July 20, 2017

ቆንጅት ስጦታው 

አማራ ክልል ግብር ለህዝብ ይፋ እንዳይሆን ትእዛዝ ተሰጠ።

ወያኔ በኦሮሚያ የተነሳበትን ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ ሌሎች ከተሞች እንዳይስፋፋበት በአማራ ክልል የተጠናውን የነጋዴዎች የቀን ገቢ ግምት እንደ ኦሮሚያ ህዝብ ለተቃውሞ ይነሳብኛል በሚል ለአማራ ክልል መንግስት ወያኔ ትእዛዝ ሰጥቷል ፡፡

ነጋዴው በተገመተው የቀን ገቢ ግብር ተመን መሰረት ምን ያህል እንደሚከፍል እስካሁን ሊነገረው ይገባ ነበር ሆኖም ወያኔ ከፍራቻው የተነሳ የግብር ተመኑ ለህዝብ እንዳይነገር ነው ያደረገው ፡፡ ግብር ለመክፈል ነጋዴው በራሱ መጥቶ ልክፈል እስካላለ ድረስ ማንኛውም ገቢዎች ሰራተኛ ነጋዴውን ግብር ክፈል ብሎ እንዳይጠይቅ የሚል ሲሆን ወያኔ ሁሌም አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ ከጭንቅ ለመውጣት ከሚያደርጋቸው ነገሮች ውስጥ ህዝብን ከህዝብ ለማጣላት ሲጥር እንደነበር ይታወቃል ይህ የአሁኑ አካሄዱም ከዚህ የተለየ አይደለም ሌሎች አካባቢዎች በግብር ምክንያት አመፁ ሲቀጣጠል የአማራ ክልል ህዝብን ግብር አለማስከፈል እና አመፁ የተቀጣጠለባቸው አካባቢዎች መቆጣጠር እስኪችል ድረስ የአማራን ክልል ህዝብ ለማዘናጋት የሚጠቀመው ዘዴ እንጂ ወያኔ እደዘንድሮ በገንዘብ እጦት ችግር ውስጥ ገብቶ አያውቅም ስለዚህ የግብሩን ሁኔታ ለጊዜው የተወው ለማስመሰል እየሞከረ ይገኛል ፡፡