ጣና ማለት እንዲያው በደፈናው የዚህች ሀገርና የቤተክርስቲያን የምሥጢር ኪስ ወይም ግምጃ ቤት ነው ብየ ብለው በቀላሉ የሚገልጸው ይመስለኛል፡፡ ጣናን ከምናውቅለት ሀብቱና ምንነቱ የማናውቀው ይበልጣል፡፡ ሁሉም ነገር በጊዜው የሚገለጥ በመሆኑ የማይታወቀውን የጣናን ምንነትና ፋይዳ ጣና ማለት እንዲህ ነው፣ ጣና እንዲያ ነው!” እያልኩ ከመለፍለፍ እቆጠባለሁ፡፡

ከዐሥር ዓመታት በፊት ነው የትግራይ ባለሥልጣናት ጣናን ሊጎበኙ መጡና በሚጎበኙበት ሰዓት በጣና እጅግ በመጎምጀት ካለባቸው የቀማኛነት የውንብድና የዘራፊነት ሰብእናቸው የተነሣ ጣና ሊንቀሳቀስ የማይችል የተፈጥሮ ሀብት መሆኑን እረስተው አሰፍስፈው እየተንጫጩ ዋይእያሉ በትግርኛ መውሰድ አይቻልም ወይ?” ብለው እርስ በእርሳቸው መጠያየቃቸውን ሰምተን ሲበዛ ተገርመን እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡

ወያኔ ለዚህች ሀገርና ሕዝቧ በተለይም ለአማራ ሕዝብ ያለውን የጥፋት ዓላማ በሚገባ እያወቅን እስከዛሬ ድረስ ነገሮችን የምናይበት መነጽር የዋህነት የተሞላና ዘልማዳዊ ሆኖ ለሚፈጠሩ ችግሮች ሌሎች ነገሮችን በመጥቀስ እውነታውን የምንሸሽበት አባዜና አኪያሔድ በእጅጉ ያበሳጨኛል፡፡ ይህ ችግራችን ለገዛ አሳሳቢ ችግሮቻችን መፍትሔ ለመስጠት ያለብንን ዳተኝነትና ግዴታን ለመወጣት ያለብንን የፍላጎት ማጣት ያሳያል፡፡ ነገሩ ትንሽ ግራ አጋቢና በመረባረብ የሚጠይቀውን ዋጋ ከፍሎ ራስን ማዳን መታደግ ሲቻል ወዶና ፈቅዶ ራስን ለአውሬ በመስጠት ለመበላት የመፍቀድን ያህል ጅልነት የሚስተዋልበት ትንግርት ነው፡፡

ወገን ሆይ! ጣና ጭንቅ ላይ ነው፡፡ ጣና ጭንቅ ላይ ነው ማለት በአስቸኳይ ጊዜ ደረጃ ጎንደርና ጎጃምን እንደአጠቃላይ ደግሞ ኢትዮጵያን ለከፍተኛ ችግር መዳረጉ ነው ማለት ነው፡፡ ጣና በጎንደር እና በጎጃም መሀል ይኑር እንጅ የጣና አንዳች ነገር መሆን ጉዳቱ 90 በመቶ ክፍሉን የያዘው ጎንደርና 10 በመቶ ክፍሉን የያዘው ጎጃም ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያንም አልፎ ግብጽና ሱዳንንም ነው የሚጎዳው፡፡ ጣና እዚህ ቦታ ላይ ባይኖር ኖሮ ጎንደርና ጎጃም አልፎም ሌላው አካባቢ የሰሐራ በረሐ አካል በሆነ ነበር፡፡ አሁን እንኳ ጣና እያለ ራሱ በጋ ላይ የአካባቢው አየር በረሐ ነው፡፡ የአካባቢውን አየር ቀዝቀዝ የሚያደርገውና የሚያመጣጥነው ጣና ነው፡፡ አካባቢው ላይ ያለውን የበጋውን ልብስ የማያስለብስ ከፍተኛ ሙቀትና ወበቅ ልብ በሉና ጣና ባይኖር ኖሮስ!” ብላቹህ አስቡት፡፡ የሰው ልጅ በአካባቢው መኖር የሚችል ይመስላቹሀል? አጠቃላይ የአየር ንብረቱና ሥነምኅዳሩ (It’s ecology) ግልብጥብጡ ይወጣል፡፡ የነበረው እንዳልነበረ ሆኖ ያልነበረው ይኖራል፡፡

ከስድስት ዓመታት በፊት ወያኔ የአከባቢው ሰው እንቧጭ ሲል የሚጠራውንና ምንጩ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ ሆኖ በሳይንሳዊ (መጣቃዊ) ስም አጠራሩ Eichhornia crassipes ወይም Water Hyacinth በመባል የሚታወቀውን የውኃ አረም አምጥቶ ረጭቷል፡፡ ይህ እጅግ አደገኛ አረም መከሰቱ ከታወቀ ጊዜ ጀምሮ አረሙን የማጥፋት ወይም የመቆጣጠር እርምጃ እንዲወሰድ ለሚነሡ የሕዝብና የምሁራን ጩኸት ተገቢውን ምላሽ ነፍጎ አረሙ አሁን ከደረሰበት አሳሳቢ ደረጃ እንዲደርስ ያደረገውም ለዚህ ነው፡፡

ወያኔ ለምንድነው ይሄንን ያደረገው? ከተባለ መጀመሪያ ላይ አረሙን አምጥቶ ሲረጭ ደንቆሮውና አረመኔው ወያኔ አስቦ የነበረው ከገበሬው ተነጥቆ ለባለሀብት የተቸበቸበውን መሬት አላሳርስ ከማለት አልፎ አንዱን ባለሀብት እስከመግደል ድረስ የደረሰውና ባለሀብቶቹን ተነጥቆ ከተሸጠላቸው መሬት አላስደርስ ያለው በጣና ዳርቻ ዙሪያውን ያለውን ገበሬ በዚህ አስከፊና አደገኛ አረም አማሮ በማስለቀቅ መሬቱን ለባለሀብት ለመቸብቸብና በባለሀብት ስም ለራሱ ወገኖች ለመለገስ በማሰብ ነበር፡፡ ገበሬው ግን ይሄንን የከብትና የአጠቃላይ ሥነ ምኅዳሩ ፀር የሆነውን አደገኛ አረም በተቻለው አቅም ክረምት በውኃው የሚያዘውን በጋ ግን ውኃው ሲሸሽ እያረሰ የሚጠቀምበትን ባሕረሸሽ መሬት አረሙን እየነቀለ ለመከላከል ጥረት በማድረግ እያረሰ ለመጠቀም ከፍተኛ ጥረት አደረገ እንጅ እስከአሁን ወያኔ እንዳሰበው ተማሮ ሌላ ቦታ ምትክ መሬት ጠይቆ ሊለቅለት አልቻለም፡፡ ዘንድሮ ግን አረሙ ካለው በአጭር ጊዜ ውስጥ የመስፋፋትና ሰፊ ሽፋን የመያዝ ባሕርይው የተነሣ ገበሬው በተቻለው አቅም እየተከላከለውም አጠቃላይ የጣናን ዙሪያ ወሮ ይዞት በሰው አቅም መከላከል ከማይቻልበት ደረጃ በመድረሱና ከዚህ በኋላም ገበሬው ከብቶቹ እየተመረዙበት፣ እርሻውን ትቶ አብላጫ የግብርና ሥራ ሰዓቱን ይሄንን አረም ለማስወገድ በማጥፋት መቀጠል ስለማይችል ወያኔ የልቡ ሊደርስለት እንደሚችል እያሰበ ይገኛል፡፡

ምሁራን በአሁኑ ሰዓት የእንቧጭ አረም ከገበሬው አቅም በላይ እንደሆነና ጊዜው ሳይረፍድ አገዛዙ በሙሉ አቅም ተንቀሳቅሶ አደገኛውን አረም እንዲቆጣጠር አጥብቀው ቢያሳስቡም ሰሚ አላገኙም፡፡ አቅም ያላቸው ዜጎች የተቻላቸውን ለማበርከት ሲሞክሩም ያለ እኛ እውቅናና ይሁንታ ማንም ምንም ማድረግ አይችልም!” የሚል ትዕዛዝ ወያኔ በማስተላለፉ መንቀሳቀስ አልተቻለም፡፡ አያይዠ ያቀረብኩት ፎቶ (ምስለ አካል) አንድ የባሕር ዳር ነዋሪና የኢንጅኒየሪንግ (የምሕንድስና) ባለሞያ በግል ተነሳሽነትና ወጪ እንቧጭ አረምን እየነቀለ የሚያስወግድ ማሽን (ማሳልጥ) እራሱ ዲዛይን አድርጎ (ተልሞ) በመሥራት ከሀገር ውጨ ምንም ዓይነት ማሽን (ማሳልጥ) መጠበቅና ጊዜ መግደል ሳያስፈልግ ቀናነቱ ካለ በራስ አቅም ተንቀሳቅሶም እንዲህ ዓይነት መሣሪያዎችን በመጠቀም አረሙን መቆጣጠር እንደሚቻል ያሳየበት ሥራ ነው፡፡

ወያኔ ኢትዮጵያን ሲወር ከየአካባቢው እየነቀለ ወደ ትግራይ እያጋዘ እንደወሰደው ማሽን እና ማሽነሪ (ማሳልጥ እና ገነ ማሳልጥ) ጣናንም ወደ ትግራይ መውሰድ ባለመቻሉ ተስፋ ቆርጦ አልተቀመጠም፡፡ ጣናን ወደ ትግራይ መውሰድ ባይችልም ባለሀብት ወይም ኢንቨስተር (መዋዕለ ንዋይ አፍሳሽ) የሚል የሽፋን ስም በመስጠት ትግሬን ወደ ጣና በማምጣት የልቡን ለማድረስ እንደሚችል አውቆ ሸፍጥ የተሞላበት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ይሁንና ወያኔ መሰለው እንጅ ተነቃቅተናልና የፈለገ ተአምር ቢመጣ እዚያው ያልቃታል እንጅ ገበሬው መሬቱን ለቆ ይሔዳል ማለት ዘበት መሆኑን ወያኔ ቢረዳ መልካም ነው፡፡

እንዳልኳቹህ ወያኔ ይሄንን አደገኛ አረም አምጥቶ ሲረጭ ዓለማው ገበሬውን አማሮ ለማፈናቀያ ነበረ፡፡ ይሄ ቢሳካለት ገበሬው ከለቀቀ በኋላ በዘመናዊ መንገድ አረሙን ተቆጣጥሮ ብሎም አስወግዶ ያንን ለምና ለእርሻ ምቹ መሬት ለመጠቀም ነበረ፡፡ ይሄ ካልተሳካለት ደግሞ ምንም ዓይነት አረሙን የመከላከልና የመቆጣጠር እርምጃ ባለመውሰድ የጣና ህልውና እንዲያከትም በማድረግ የአማራን ሕዝብ ጥቅም ማሳጣትና ህልውናውን አደጋ ላይ መጣልን በማሰብ ነው፡፡

ጣናን በተመለከተ ከልጅነቴ ጀምሮ አንድ እየሰማሁት ያደኩት ነገር አለ፡፡ ጣና ይደርቅና ዳጋ በእግር ይገባበታል!” የሚል ንግርት ወይም ትንቢት ነው፡፡ ትንቢቱ ወይም ንግርቱ እውነት ይሁን አይሁን አላውቅም፡፡ ነገር ግን ትንቢቱ በአባቶች በገዳማውያኑ የሚነገር በመሆኑ ዝም ተብሎ የሚወራ ወሬ እንዳልሆነ መገመት ይቻላል፡፡ የዚህ ትንቢት የመፈጸም ያለመፈጸም ጉዳይ የሚወሰነው ግን በእኛው ስንፍና ወይም ብርታት ነው ብየ አምናለሁ፡፡ ከበረታንና በመንፈሳዊውም በሥጋዊውም ማድረግ የሚጠበቅብንን ሁሉ ካደረግን በነነዌ ሰዎችና በሕዝቅያስ ላይ የተነገረውን የጥፋት ትንቢት ትቶ ሊደርስባቸው ከነበረው መከራና እልቂት የታደገ አምላክ በእኛም ላይ የተናገረውን የትንቢት ቃል ትቶ ይታደገን ዘንድ የታመነ ነው፡፡ ከሰነፍንና በመንፈሳዊውም በሥጋዊውም ማድረግ የሚጠበቅብንን ትግል ጥረትና ንስሐ ሳንፈጽም እጅ እግራችንን አጣምረን የሚሆነውን ሁሉ በዝምታ የምንመለከት ከሆነ ከእግዚአብሔር የተነገረው ትንቢት ይደርስና ጣና ይደርቃል ሕዝቡም ይጠፋል፡፡ ምርጫው በእጃችን ነው፡፡ ወገን ሆይ! ሳይረፍድብህ ንቃ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com