August 4, 2017 06:33

መገንጠል ኣጀንዳችን ኣይደለም። ይሄ መንግስት የምንቃወምበት አንዱ መሰረታዊ ጉዳይ እኛ/ዓረና መገንጠል አንደግፍም። የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ያለ መገንጠል ግን እንደግፋለን። ይሄንን ምንለው በእኩልነት ላይ የቆመ አንድነት የጭቆና ምንጭ ሳይሆን የሀያልነት ሁነኛ መሳርያ ስለሆነ ነው። መገንጠልን የምንቃወመው ስትገነጠል ከነችግሮችህ ነው የምትገነጠለው/ ችግርችህም ኣብረ ይዘሃቸው ነው የምትገነጠለው። ስለተገነጠልክ ብቻ ችግሮችህ እንደ ጉም ብን ብለው ይጠፋሉ ማለት አይደለም።

አፍሪካ እንደ አውሮፓ ህብረት ወደ አንድነትና ህብረት እናምጣት እየተባለ ዘለው ያልጠገቡ አንዳንድ ወጠጤዎች ደግሞ “ሃገረ አግኣዝያን” እያሉ የአፍሪካ ቀንድ በሙሉ ወደ ትርምስ ቀጠና የሚያስገባ አጀንዳ ያራግባሉ። መገንጠል አዋጭ ቢሆን ኖሮ ለ ኤርትራና ለ ደቡብ ሱዳን ይጠቅም ነበር። ይሄው ዓለም ወደ ፊት ሲገሰግስ ሁለቱም ሃገራት ግን እንደግመል ሽንት ወደ ኋላ እየነጎዱ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አምባገነን ስርዓት በጋራ በመታገል እውነተኛ ነፃነት ተቀዳጅቶ በፍቅርና በአንድነት መኖር እንጂ ሃገረ አግኣዝያን፣ ቤተ አማራና ኦሮምያ ትቅደም! እያለ ወደ ድንጋይ ዘመን መመለስ አይፈልግም። ዓረና በኢትዮጵያ አንድነት መቼም አይደራደርም። ፀረ አንድነትና ትገንጣይ ሃይሎች 100, 000, 000 የኢትዮጵያ ህዝብ አሰልፈን ዛሬም እንደ ትላንቱ እንታገላቸዋለን።

ዓረና ምንግዜም ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ዘብ ይቆማል።

ኢትዮጵያ አንድነትዋ ተጠብቆ ለዘለዓለም ትኖራለች!!!