JULY 27, 2017

አሜሪካ አምርራለች” በሚሉና ” አሜሪካ ምን ታመጣለች” በማለት በሚከራከሩ ወገኖች መካክል የብዕር ጦርነቱ ከፍተኛ ነበር። ኢህአዴግም ቢሆን በውስጥ ጉዳዩ ማንም እጁን ሊጠመዝዘው እንደምይችል በተደጋጋሚ አስታውቋል። የኒውጀርሲው እንደራሴ ክሪስ ስሚዝ ቀድሞ ከነበራቸው አቋማቸው ሳይላዘቡ ” በሽብርተኛች ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር መስራት ዜጎችን ለማሰቃየት ዋስትና አይሆንም” ሲሉ ድምጻቸውን አጉልተው አሰሙ።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይህንኑ ጉዳይ አስቀደሞ ለመከላከል በየወሩ  ከፍተኛ ገንዘብ የሚከፍላቸውን ሎቢስቶች ቀጥሮ የሚችለውን ሲያደርግ ቆየ። የተጋነነ ገንዘብ ስለመክፈሉ ተጠይቆም ” ያለና የተለመደ አሰራር ነው” በሚል በአምባሳደር ግርማ ብሩ በኩል ማስተባበያ በመስጠት ስራውን ከሎቢስቶቹ ጋር ቀጠለ።

አገሪቱ እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነች፤ … ስልጣን የመስጠት አጋጣሚ ይመጣል’ቶም ማሊኖውስኪ

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የዴሞክራሲ፣ የሠብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ በዚሁ በሰብአአዊ መብቶች ዙሪያ ከሚፈለጉት ባለስልጣናት ጋር ከተነጋገሩ በሁዋላ ” እንደ ወዳጅ መክረናል”  ” ሁሉም ነገር በኢህአዴግ እጅ ነው። አገሪቱ እንደሚንተከተክ ማሰሮ ነች” የሚል ማጠቃለያ ሰጡ ። አነጋገራቸው ጨው ለራስህ ስትል አይነት ነበር። በወቅቱ ኤምባሲው የተለሳለሰ መግለጫ አውጥቶ ስለነበር ብዥታ የተፈጠረ ቢመስልም ” የአሜሪካኖቹ አካሄድ እንደዚህ ነው” በማለት በእርጋታ መጠበቁ እንደሚሻል የተናገሩ ነበሩ።

በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ የተወሰደው የሃይል ርምጃ “የተጋነነ ነው” በሚል የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሺነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን  ለአራት ቀናት  አዲስ አበባ ቆይተው በድጋሚ ጉዳዩ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠየቁ ፣ እሳቸውም ማየት የምፈልጉትን ቦታና ለማነጋገር የፈለጉዋቸውን  ሁሉ በነጻነት ማየትና መግኘት እንዳልቻሉ መደረጉን ይፋ አደረጉ። በስተመጨረሻ ” የማታ ማታ የዚህችን አገር መጺአ እድል ለማበጅት ርምጃ መውሰድ ያለባት መንግስት ብቻ ነው” የሚል መግለጫ ሰጡ።

ኮሚሽነር ዛይድ አዲስ አበባ  የተጠሩት የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ” ገለልተኛ ሆኜ አጣራሁት” ያለውን ሪፖርት ይፋ ካደርገ በሁዋላ ነበር። የኮሚሽኑ ሪፖረት ሲቀርብ ” ኢህአዴግ ገደለ፣ ኢህአዴግ አሰረ፣ ኢህአዴግ አጣራ፣ ኢህአዴግ ፓርላማ ሆኖ ሰማ፣ ራሱ በራሱ ለራሱ ወሰነ፤ ይህንን ድራማ አንቀበለውም” በሚል ተቃዋሚ ሃይሎች እና የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ቅሬታቸውን በሚያሰሙበት ወቅት መሆኑ አይዘነጋም።

ሂውማን ራይትን ጨምሮ በርካታ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የአውሮፓ ኮሚሽን፣ ስርስር እየተከታተሉ የሚያቀርቡት ሪፖርተና በቪዲዮ የተደገፉ መረጃዎች ፣ እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች ይፋ የሚሆኑት ሰነዶች ፋይዳቸው ምስክር ወደ ማያስፈልገበት ደረጃ ደረሰ። ዶክተር አዲሱ የሚመሩት የሰባዊ መብት ኮሚሽን ብቻ ስልታዊ ድጋፍ ሲሰጥ የተቀሩት ሁሉ በተደጋጋሚ አወገዙ።

Image result for susan rice

በአሜሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ሚዲያዎች የኢትዮጵያን ጉዳይ ከተራ አስተያየትና ዜና አልፈው ርዕሰ አነቀጽ አደረጉት። የሚዲያዎቹ ዱላ የአሜሪካ አቋም  እንደተቀየረ የሚያሳዩ ምልክቶች እነድሆኑ ጸሃፍቶች የራሳቸውን ጽንፍ በሚያሳይ መልኩም ቢሆን በስፋት ተቹበት። ከዚህም  በላይ ሶማሊያ ያለው የኢትዮጵያ ጦር በድንገት ለቆ መውጣቱ ተሰማ። እንደወትሮው ብዙም እሹሩሩ እንዳልነበር ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ጠቆሙ። በዚሁ መካከል አሜሪካ አዲስ አስተዳደር ሰየመችና እነ ሱዛን ራይስ ወደ ጎን ተባሉ። ሌሎችም ለኢህአዴግ የሚወገኑ እንደሆኑ የሚታሙ  ሃላፊዎች ተነሱ።

ይህ ሁሉ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝ ጉዳይ ሙጢኝ ያለው ህግ መንገዱን እንደያዘ ነበርና  ዛሬ 27.07.17 ሃሙስ  በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ በሙሉ ስምምነት አልፏል ።  አጀንዳወ ሂዝቦላን ጨምሮ ከዘጠኝ አገሮች ጋር ጎን ለጎን መታየቱ ደግሞ አሜሪካንና ኢህአዴግ ወዴት የሚያሰኝ አድርጎታል። በረቂቅ ህግነት በሙሉ ድምጽ ያለፈው አዋጅ ወደ እንደራሴዎች ምክርቤት ቀርቦ ድምጽ እንዲሰጥበት ይደረጋል፡፡

   የአሜሪካ ሬዲዮ ዘጋቢ ሄኖክ ሰማእግዜር ከስፍራው የሚከተለውን ዘግቧል።

የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳድርን የሚወቅስ የህግ ረቂቅ ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ በሙሉ ስምምነት አልፏል። ለሙሉ ኮሚቴው ከቀረቡት ዘጠኝ የሕግ ረቂቆች አንዱ የሆነው ውሳኔ 128 በኒው ጀርሲው እንደራሴ ክሪስ ስሚት እና ከ50 በላይ የተወካዮች ምክር ቤቱ አባላት የደገፉት ነው።

የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴው የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት እንደራሴው ክሪስ ስሚዝ ባሰሙት ቃል “ኢትዮጵያ ጠቃሚ ወዳጅና በዓለም አቀፍ ሰላም ጥበቃ ውስጥም አጋር ብትሆንም እየቀጠሉ ያሉት የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎች ፈፅሞ ተቀባይነት የላቸው” ብለዋል።

“በፀጥታ ኃይሎች የሚፈፀሙ የዘፈቀደ እሥራቶች፣ ግድያዎችና የማሰቃየት አድራጎቶች፣ በመናገርና በመደራጀት ነፃነቶች ላይ እየተጣሉ ያሉ እገዳዎች፣ በተቃዋሚዎችና በጋዜጠኞች ላይ የሚካሄዱ በፖለቲካው የሚመሩ የፍርድ ሂደቶች፣ የማዋከብና የማሸማቀቅ ድርጊቶች …. ሪፖርቱን ስታነብቡት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የቀረበ ክሥ ዓይነት ነው” ብለዋል ሊቀመንበሩ አክለው።

ለሙሉው ዘገባ የተያያዙትን የድምፅና የቪድዮ ፋይሎች ይክፈቱ⇓

https://ethiopanorama.comwp-content/uploads/2017/07/b80f53e2-0c7f-47b6-9dad-abb05b16bdb0_48k-1.mp3