አቶ ዛይድ ወልደገብርኤል

(ዘ-ሐበሻ) መንግስት የሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች እንደዘገቡት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንን ለረጅም ዓመታት በዋና ዳይሬክተርነት የመሩት አቶ ዛይድ ወልደገብርኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዘብጥያ ወረዱ::

አቶ ዛይድ ወልደገብርኤል የዘር ሃረጋቸው ሲፈተሽ ሙሉ በሙሉ ኤርትራዊ ደም እንዳለባቸው ይነገራል::

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩትና ካለፈው ሐምሌ ወር አንስቶ የመሰረተ ልማት ማስተባበሪያ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን እየሰሩ የነበሩት አቶ በቀለ ንጉሴ ባለፈው ሳምንት መታሰራቸውን የገለጹት የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዛሬ በአስቸኳይ ጥሪ የተሰባሰበው ፓርላማ ያለመከሰስ መብታቸውን ያነሳው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዓለማየሁ ጉጆም መታሰራቸውን ዘግበዋል::

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት ባለስልጣናት; ነጋዴዎችና ደላሎች ቁጥር 51 የደረሰ ሲሆን በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ኪሮስ ደስታ ዘብጥያ መውረዳቸው ተዘግቧል::

አቶ ዓለማየሁ ጉጆ

ይህ የጸረሙስና እንቅስቃሴ እስካሁን በሙስና እንደተጨማለቁ የሚነገርላቸውን አባይ ጸሐዬ ; ወ/ሮ አዜብ መስፍንን እና ስብሃት ነጋን አልነካም:: የሕወሓት የደህንነት ሹም ወ/ሮ አዜብን እና ስብሃት ነጋን ያጋለጡበትን ቭድዮ (Video) ለማየት እዚህ ይጫኑ::