July 29, 2017 –

 ቆንጅት ስጦታው 

በጉጂና በአማሮ ነዋሪዎች መካከል ለተነሳው ግጭት ተጠያቂው የሕወሓት አገዛዝ መሆኑ ተገለፀ ።

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ የተነሳው ግጭት እጅግ አሳሳቢም መሆኑን በአከባቢው የሚኖሩ የመንግስት ሰራተኞች ይናገራሉ ። በምዕራብ ጉጂ ዞን በመንግስት ስራ ላይ የሚገኝና ለአስተዳደሩ ቅርብ የሆነ ሰው እንደገለፀው የምዕራብ ጉጂ ዞን ጽሕፈት ቤት ከጉጂ ለሚነሱና አማሮን ለወረሩ ታጣቂዎች የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ በአከባቢው የሰፈረው የሕወሓት ሰራዊት የጥይት እና ቦምብ ድጋፍ ሲያደርግ የወረራ ስትራቴጂም አስተምሯቸዋል ። ከአማሮ ነዋሪዎች ቀድሞ ጥቃት ከተከሰተ የመከላከል እርምጃ የሚወስደው በመከላከያ ሰራዊት ስም በቦታው የሰፈረው የሕወሓት ጦር ነው ።

የጉጂ ታጣቂዎች በአከባቢው ከሚገኘው የሕወሓት ሰራዊት መኮንኖች እንዲሁም ከመስተዳደሩ ኃላፊዎች ጋር የስልክ ግንኙነት እንደሚያደርግ የቅርብ ሰው የሆኑት የመንግስት ሰራተኛው ለምንሊክ ሳልሳዊ ይናገራሉ ። የጉጂ ታጣቂዎች ድንገተኛ ጥቃት እንዲፈፅሙ ጥቃቱንም ፈፅመው እንዲያመልጡ ከስትራቴጂ ጀምሮ ድጋፍ ይደረግላቸዋል ።

በአማሮ ወረዳ በአንድ ጥቃት ብቻ ዶርባዴ ፣ ጃሎ እና ሻሮ የተሰኙ ሶስት መንደሮች በሕወሓት በሚመሩ የጉጂ ታጣቂዎች መቃጠላቸውን የራሳቸው ሰው የሆነው የጉጂ መስተዳደር ሰራተኛ ይናገራል ፤ በትንሹ አስር የአማሮ ነዋሪዎችም መገደላቸውን ጨምሮ ይገልፃል ፤ የሕወሓት መንግስት ይህን ግጭት ለምን አላማ ፈለገው ሲል በቁጭት ይጠይቃል ፤ የመስተዳደሩ ሀላፊዎች ትእዛዝ ከማስፈፀም ውጪ ስለ ግጭቱ መባባስ ምንም መረጃ እንዳሌላቸው ይገልፃል ።

ምንሊክሳልሳዊ