀምሌ 11 ቀን 2009 .ም የቀረቡ ሲሆን የመከላከያ ምስክሮች የሰጡት ቃል ከመቅረፀ ድምፅ ባለመገልበጡ ብይን መስጠት እንዳልተቻለ ዳኛው ተናግረዋል፡፡በዚሁ መዝገብ የተከሰሱትና በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቶ የነበረው የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ ዛሬም አልቀረቡም፡፡ፍርድ ቤቱም የመከላከያ ምስክሮች ተገልብጦ እንዲቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት አቶ ዳንኤል ሺበሺን በተመለከተ ብይን ለመስጠት ለሀምሌ 21 ቀን ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን አቶ አብርሃ ደስታን ፖሊስ ለቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia