August 4, 2017 16:16

ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት በነበረችበት ጊዜ በቀይ ባህር ላይ ያላትን ቁጥጥር  አለም አቀፍ ተቀባይነት የጎላ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካል አቀማመጦ ምክንያት እና ምስጋና ለነገሰስታቶቾ ታሪካዊ የባህር በር ባለቤት  አድርገዎት ቢያልፉም ይኸ ትውለድ ግን ማስቀጠል አልቻለም፡፡

ዛሬ የአትዮጵያ ህዝብ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሲሆን ይህም በዓለም ብቸኛ በህዝብ ቁጥር አንደኛ ሁና የባህር በር የሌላት አገር ያደርጋታል፡፡ በአፍሪካ ኢትጵያን ጨምሮ 15 አገሮች የባህር በር የሌላቸው ሲሆን ነገር ግን 14ቱ የአፍሪካ አገሮች የህዝብ ብዛታቸው ከ20 ሚሊዮን በታች ነው፡፡

ይህን ማስታዎሻ እንድፅፍ ያስገደደኝ በቅርቡ ከአሰብ ወደብ ተነሳ በተባለ ንብረትነቱ በየመን ሁቱ ሚሊሻዎች ላይ ዘመቻ የከፈተው ጥምር ጦር የሆነ መርከብ  በሁቱ ሚሊሻዎች አደጋ ተጣለበት የሚለው ዜና ነው፡፡

የቀይ ባህር አካባቢ የቄሳርን ለቄሳር እንዲሉ ታሪካዊት እና ቀደመት የሆነችው ኢትዮጵያ በበላይነት መምራት ሲገባትና ለዓለም አገራት ምሳሌነቶን ማሳየት ሲገባት ዛሬ ከእጃችን አፈትልኮ የወጣበት ምክንት ታሪካዊ ውርደት መሆኑን መጠቆም እወዳለሁ፡፡

ኤርትራ ሲያሻት ለኢራን (ሺአ ተከታይ)፤ ሲያሻት ለሳዉድ አረቢያ (ሱኒ ተከታይ) እያከራየች እርጥባን ብታገኝበትም ተጨማሪ ግን አካባቢዉን የስጋት ቀጠና ሁኖል፡፡  የእኛ ደካማ መሪዎችም  ግን ኤርትራ ብትፈልግ ግመሎን ውሃ ታጠጣዉ ብለው ቢያጣጥሉትም ለኢትዮጵያዊያን ግን አጥጋቢ መልስ አይደልም፡፡

ግመሎ እያለችው ከቀየው ከቀይ ባህር አፋር(አፈር)፤ላሟን ካልጫንኩ አለ ተሻግሮ በብድር፡፡

ላሙ (ኬንያ)፤ በርበራ(ሰማሊያ)፤ሱዳን ፖርት (ሱዳን) አሉን እያሉ ከማላዘን ግመሎ ያለችበትን ቀይ ባህር ጠበቅ ማድረግ አማራጭ የለውም፡፡ቀይ ባህር ተፈጥሮዊ የአፋር (አፈር) ህዝብ ሀብት እንደሆነ ይኸም በአለም አቀፍ ህግ ተቀባየይነት እንዳለው(Law of intimacy) የምዳስስበት ፅሑፍ ይኖራል፡፡ ሱልጣን አሊ ሚራህ ሰለአፋር ኢትዮጵያዊነት ሲያስረግጡ ግመሉ ሳትቀር የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ትለያለች ነበር ያሉት፡፡ የአፍርን ህዝብ ለሁለት የከፈሉት የእኛ መሪዎች (ጎረምሷች እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አገላለፅ) በሰንደቅ ዓላማችን እንደቀለዱ ወደ ግብዓተ መሬት ወረዱ፡፡ ስለ ቀይ ባህር የእኛነት ዳጉ ካደረግሁ በኃላ እመጣለሁ፡፡

አንድ ቀን ግን ኢትዮጵያ ዳግማ በቀይ ባህር አካባቢ ታንሰራራለች፡፡ ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!