Wednesday, 19 July 2017 13:39

በ  ፋኑኤል ክንፉ 

ግብር መክፈል ዘመናዊ የመንግስት ሥርዓትን ለመዘርጋት ያለው ድርሻ፤ የማይተካ ነው። ጠንካራ የግብር አሰባሰብ ሥርዓት ያለው መንግስት፣ ዜጎች ለሚያቀርባቸው ኢኮኖሚያዊ እና የማሕበራዊ ፍትህ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት መደላደሎችን ይፈጥርለታል። የዜጎችን ወቅታዊ ጥያቄዎች በአፋጣኝ መመለስ የሚችል ሥርዓተመንግስት፣ የተረጋጋ ፖለቲካ በአንድ ሀገር ውስጥ የመፍጠር እድሉ በጣም ሰፊ ነው።

ዘመናዊ የመንግስት ሥርዓት ባለበት ሀገር፣ ከዜጎች የሚሰበሰበውን ግብር በተጠያቂነት እና በግልጸኝነት ማስተዳደር መለያቸው ነው። ከዜጎች የሚሰበሰብ ግብር ከሕግ አግባብ ውጪ መጠቀም በሕግ የሚያስጠይቅ ብቻ ሳይሆን፣ በግብር ከፋዩ ዘንድ እንደሞራል ግሽበት የሚታይ ነው። ይህም በመሆኑ በዘመናዊ መንግስት ሥርዓት አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ የሥርዓቱ ተሿሚዎች፣ ዜጎች ለሚከፍሉት ግብር ከበሬታ እና በቂ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ የሚሆኑት።

ዘመናዊ የመንግስት ሥርዓት በአግባቡ ባልዘረጉ ወይም ለመዘርጋት የሚዳዱ መንግስታት፣ የተጠያቂነት እና የግልጸኝነት አሰራሮች በእነሱ በጎ ፈቃድ የሚቸር እንጂ፤ የግብር ከፋዩ ሕብረተሰብ የሚገባው መብቶች ተደርገው አይወሰዱም። ግብር ከፋዩም የተሰበሰበው ገንዘብ ከወዴት ደረሰ የሚል ጥያቄ ማንሳት አለመደም፤ እንዲለምድም አልተደረገም። የሚቀርብለትን የአስተዳዳሪዎቹን ሪፖርት አዳምጦ፣ ከመንሾካሾክ እና ከሐሜታ በላይ አያሻግረውም። ቢያሻግረውም፣ ምን እንደሚደርስበት መገመት ይከብደዋል። እንዲህ እንዲህ እያለ ጠያቂም ተጠያቂም የሌለበት ሥርዓተ መንግስት ለመመስረት ይገደዳሉ።

በኢትዮጵያ ያለውም ተጨባጭ ሁኔታ ብዙ የራቀ አይደለም። ለዚህ ጥሩ አብነት የሚሆነን የፌዴራል ዋና ኦዲተር የአቶ ገመቹ ዱቢሶ የ2007 .. እና የ2008 .ም ሪፖርቶች ናቸው። የዋና የኦዲተር መ/ቤቱ የኦዲት ሪፖርት ዓላማ ናቸው ተብለው የተቀመጡት፣ መንግሥታዊ ተቋማት የተመደበላቸውን ዓመታዊ በጀት ለተመደበለት ዓላማ፣ በቁጠባና በሥርዓት ተጠቅመውበታል ወይ የሚለውን ኦዲት በማድረግ እና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ለማድረግ መሆኑ በተደጋጋሚ ተገልጿል። እስካሁንም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት አድማጭ እንደሆነ ቀጥሏል። በርግጥ የፓርላማው ኮሚኒኬሽን ኋላፊ “ሪፖርቱ ከቀረበልን አንድ ወር ሳይሞላው ዝምአላችሁ ተብለን፤ መወቀስ የለብንም” የሚል ምላሽ ማቅረቡን አስታውሳለሁ። በኋላ ሲገባን፣ የፓርላማው ኮሚኒኬሽን ኃላፊው ከተቀጠሩ አንድ ወሩ ይሆናል ብለን ምላሽ አልሰጠንም።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር የአቶ ገመቹ ዱቢሶ የ2008 .. በጀት አመት የኦዲት ሪፖርት እንደሚያሳየሁ፣ በ113 /ቤቶችና በ28 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ውስጥ ብቻ ከ 5 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ሳይወራረድ መገኘቱን ነው። እንዲሁም የአቶ ገመቹ በ2007 .. በጀት ዓመት የሒሳብ ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ በ94 /ቤቶችና በአንድ ቅርንጫፍ መ/ቤት በድምሩ 2 ቢሊየን 78 ስምንት ሚሊየን 949 ሺህ 440 ብር ከ60 ሳንቲም በወቅቱ ሳይወራረድ መገኘቱን ነው።

ከአቶ ገመቹ ዱቢሶ ሪፖርት መረዳት የሚቻለው የሥርዓተ መንግስቱን የፋይናንስ ደንብ፣ ሕግና ሥርዓትን የሚጥሱ ተቋማት ቁጥር እየጨመረ መሄዱን ነው። አጨማመሩ ሲታይ ደግሞ ሥርዓተ መንግስቱ በአብይ ሙስና እያደፈ፣ የመታነቂያው ሸምቀቆ እየጠበቀለት ይመስላል። ዘመዳቸውን ከሕግ አግባብ ውጪ ቀጥረዋል ተብለው በአደባባይ ይሰቀሉ ተብሎ እንዳላየን፣ የቢሊዮን ሙሰኞች መፈልፈያ ሥርዓት መንግስት ሲፈጠር ማየት አስደንጋጭ ነው። በተለይ ከሥርዓት መንግስቱ ጋር የተጣባ ሙስና ከጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች እኩል አደጋ መፍጠር የሚችል ነው።

ከሁሉ በላይ የሚያሳዝነው ግን በታክስ እና በቀረጥ መልክ ከሕዝብ የሚሰበሰብ ገንዘብን በሥርዓት እና በቁጠባ ለዜጎች ማሕበራዊ ፍትህ እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፤ በሥርዓተ መንግስት ውስጥ የተደራጁ ለኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካ ኢኮኖሚ ማበብ ተግተው የሚሰሩ እና የተቀራማች ቢሮክራሲን እና በአደረጃጀታቸው ለዘረጉ ኃይሎች፤ መሞሰኛ መሆኑ በጣም አንገት የሚያስደፋ ተግባር ነው።

በዚህ ጽሁፍም ማንሳት የተፈለገው በከተማችን አዲስ አበባ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አዲስ የግብር ደረጃ አሰጣጥና ክለሳ የተፈጠረውን ሁኔታ ለማመላከት ነው። አንደኛው፣ ከቅሬታ አቅራቢዎች አንድ እንደማሳያ አቅርበናል። ሁለተኛ፣ የታክስ ሠራተኞች ግዴታዎችና ኃላፊነቶች ምን ይመስላል የሚለውን ከአዋጁ አስቀምጠናል። ሶስተኛ፣ በግምት የሚከናወን የታክስ ስሌት ምን ማለት ነው። አራተኛ፣የታክስ እና ይግባኝ የሚቀርብባቸው ውሳኔዎች የመጨረሻ ስለመሆናቸው ናቸው።

የጽሁፉም ዓላማ የገቢዎችና ጉምሩክ ኃላፊዎች አንዳንድ ነገሮች እንዲገነዘቡ የሚያስችል ሲሆን በግብር ከፋዩም በኩል ችግሮች ቢኖሩ እንኳን ያሉትን የህግ አግባብ ቢመለከቷቸው የተሻለ ይሆናል ለማለት ነው። ምን ጊዜም ቢሆን ትልቁን ሰላማችንን እንጂ፣ የሥርዓቱን ጠብደል ሙሰኞች በመመልከት ብቻ ሌላ አማራጭ ማየት የለብንም። አሁን በአለንብት ዘመን ውዱ ነገር፣ ሰላም ነው። መልካም ንባብ።

/ሮ ገነትን እንደማሳያ…..

/ሮ ገነት ግዛቸው በቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ሃያ ሁለት ተብሎ በሚጠራው ሠፈር በአንድ አነስተኛ ክፍል ምግብ በማቅረብ ይተዳደራሉ። አዲሱ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የግብር ክለሳ መደረጉን ተከትሎ በሃዘን እና በብስጭት ውስጥ ቆዝመው ነበር ያገኘኋቸው። የግብር ክለሳው የፈጠረባቸውን ስሜት እና ምክንያታቸውን ክለሳው የፈጠረባቸውን ለውጦች ለማዳመጥ፣ መንግስት የዘረጋው የግብር ክለሳ ጥናት እንዴት አገኙት የሚል ጥያቄ አቀረብኩላቸው
/ሮ ገነት፣ “መንግስት ግብር በመሰብሰቡ ቅሬታ የለኝም። ሆኖም ግን፣ ለመኖር የሚሰራ እና ለማግኘት የሚሰራውን መለየት ያልቻለ የግብር ብይን፤ በርግጥ የመንግስት ፍላጎት ነው የሚል ጥያቄ ግን አለኝ” አሉ።

/ሮ ገነት ቀጠል አድርገው፣ “ትሰማለህ፣ ሶሪያ አንድ አመት ከስምንት ወር ተቀምጬ ነው የመጣሁት። ባዶ እጄን የሀገሬን ፓስፖርት ብቻ ይዤ ነው የተመለስኩት። በሶሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አዋጥተው የሰጡኝን ልብሶች እንኳን ይዤ እንዳልመጣ አሰሪዬ ከልክሎኛል፤ አንድ ልብስ ይዛ የምትሄድ ከሆነ በጥይት እግሯን አፈርሰዋለሁ እያለ ይዝትብኝ ነበር። ጭንቅላቴ ላይ በደረሰብኝ ተደጋጋሚ ድብደባ ተፈልጦ ነበር፤ ለሀገሬ የበቃሁት። አዲስ አበባ እህቴ ጋር ስደርስ፣ ትቼያቸው የሄድኩት ልብሶቼ በፌስታል ተቋጥረው ነው የጠበቁኝ። እህቴም ምንም አልነበራትም። ሁሉም ሰው ለልጆቹ ልብስ ይዞ ሲመጣ፣ አንድ ልብስ ለልጄ መሆን አለመቻሌ በወቅቱ ለከፍተኛ ሃዘን ዳርጎኝ ነበር። መንፈሴም ሞራሌም ልክ አልነበረም። ላገኝ ሄጄ፣ ያለኝን ሁሉ አጥቼ ነው የተመለስኩት። እስካሁን ይህ ሐዘን ከልቤ ሳይወጣ ራሴን ለማሸነፍ ደፋ ቀና ስል አዲስ የግብር አከፋፈል ስለተጀመረ ከደረጃ “ሐ” ወደ “ለ” አድገዋል አሉኝ። ባደረገው፣ በከፈልኳችሁ” የሚል ምላሽ ነበር የሰጠሁት።

ዛሬ ላይ እንዴት እንደደረስኩ እንኳን የኋላ ታሪኬን የማያውቅ ሰው በዓመት 57ሺ ብር ግብር መክፈል አለብሽ ሲል በጣም የሚገርም ብቻ ሳይሆን፤ አስደንጋጭ ነው” አሉ። ወ/ሮ ገነት ቀጠል አደረጉ እና ወንድሜ ትሰማኛለህ፣ “ ሀገሬ ስገባ አማራጭ ስላልነበረኝ፣ አንድ አፍሪካ ባለቤት ያላት እህት ጋር በሀገሬ ምግብ ለማብሰል ሥራ የጀመርኩት። መቼም እግዚያብሔር ይባርካት፣ መልካም የቤት እመቤት ናት። ለአስር ዓመታት በእሷ ቤት ምግብ ሳበስል ነበር የቆየሁት። እንደሰው ልብስ ልልበስ አላልኩም፤ ጸጉሬ ልሰራ አላልኩም፤ የምትሰጠኝን ደሞዝ ለልጄ ማስተማሪያ ብቻ ነበር የማውለው። መቼም የወለደ የልጅን ነገር ያውቀዋል። አሰሪዬ ስታሰናብተኝ አንድ ማቀዝቀዣ ፍሪጅ፣ ሳህንና ብርጭቋዎች፣ የተወሰኑ ወንበሮች ስለሰጠችኝ ነበር፤ ይህንን አነስ ያለ ምግብ ቤት ለመክፈት የበቃሁት። ፈቃድም ከወጣሁ አራት ወር አይሞላኝም። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለሁ ነው፤ የቀን ገቢዎ 2400 ብር ሲሆን አመታዊ ገቢዎ ከ500 ሺህ ብር በላይ መሆኑን እንገልፃለን የሚል ደብዳቤ ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ቦሌ ክ/ከተማ አ/////ቤት የደረሰኝ።”

በምን አይተው ነው 58ሺ ብር የገመቱት። ኖሮኝ ቢሆን፣ ለመንግስታችን ለመክፈል ወደኋላ አልልም። መንግስት ወዴት ይወስደዋል፣ ተመልሶ ለእኛ ነው። በሶሪያ ምድር ስናፍቅ የነበረው ለሀገሬ አፈር መብቃት ብቻ ነበር። አሁን ደግሞ ሀገሬ ጠላሁኝ” …ሳግ…እምባ…ይተናነቃቸው ጀመር…በእኔም ላይ ግራ የሚያጋባ ስሜት ተፈጠረብኝ።

አመታዊ ወጪዎትን ክፍለ ከተማው ስንት ነው የገመተልዎት?” የሚል ጥያቄ አነሳሁ። ወ/ሮ ገነትም፣ “ምንም አልነገሩኝም። በጣም ነው ያዘንኩት። ወዴት ብር ብዬ እንደምጠፋም አላውቅም። ወደሌላ ቦታ ሄጄም እንዳልሰራ ምግብ አቅራቢ ሆኜ የቋጠርኳት ትንሽ ገንዘብም ትበተናለች። የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ከወሰድኩ ገና አራት ወሬ ነው። እነሱ የሚሉት 57ሺ ቀርቶ 1 ሺህ ብር ባንክ አላስቀመጥኩም። የሚገርምህ ምግብ አቅርበህ ዞር ስትል በልቶ ሳይከፍል የሚሰወር ሰው ያለበት። መብራት በፈለከው ጊዜ ይጠፋል። ሥጋ ገዝተህ መብራት ሳይኖር ሲቀር ከፍሪጅ አውጥተህ ትደፋለህ። የቤት ኪራይ አከራዩ ባለህ ነው የምትከፍለው። ከፈልክ ማለት ግን አለህ ማለት አይደለም። ወደፊት ሰርተህ ለመክፈል ካለህ ጉጉት ነው የምታደርገው። ከተማ ውስጥ ቁጭ ብለህ ውሃ አስራ አምስት ብር ቀድተህ ነው የምትጠቀመው። ይህ ቅሬታ የእኔ ብቻ አይደለም። አካባቢውን ዞረህ መመልከት ብቻ በቂ ነው። እያለቀስን ነው። ከፍቶ የሰራ ሰው ብር አለው ማለት አይደለም። እኔ የምሰራው ለማግኘት ወይም ለእድገት አይደለም። የምሰራው፤ ለመኖር ነው። የሰው ፊት ሰልችቶኛል። እያለቀስን ነው። በአረብ ሀገር ያ ሁሉ ድብደባ ሲደርስብኝ አልፌዋለሁ። ሳቅ እንኳን በሀገሬ ላይ ነው የሳኩት።”

ከፌዴራል የታክስ አስተዳደር በአዋጅ ቁጥር 983/2008 የተወሰደ

የታክስ ሠራተኞች ግዴታዎችና ኃላፊነቶች

1. የታክስ ሠራተኞች በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ እና በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀጽ ፳ () በሚሰጠው ውክልና መሠረት ከታክስ ሕጎች አፈፃፀም ሲባል የተሰጠውን ማንኛውንም ሥልጣኑን ሊሠራበት ወይም ማንኛውንም ተግባርና ኋላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።
2.
የታክስ ሠራተኛ በታክስ ሕጎች በተሰጠው ማንኛውም ሥልጣኑ የሚሠራው ወይም ማንኛውንም ተግባርና ኃላፊነቱን የሚወጣው ታማኝነትና ፍትሐዊነትን በተላበሰ መንገድ መሆን የሚገባው ቢሆን ታክስ ከፋዩንም በአክብሮት የማስተናገድ ኃላፊነት አለበት።
3.
የታክስ ሠራተኛ ከሚከተሉት ጋር በተያያዘ ሕጎች የተሰጠውን ሥልጣን ሊሠራበት ወይም ኃላፊነቱን ወይም ተግባሩን ሊያከናውን አይችልም፡

/ የቀረበለት ጉዳይ ከሠራተኛው የግል፣ የቤተሰብ፣ የንግድ፣ የሙያ፣ የቅጥር ወይም የፋይናንስ ግንኙነት ካለው ሰው ጋር የተገናኘ ከሆነ፡
/ በሌላ መልኩ የጥቅም ግጭት የሚያስከትል ከሆነ።

4. የታክስ ሠራተኛ ወይም ሥራው በቀጥታ የሚመለከተው የሚኒስቴሩ ሠራተኛ የታክስ ሂሳብ ሠራተኛ ወይም አማካሪ ወይም የታክስ ማስታወቂያ ለሚያዘጋጅ ወይም ታሱክን አስመልክቶ ምክር ለሚሰጥ ሰው የሂሳብ ሠራተኛ ወይም አማካሪ በመሆን ሊያገለግል ወይም የዚህ ሰው ተቀጣሪ እንዲሆን የቀረበለትን ሃሳብ ሊቀበል አይችልም።

በግምት የሚከናወን የታክስ ስሌት

1. ማንኛውም ታክስ ከፋይ ከታክስ ሕግ መሠረት በማንኛውም የታክስ ጊዜ ማቅረብ የሚገባውንም የታክስ ማስታወቂያ ያላቀረበ እንደሆነ ባለሥልጣኑ በማንኛውም ጊዜ የሚያገኘውን ማስረጃ መሠረት በማድረግ ለታክስ ጊዜው ታክስ ከፋዩ ሊከፍል የሚገባውን ታክስ በግምት (“የግምት ስሌት” ተብሎ የሚጠራ) ማስላት የሚችል ሲሆን የግምት ስሌቱ የሚከተሉትን ይመለከታል፡
/ በፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ ሠንጠረዥ “ለ” ወይም “ሐ” ኪሳራን በሚመለከት የታክስ ጊዜውን የኪሳራ መጠን፣
/ በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ መሠረት በግብዓት ላይ በብልጫ የተከፈለ የተጨማሪ እሴት ታክስን በሚመለከት ለታክስ ጊዜው በግብዓት ላይ በብልጫ የተከፈለውን የታክስ መጠን፣

/ በሌላ ማንኛውም ሁኔታ ዜሮ መጠንን ጨምሮ በታክስ ጊዜው ሊከፈል የሚገባውን የታክስ መጠን፣

2. ባለሥልጣኑ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () መሠረት ታሱ በግምት ለተሰጠው ታክስ ከፋይ የሚከተሉትን ዝርዝር ነጥቦች ያካተተ የታክስ ግምት ስሌት ማስታወቂያ መስጠት አለበት።

/ እንደሁኔታው የተሰላውን የታክስ መጠን፣ ወደፊት የሚሸጋገር የኪሳራ ወይም በብልጫ የተከፈለን የግብዓት ታክስ መጠን፣

/ በተሰላው ታክስ ላይ ሊከፈል የሚገባ የቅጣት መጠን ካለ፤

/ በተሰላው የታክስ መጠን ላይ ሊከፈል የሚገባ የዘገየ ክፍያ ወለድ መጠን ካለ፤

/ የታክስ ስሌቱ የሚመለከተውን የታክስ ጊዜ፣

/ ማስታወቂያው ከተሰጠበት ቀን ጀመሮ በ፴ (በሰላሳ) ቀናት ውስጥ ታክሱ፣ ቅጣቱ እና ወለዱ የሚከፈልበትን ቀን፣
/ ቅሬታ ማቅረብ የሚችልበትን የጊዜ ገደብ ጨምሮ በታክስ ግምት ስሌቱ ላይ ቅሬታውን የሚያቀርብበትን አኳኋን።

3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () መሠረት የሚሰጠው የታክስ ግምት ስሌት ማስታወቂያ ታክሱን በሚጥለው የታክስ ሕግ መሠረት በተዘጋጀው የታክስ ግምት ስሌት ሊከፈል የሚገባው ታክስ የሚከፈልበትን ጊዜ (“የመጀመሪያው የታክሰ መክፈያ ጊዜ” ተብሎ የሚጠቀስ) ሊለወጥ የማይችል ሲሆን፤ የታክስ ክፍያው በመዘግየቱ ምክንያት የሚጣል ቅጣትና ወለድ መታሰብ የሚጀምሩት ከመጀመሪያው የመክፈያ ጊዜ አንስቶ ይሆናል።

4. ይህ አንቀጽ ተፈፃሚ የሚሆነው በታክስ ስሌት ለሚሰበሰብ ታክስ ብቻ ነው።

5. ይህ አንቀጽ በባለሥልጣኑ የተዘጋጀ የታክስ ግምት ስሌት የደረሰው ማንኛውም ታክስ ከፋይ የግምት ስሌቱ የሚመለከተውን የታክስ ማስታወቂያ የማቅረብ ግዴታውን አያስቀርም።

6. በባለሥልጣኑ የተዘጋጀ የታክስ ግምት ስሌት ማስታወቂያ ለታክስ ከፋዩ ከደረሰው በኋላ ለዚያ የታክስ ጊዜ ታክስ ከፋዩ የሚያቀርበው የታክስ ማስታወቂያ ለታክስ ጊዜው እንደቀረበ በታክስ ከፋዩ የተዘጋጀ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ ሆኖ አይቆጠርም።

7. ባለሥልጣኑ በማንኛውም ጊዜ በግምት ላይ የተመሠረተ የታክስ ስሌት ሊያዘጋጅ ይችላል።

8. ባለሥልጣኑ ለዚህ አንቀጽ አፈፃፀም የሚያግዙ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል።

የታክስ እና ይግባኝ የሚቀርብባቸው ውሳኔዎች

የመጨረሻ ስለመሆናቸው

1. በዚህ ክፍል በተደነገገው ሥነ ሥርዓት መሠረት ካልሆነ በስተቀር፡
/ የታክስ ወይም ይግባኝ ሊቀርብበት የሚችል ውሳኔ ወሳኝ እና የመጨረሻ በመሆኑ በማናቸውም ሁኔታ በኮሚሽኑ ወይም በፍርድ ቤት ወይም በሌላ የዳኝነት ሥነሥርዓት ተቃውሞ ሊቀርብበት አይችልም፣
/ የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ወይም ውሳኔ ወይም በባለሥልጣኑ እንደ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ ወይም ውሳኔ ቅጂ የተረጋገጠ ሰነድ ማቅረብ የታክስ ስሌት ማስታወቂያው ወይም ውሳኔው በአግባቡ የተሰጠ በመሆኑ እንዲሁም በታክስ ስሌት ማስታወቂያው ወይም ውሳኔው የተመለከተው የታክስ መጠን እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ትክክለኛ ስለመሆናቸው ወሳኝ ማስረጃ ነው። እንዲሁም
/ ታክስ ከፋዩ ራሱ የሚያሰላውን ታክስ በተመለከተ ታክስ ከፋዩ ራሱ ያሳወቀበትን ዋናውን የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ ወይም በባለሥልጣኑ እንደራስ ታክስ ስሌተ ማስታወቂያው ዋናው ቅጂ የተረጋገጠ ሰነድ ማቅረብ ስለማስታወቂያው ይዘት ወሳኝ ማስረጃ ነው።

2. ባለሥልጣኑ ለታክሰ ከፋይ የታክስ ስሌት ወይም ውሳኔ ማስታወቂያ በኤሌክትሮኒክ ዘዴ በሚሰጥበት ጊዜ፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () () የተመለከተው የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ወይም ወሳኔ ቅጂ ማስታወቂያውን ወይም ውሳኔውን በመለየት እና በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የተላለፈውን የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ወይም ውሳኔ ዝርዝር ጉዳዮች በመግለጽ በባለሥልጣኑ የተረጋገጠን ሰነድ ይጨምራል።

3. ታክሰ ከፋይ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ በኤሌክትሮኒክ ዘዴ በሚያቀርብበት ጊዜ፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () () የተመለከተው የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ ቅጂ ማስታወቂያውን በመለየት እና በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የተላለፈውን የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ ዝርዝር ጉዳዮች በመግለጽ በባለሥልጣኑ የተረጋገጠን ሰነድ ይጨምራል።

4. ለዚህ አንቀጽ ዓላማ “ውሳኔ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪(፴፬) ለታክስ ውሳኔ በተሰጠው ትርጉም ሥር በፊደል ተራ ()()()()() ወይም () የተመለከተውን ነው።

በታክስ ውሳኔ ላይ ስለሚቀርብ የቅሬታ ማስታወቂያ

  1. በታክስ ውሳኔ ቅር የተሰኘ ታክስ ከፋይ የውሳኔውን ማስታወቂያ በደረሰው በ፳፩ (በሃያ አንድ) ቀናት ውስጥ ውሳኔው ላይ የቅሬታ ማስታወቂያ ለባለሥልጣኑ በጽሑፍ ማቅረብ ይችላል

    2. ቅሬታ የቀረበበት የታክስ ውሳኔ በተሻሻለ የታክስ ስሌት ላይ ከሆነ የታክስ ከፋዩ የተሻሻለውን የታክስ ስሌት የመቃወም መብት የመጀመሪያውን የታክስ ስሌት በመለወጥ፣ በመቀነስ ወይም በመጨመር በተደረገው ማሻሻያ ላይ ብቻ የተገደበ ይሆናል።
    3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () መሠረት በታክስ ከፋይ የቀረበ የቅሬታ ማስታወቂያ በአግባቡ እንደቀረበ የሚቆጠረው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ቅድመ ሁኔታዎች ሲሟሉ ብቻ ነው

    / የቅሬታ ማስታወቂያው ታክስ ከፋዩ የታክስ ውሳኔውን የሚቃወምበትን ምክንያቶች፣ ታክስ ከፋዩ ውሳኔውን ለማስተካከል ሊደረጉ ይገባል ብሎ የሚያምንባቸውን ማሻሻያዎች እና እነዚህን ማሻሻያዎች ማድረግ አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያቶች በትክክል የሚገልጽ ከሆነ፣

    / ቅሬታው ከታክስ ስሌት ጋር የተገናኘ ከሆነ ታክስ ከፋዩ በታክስ ስሌቱ መሠረት መከፈል ያለበትን እና በቅሬታ ማስታወቂያው ተቃውሞ ያላቀረበበትን ታክስ የከፈለ እንደሆነ፤ እንዲሁም

    / በታክስ ውሳኔው ላይ ቅሬታ ቢኖረውም ታክሱን ከፍሎ የቅሬታ ማስታወቂያ ማቅረብን የመረጠ ከሆነ የተወሰነበት ታክስ ከከፈለ ነው።

    1. ባለሥልጣኑ የቅሬታ ማስታወቂያው በአግባቡ አልቀረበም ብሎ ሲያምን ለታክስ ከፋዩ የሚከተሉትን የሚገልጽ የጽሑፍ ማስታወቂያ ወዲያውኑ ይሰጠዋል፡

/ ቅሬታው በአግባቡ አልቀረበም የሚልባቸውን ምክንያቶች፤ እና

/ ከሚከተሉት በዘገየው ጊዜ ውስጥ ታክስ ከፋዩ ቅሬታውን ካላቀረበ የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ እንደሚያልፍ፡
(1) ቅሬታው የሚመለከተው የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ በደረሰው በ፳፩ (በሃያ አንድ) ቀናት ውስጥ፤ ወይም
በዚህ ንዑስ አንቀጽ መሠረት የሚሰጠው ማስታወቂያ በደረሰው በ፲ (በአሥር) ቀናት ውስጥ።

2 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () መሠረት የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ያለፈ ከሆነ ባለሥልጣኑ ይህንን የሚገልጽ የጽሁፍ ማስታወቂያ ለሚመለከተው ታክስ ከፋይ ይሰጣል።

3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () የተመለከተው የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ከማለፉ በፊት ታክስ ከፋዩ በታክስ ውሳኔ ላይ የቅሬታ ማስታወቂያ የሚያቀርብበት ጊዜ እንዲራዘምለት ለባለሥልጣኑ የጽሁፍ ማመልከቻ ማቅረብ ይችላል።
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () መሠረት ማመልከቻ ሲቀርብ፤ ባለሥልጣኑ፡

/ ታክስ ከፋዩ በኢትዮጵያ ውስጥ ያልነበረ በመሆኑ፤ በህመም ምክንያት ወይም በሌላ አጥጋቢ ምክንያት በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ () ወይም () በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የቅሬታ ማስታወቂያውን ማቅረብ አለመቻሉ፤ እና 
/ የቅሬታ ማስታወቂያውን ለማቅረብ በታክስ ከፋዩ በኩል ምክንያታዊ ያልሆነ መዘግየት አለመኖሩን፤
ሲያምንበት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () የተመለከተው የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜው ካበቃበት ቀን ጀምሮ ከ፲ (ከአሥር) ቀናት ላልበለተ ጊዜ ሊያራዝም ይችላል።

በቅሬታ ላይ ውሳኔ ስለመስጠት

  1. ባለሥልጣኑ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶፬ መሠረት በአግባቡ የቀረቡ ቅሬታዎችን በነፃነት በመመርመር በቅሬታዎቹ ላይ ለሚሰጠው ውሳኔ የውሳኔ ሃሳብ የሚያቀርብ ቋሚ የሥራ ክፍል ያቋቁማል።

    2. ባለሥልጣኑ፣ ቅሬታዎች የሚታዩበትን ሥነ ሥርዓት እና ለባለሥልጣኑ የሚቀርቡ የውሳኔ ሃሳቦች የሚመሠረቱባቸውን ጉዳዮች እና የውሳኔ አሰጣጡን ሥርዓት የያዘ ዝርዝር መመሪያ ያወጣል።

    3. የሥራ ክፍሉ በታክስ ስሌት ላይ የቀረበውን ቅሬታ ሲመረምር በታክስ ስሌቱ የተመለከተው የታክስ መጠን ሊጨምር ይገባል የሚል እምነት ሲኖረው፣ የሥራ ክፍሉ የታክስ ስሌቱ ለሚመለከተው የታክስ ሠራተኛ ተመልሶ እንደገና እንዲታይ የውሳኔ ሃሳብ ለባለሥልጣኑ ማቅረብ ይኖርበታል።

    4. ባለሥልጣኑ በሥራ ክፍሉ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ከመረመረ በኋላ፣ የቀረበውን ቅሬታ በሙሉ ወይም በከፊል በመቀበል ወይም ውድ በማድረግ ውሳኔ የሚሰጥ ሲሆን ውሳኔውም “በቅሬታ ላይ የተሰጠ ውሳኔ” ተብሎ ይጠቀሳል።
    5. ባለሥልጣኑ በቅሬታ ላይ የሰጠውን ውሳኔ ለታክስ ከፋዩ በጽሑፍ የሚያሳውቀው ሲሆን፣ በታክስ ስሌት ላይ የቀረበ ቅሬታ ከሆነ የታክስ ስሌቱን ማሻሻልን ጨምሮ ውሳኔውን ለማስፈፀም አስፈላጊ የሆኑትን እርምጃዎች ይወስዳል።

  1. በቅሬታ ላይ የተሰጠ ውሳኔ ማስታወቂያ የጉዳዩን ዋና ፍሬ ነገሮች፣ ግኝቶች እና ለውሳኔው መሠረት የሆኑትን ምክንያቶች እና ለኮሚሽኑ ይግባኝ ማቅረብ እንደሚቻል የሚገልፅ መግለጫ ማካተት አለበት።

    7. ታክስ ከፋዩ ቅሬታ ካቀረበበት ቀን ጀምሮ ባሉት ፻፹ (አንድ መቶ ሰማንያ) ቀናት ውስጥ ባለሥልጣኑ በቅሬታው ላይ ውሳኔ ካልሰጠ ታክስ ከፋዩ ይግባኙን ፻፹ (አንድ መቶ ሰማንያ) ቀን በተጠናቀቀ በ፴ (በሰላሳ) ቀናት ውስጥ ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ማቅረብ ይችላል።

ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ይግባኝ ስለማቅረብ

  1. ይግባኝ ሊቀርብበት በሚችል ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ታክስ ከፋይ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፹፷ መሠረት የይግባኝ ማስታወቂያውን ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ሊያቀርብ ይችላል።

    2. በታክስ ስሌት ላይ ከቀረበ ቅሬታ ጋር በተገናኘ በታክስ ከፋይ ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የሚቀርብ የይግባኝ ማስታወቂያ በአግባቡ ቀርቧል ሊባል የሚችለው በክርክር ላይ ያለ ታክስ ፶% (ሃምሳ በመቶ) የተከፈለ እንደሆነ ብቻ ነው።
    3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () “በክርክር ላይ ያለ ታክስ” ከታክሱ ጋር በተገናኘ ሊከፈል የሚገባውን ቅጣትና የዘገየ ክፍያ ወለድን አይጨምርም።

    4. የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () መሠረት የይግባኝ ማስታወቂያ የሚቀርብበት ጊዜ እንዲራዘም ስለሚቀርብ ማመልከቻ መመሪያ ሊያወጣ ይችላል።

ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ስለማቅረብ

  1. ለኮሚሽኑ በቀረበ የታክስ ይግባኝ ተካፋይ የነበረ ሰው ኮሚሽኑ በሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ እንደሆነ የኮሚሽኑ የውሳኔ ማስታወቂያ በደረሰው በ፴ በ(ሠላሳ) ቀናት ውስጥ የይግባኝ ማስታወቂያውን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ይችላል።
    2. በኮሚሽኑ በታየ የታክስ ይግባኝ ላይ ተከራካሪ የነበረ ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () የተመለከተው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ እንዲራዘምለት በጽሑፍ ማመልከቻ ሲጠይቅ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጊዜውን ሊያራዝመው ይችላል።
    3. በታክስ ስሌት ላይ ከቀረበ ቅሬታ ጋር በተገናኘ በታክስ ከፋይ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚቀርብ የይግባኝ ማስታወቂያ በአግባቡ ቀርቧል ሊባል የሚችለው በክርክር ላይ ያለ ታክስ ፸፭% (ሰባ አምስት በመቶ) የተከፈለ እንደሆነ ብቻ ነው።

    4. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ የሚቀርበው በሕግ ጉዳዮች ላይ ብቻ ሲሆን የይግባኝ ማስታወቂያውም በቀረበው ይግባኝ የሚነሱትን የሕግ ጉዳዮች መግለፅ አለበት።

    5. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኙን በማሰማት፡

    / የኮሚሽኑን ውሳኔ ሊያጸናው፣

    / የኮሚሽኑን ውሳኔ በመሻር፡

    () የኮሚሽኑን ውሳኔ የሚተካ ውሳኔ ሊሰጥ፤ ወይም

    () ፍርድ ቤቱ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ጉዳዩ እንደገና እንዲታይ ለኮሚሽኑ ወይም ለባለሥልጣኑ መልሶ ሊልከው፤ ወይም 
    / ይግባኙን ውድቅ ሊያደርገው፤ ወይም 

    / ተገቢ መስሎ የታየውን ሌላ ውሳኔ ሊሰጥ፤ ይችላል።

    6. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ () “በክርክር ላይ ያለ ታክስ” ማለት የታክስ ይግባኝ ኮሚሽኑ እንዲከፈል ውሳኔ የሰጠበት እና ታክስ ከፋዩ በይግባኝ ማስታወቂያ ቅሬታ ያቀረበበት ታክስ ሲሆን ከታክሱ ጋር በተገናኘ ሊከፈል የሚገባውን ቅጣትና የዘገየ ክፍያ ወለድን አይጨምርም።

ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስለሚቀርብ ይግባኝ

1. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረበ የታክስ ይግባኝ ተካፋይ የነበረ ሰው ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውስኔ ቅር የተሰኘ እንደሆነ የፍርድ ቤቱ የውሳኔ ማስታወቂያ በደረሰው በ፴ (በሠላሳ) ቀናት ውስጥ የይግባኝ ማስታወቂያውን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ይችላል።
2. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በታየ የታክስ ይግባኝ ላይ ተከራካሪ የነበረ ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () የተመለከተው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ እንዲራዘምለት በጽሁፍ ማመልከቻ ሲጠይቅ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጊዜውን ሊያራዝመው ይችላል።

የማስረዳት ኃላፊነት

በዚህ ክፍል መሠረት ከታክስ ውሳኔ ጋር በተገናኘ በሚደረግ ማንኛውም የታክስ ክርክር ሂደት የታክስ ውሳኔ ትክክል አለመሆኑን የማስረዳት ኃላፊነት የታክስ ከፋዩ ነው።

የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ወይም የፍርድ ቤትን ውሳኔ ስለመፈፀም

  1. ባለሥልጣኑ የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወይም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ በደረሰው በ፴ (በሠላሳ) ቀናት ውስጥ የተሻሻለ የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ለታክስ ከፋዩ መስጠትን ጨምሮ፣ ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ አለበት።

    2. በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፷ ተመለከተው የተሻሻለ የታክስ ስሌት የጊዜ ገደብ የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ወይም የፍርድ ቤት ውሳኔን ተግባራዊ ለማድረግ በሚከናወን የታክስ ስሌት ማሻሻያ ላይ ተፈፃሚ አይሆንም። 

    ስንደቅ