Skip to content
የመቐለ ከነማ ደጋፊዎች እየታሰሩ ነው !
÷÷÷÷÷÷÷ Amdom G/Slassie…. Arena ….

የመቐለ ቡድን ደጋፊዎች በድህንነት እየታደኑ እየታሰሩ ነው። እስካሁን 61 ዋናዋና ደጋፊዎች ናቸው የተባሉ ወጣቶች ታስረዋል።
የእስራቸው ምክንያት መቐለ ስቴድዮም ቡዱናቸው ለመቀበል በተዘጋጀው ስነስርዓት ላይ ኣባይ ወልዱ፣ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ ኣቶ ኣለም ገብረዋህድ(የህወሓት ፅህፈት ቤት ሓላፊና ፅራ ኣስፈፃሚ ኣባል)፣ ኣቶ ዳንኤል ኣሰፋ(የመቐለ ከንቲባና የድህንነት ሃላፊ ጌታቸው ወንድም)ወይዘሮ ቅድሳን ነጋ(የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባልና የክልሉ ፓርላማ ኣፈጉባኤና የስብሓት ነጋ እህት)ና ሌሎች ቱባ የህወሓት ባለስልጣናት ባሉበት “ሌባ ሌባ ሌባ ውሸታም ውሸታም ውሸታም ” ብላቹ ህወሓትን ሰድባቹሃል፤ ባለስልጣኖቻችን ኣዋርዳቹሃል፣ ደፍራቹሃል፤ ዓረና የላካቹ ናቹ” የሚል ክስ እየተነገራቸው ከየቤታቸው እየተለቀሙ ታስረዋል።
የትግራይ ክልል ፀጥታ ሃይሎች በመቐለና ወልዋሎ ጨዋታ ከመካሄዱ ሶስት ቀን ቀደም ብሎ ረብሻ እንዳይፈጥሩ በማለት በርካታ ወጣቶች ኣስሮ ነበር።
ከ700 በላይ የመቐለ ቡዱን ደጋፊ ወጣቶች ድሬ ደዋ ድረስ ሄደው ክለባቸውን ደግፈዋል።
ከነዚህ ምርጥ ደጋፊዎች 61 ወጣቶች በፀረ ህወሓትነት ተጠርጥረው በድህንነት እየተለቀመ እየታሰሩ ይገኛሉ።
የመቐለ ቡዱን ደጋፊ ጀግና ወጣቶች ኣትንኩ !
Like this:
Like Loading...