Written by  አለማየሁ አንበሴ

አዋጁ ለተጨማሪ ጊዜያት እንዳይራዘም ፓርቲው ጠይቋለ

ከታወጀ 10 ወር ገደማ ያስቆጠረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከ5 ቀን በኋላ ይነሳ ይቀጥል የሚታወቅ ሲሆን  ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ፤የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተነሳ፣ ሐምሌ 30 እና ነሐሴ 7 ቀን 2009 .ም፣ በአዲስ አበባ ህዝባዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት ማቀዱን አስታውቋል፡፡ ፓርቲው ሰሞኑን ባወጣው ወቅታዊ የአቋም መግለጫው፤አስር ወራትን ያስቆጠረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የማብቂያው ጊዜ ከ5 ቀን በኋላ፣ መሆኑን በመጠቆም፣ አዋጁ ለተጨማሪ ጊዜያት እንዳይራዘም መንግስትን ጠይቋል፡፡ አዋጁ ተጥሎ በቆየባቸው ጊዜያት፤ “የዜጎችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የጣሰ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ያጠበበ፣ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲያሽቆለቁል ያደረገና የህዝብን ማህበራዊ መስተጋብሮች የገታ ነበር” ያለው ሰማያዊ፤ “መንግስት ሀገሪቱን አረጋግቻለሁ ስላለ አዋጁን ማራዘም አያስፈልግም፤ ሊነሳ ይገባዋል” ብሏል፡፡