July 31, 2017 07:41

 

አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ(አባባ ተስፋዬ)
አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ(አባባ ተስፋዬ)

ጤና ይስጥልኝ ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች እንደምን አላችሁ ልጆች አያችሁ ልጆች የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ክፍለ ጊዜ ዝግጅት እናንተን ለማስደሰት ልክ በሰአቱ ይገኛል አባባ ደሞ የልጆች ሰአት እንዳያልፍባቸው በሩጫ ዲ ዲ ዲ ከተፍ እናንተ ደግሞ ቆማችኃል ይሄ በጣም ጥሩ ነው ልጆች አንድ አባት ሲመጣ በአክብሮት መነሳት አስፈላጊ ነው
***
ደህና ሁኑ ልጆች! …
ደህና ሁኑ ልጆች!
ደህና ሁኑ ልጆች!
ነፍስ ይማር

Tiss Abay Genji

 

 

Keta Magna added 2 new photos.
3 hrs ·

የባለቅኔ ሞቱ ህይወቱ! ” ካህሊል ጂብራን
—–
በእርግጥም ህይወት የረሳውን ሁሉ ሞት የሚያነግስበት
አጋጣሚ እዚህ በኛ ቀዬ የተለመደ ሆኗል።
እኔሆ በህይወት አጋጣሚ መቆየታቸው ግርማው ያልታየን አባባ
ተስፋዬ ሳህሉን ዛሬ አጣን ። በውኪፒዲያ ላይ ከቀረበው
የህይወት ታሪካቸው ላይ ቀጣዩን አግኝተናል።
ተስፋዬ ሳህሉ (1924 እ.ኤ.አ. ተወልደው) በኢትዮጵያ
ቴሌቪዥን ላይ ስመጥርና የተወደዱ ተዋናይና በተለይም
የሕፃናትና የልጆች ተረተኛ ናቸው። ፕሮግራማቸው የልጆች ግዜ
ከ1965 እ.ኤ.አ. ጀመሮ ታይቷል። ከዚያ ጀምሮ አባባ ተስፋዬ
ተብለው አዲስ ስማቸውን ተቀበሉ። በ1998 ዓ.ም. ከ42
አመታት አገልግሎት በኋላ ከሥራቸው ተለቀቁ።
ውልደት እና አስተዳደግ
ተስፋዬ የተወለዱት ሰኔ ፳፣ ፲፱፻፲፮ ዓ.ም በቀድሞ ባሌ ክፍለ
ሃገር ከዶ የተሰኘ አካባቢ ነበር። በ፲፬ አመታቸው ወደ አዲስ
አበባ በመምጣት ትምህርታቸውን በኮከበ ፅባህ ትምህርት ቤት
መከታተል ጀመሩ።
ቲያትር እና ቴሌቭዥን ስራ
የአዲስ አበባ መስተዳደር ባህል እና ቲያትር አዳራሽ ማስታወቂያ
ካወጣ በኋላ በተዋናይነት ማገልገል የጀመሩት አቶ ተስፋዬ
በወቅቱ የሴት ተዋንያኖች ባለመኖራቸው የሴቶችንም ገጸባህሪ
ወክለው ይጫወቱ ነበር። ‘ሀ ሁ በስድስት ወር’ ፣ ‘ኤዲፐስ
ንጉስ’፣ ‘አሉላ አባነጋ’፣ ‘ዳዊትና ኦርዮን’፣ ‘ኦቴሎ’፣ ‘አስቀያሚዋ
ልጃገረድ’ና ‘ስነ ስቅለት’ ተስፋዬ ሳህሉ ከተጫወቷቸው
ተውኔቶች ዉስጥ የሚጠቀሱ ሲሆን ‘ብጥልህሳ’፣’ ነው ለካ’ ፣
‘ጠላ ሻጯ’ በድርሰት ያበረከቷቸው ተውኔቶች ሲሆኑ አራት
የተረት መጻሕፍት ለልጆች አድርሰዋል።
በ፲፱፻፶፯ ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲቋቋም የልጆች ግዜ
የተሰኝ ፕሮግራም እንዲኖር ሃሳቡን አቅርቦ በማፀደቅ
የራሳቸውን የአቀራረብ መንገድና የፈጠራ ችሎታ በመጠቀም
ለመላው የኢትዮጲያ ህዝብ ያስተዋወቃቸውን ዝግጅታቸውን
ለ፵፪ ዓመታት በአባትነት ስሜት አቅርበዋል። ለልጆች የሚሆኑ
የተዋዙ ተረቶችን፣ ጨዋታዎችን እና አስተማሪ ዝግጅቶችን
የሚያቀርቡት አባባ ተስፋዬ ያበረከቱት መተኪያ የሌለው
አስተዋጾ ብዙዎች ያነሱታል።
ታዋቂ አባባላቸው
አባባ ተስፋዬ በኢትዮጲያ ቴሌቪዢን የልጆች ግዜ ፕሮግራም ላይ
የሚያቀርቡትን ተረት ሲጀምሩ የሚናገሩአት ታዋቂ ንግግር
“ደህና ናችሁ ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች እንደምን
አላችሁ ልጆች። አያችሁ ልጆች የኢትዮጲያ ቴሌቭዥን የልጆች
ግዜ ዝግጅት ክፍል እናንተን ለማስደሰት ልክ በሰአቱ ይገኛል።
እናንተስ ዝግጁ ናችሁ? አዎዎ አባባ ተስፋዬ ሸንተረሩን
አቋርጠው ዳገቱን ወጥተው ቁልቁለቱን ወርደው በጓሮ በኩል
ከተፍ ሲሉ እናንተ ደሞ ቆማችኋል አይደል? አዎዎ በቃ አሁን
ተቀመጡ እንዳትጋፉ ታዲያ ትንንሾች ወደፊት ትልልቆች ወደኋላ
አዎዎ።”
———
ፈጣሪ የአባታችን ነብስ በገነት አጸደ ያኑር !!