July 28, 2017

(ቪሮኒካ መላኩ)

ሙስና ታሰሩ የተባሉት የመንግስት ባለስልጣኖች ስማቸው ባይጠቀስም ከስኳር ፕሮጄክቶች ጋር የተያያዘ እንደሆነ ታውቋል።

ይሄ እስር የተፈፀመው ስኳር ፕሮጄክትን በማክሰር የተጠረጠሩ ሌቦች ከሆኑ አባይ ፀሃዬንና እነ ጄነራል ክንፈ ዳኜው የሚባሉት የሜቴክ የመከላከያ ጄኔራሎች ከሌሉበት አስቂኝ እና የታሰሩት ምስኪኖች ፈረንጆቹ Scapegoat እንደሚሉት ምስኪን ናቸው ማለት ነው።

ስኳር ፕሮጄክንት እንድመራ በመለስ ዜናዊ የተሾመውና ከ50 ቢሊዮን ብር በላይ እንደ ጫት የቃመው አባይ ፀሃዬ ሲሆን የስኳር ፋብሪካዎችን እንድገነቡ ኮንትራቱ የተሰጣቸው ደሞ የሜቴክ ጄነራሎች ናቸው።

አይሁዳውያን አንድ ባህል አላቸው ራሳቸው የሰሩትን ሃጢያት እና ወንጄል የሚሸከምላቸው ፍዬል ይፈልጉና ፍየሉን አርደው ደሙን ደጃቸው ላይ ያፈሱታል ። የሰውዬውን ወንጀል በፍየሉ ደም ታጥቦ ይሄዳል ብለው ያምናሉ።

ሰውየው የሰራው ወንጀል ምንም የማያውቀውን ምስኪን ፍየል አንገቱን በጥሰው ደሙን በማፍሰስ ከወንጀሉ ነፃ ይሆናሉ። ሃበሻም የሰራውን ሃጢያት የዶሮ አንገት በካራ በመበጠስነ ደሙን በማፍሰስ ራሱ የሰራውን በዶሮ ያላክካል። ይሄንም “የጦስ ዶሮ ” ይሉታል።

የዛሬዎቹስ ስለእነ አባይ ፀሃዬ እና የሜቴክ ጄኔራሎችን ሲባል የተሰየፉት “ፍየሎችና ” እና የጦስ ዶሮዎች ” እነማን ይሆኑ?