ብሄረ አግአዚያን የሚል የTPLF think-thank ቡድን የሚያራምደው ከኤርትሪያዊያን ጋር ሊፈጥረው ስለሚፈልገው የወንድማማችነትና ጓዳዊ ትስስር መመርመር ፤ በአንክሮ መከታተልና ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይገባል ባይ ነኝ፡፡

ከሚቀጥሉት ጹሁፎች በመነሳት ነብስ ዘርቶና ስጋ ለብሶ መንቀሳቀስ የጀመረ እርኩስ መንፈስ የተላበሰ ሌሎችን ለመዋጥ ተዘጋጀ ማህበር ነው፡፡ ይህ ለመሆኑ ማሳያዎቼን ማቅረብ ይኖርብኛል፡፡ የሚቀጥለው አርፈተ ነገር ከተስፋይ ኪሮስ (ተስፋኪሮስ አረፈ አይደለም) የተወሰደ ነው፡፡

“የአግአዚያን እንቅስቃሴ ወደድንም ጠላንም እንቅስቃሴው በአውሮፓ፣ በአሜሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ሀገራት ጽ/ቤቶችን በመክፈት የአባላቱን ቁጥር በሚገርም ፍጥነት እያበዛ ያለ ማሕበር ነው፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የሚኒሊክ የአሻጥር ፖለቲካ የተለያየ ህዝብ አንድ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡” Even if this information is true, the plan will be hard or impossible for its realization on the ground. Null result! Just my opinion”

በታሪክ ከደቡብ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ፈልሰው ገቡ የሚባሉ አጋአዚያን ፤ ሀድራማዊት የሚባሉ ጎሳዎች እንደነበሩና ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበረው የአገው ማህበረሰብ ጋር ተዋህደው መጥፋታቸውን ታሪክ ይመሰክራል፡፡ በዚህ ሰአት ብሄረ አግአዝያን የሚባሉ ስደተኛ ቅሪቶች መኖራቸውን አላውቅም፡፡

ትግራይ ራሱ ኢሮፕን/ሳሆን ፤ ኩናማን እና አገውን በማቀፍ አይደለም ወይ እየተመሰረትኩኝ ነው እያለን ያለው??? እና እነዚህ አካላት በምን መስፈርት አጋአዚያን ሆነው ነው ለተፈጻሚነቱ አብረው ሰርተው የተባለውን ሃሳብ እውን ሊየያደርጉ የሚችሉት???? ብሎ ማሰብ ይቻል ይሆናል፡፡ ምእራብ ትግራይ የሚባለው የኩናማ ተጽእኖ የበዛበት ፤ በታሪክ በአገውነት የሚታወቀው ተምቤንና ከተምቤን ወደ ደቡብ አቅጣጫ ያለው ሰሃርቲ ሳምረ ፤ ቦራ ስላዋ ፤ አበርገሌ እና ከአገው ጋር ከፍተኛ ቅርኝት አለው የሚባለው እንደርታ በምን መስፈርት አጋአዚያን ይሆናሉ???? ማለትም ይቻላል፡፡ ሌሎች ታሪካዊ ይሁን ማህበረ-ባህላዊ ቁም ነገሮችን ያዘሉ መሰል ጥያቄዎችን መጠየቅ ይቻላል፡፡

ነገር ግን መነሻ ታሪካዊ መሰረት ይኑረው አይኑረው ፤ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ድጋፍ ያገኛል አያገኝም ፤ የሚገመተው የፖለቲካ አላማውስ አሁን ካለው ነባራዊና ተጨባጭ የኢትዮጵያና የኤርትራ ሁኔታ ጋር ሊመስልና ሊሳካ የሚችል አካሄድ ነውን???? ሌላ ጥያቄ ነው፡፡ ተቋቁሞ ግን “በምንልክ አሻጥር ተለያየ” የሚሉትን የኤርትራና የትግራይን ትግሬዎች በቅርቡ ለማገናኘት በሚል በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑ የማይታበል ሀቅ ይመስላል፡፡ የኤርትራና ትግራይ አግአዚያን እንቅስቃሴ ለቀሪዎቻችን ሊኖረው የሚችለውን ትርጉም ምንድን ነው የሚለውን እንድናስብ ለማስገንዘብ ነው፡፡

ብሄረ አግአዚያን የሚባሉትን ሳስብ አእምሮየ ውስጥ የሚመጡብኝ ሁለቱ TPLF እና EPLF ወይም ሻእብያን የመሰሉ ድርጅቶችና ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድሃኔ የተባሉ የኤርትራ ሙሁር ናቸው፡፡ በግምት ከሶስት አመት በፊት አካባቢ ይመስለኛል በጻፉት አርቲክል በኤርትራም በትግራይም ያሉት ሁለቱ የገዥ መደቡ አባላት ለተመሳሳይ አለማ እየሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡ ኢትዮጵያን የሚመሩት አካላት በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን በኩል የኤርትራ ትውልድ እንዳለቸው የሚወራውን ያክል በኤርትራ በኩልም ያሉት መሪዎች የትግራይ ትውልድ ያላቸው የተጠራቀሙበት ተደርጎ እንደሚወሰድ ይገልጻሉ፡፡ ይህ ፕረዚደንቱንም ይጨምራል፡፡

እንደሳቸው አባባል የኤርትራ ማህበረሰብ ተራማጅ ፤ ለውጥ የሚቀበልና ስልጡን ማህበረሰብ ተደርጎ ይቆጠር እንደነበር በተቃራኒዉ የትግራይ ማህበረሰብ ደግሞ ወግ አጥባቂና ለወግና ልማድ ተገዥ እንዲሁም ለለውጥ የማይመች ተደርጎ ይቆጠር እንደነበር ያብራሩና ይህ አመለካከትና ተጨባጭ ነበር ብለው የሚያምኑት ነባራዊ የነበረው ሁኔታ እንዲሁም ይህ አመለካከት የወለደው በኤርትራና በትግራይ መካከል የነበረውን የተዛነፈ የስነ-ልቦና ልዩነት ፤ አመለካከትና አንዱ ለአንዱ የነበረውን የተዛባ አመለካከት ለመቀየር በየፊናቸው እየሰሩ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ የኤርትራ መንግስት የኤርትራን ማህበረሰብ በብዙ መልኩ ቀይዶ በመያዝና ማህበረ-ባህላዊ እድገቱን በመግታት ዝቅ አድርጎ ያየው የነበረውን የትግራይን ማህበረሰብ በሚያደርገው ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴና እድገት የተለየ አድናቆትና ክብር እንዲያሳድር ለማድረግ ተግቶ እየሰራ ነው ይላሉ፡፡ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ የሀገሪቱን ሃብት በብልጫ በመውሰድ ክልሉን በማልማት የትግራይን የሞራልና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማሳደግ ከኤርትራዊያኖቹ ጋር ተቀራራቢ ስነ-ልቦና እንዲፈጥር በማድረግ ሁለቱን ማህበረሰቦች የማቀራረብ ስራ መስራት ነው፡፡ አባባሉ አንደገባኝ አንዱ ዝቅ እንዲል አንዱ ደግሞ ከፍ እንዲል ተደርጎ በተመጣጠነ ስነልቦና ለአዲስ የትግራይ ትግሪኝት አገር ምስረታ ዝግጁ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

ገበጣ በሚባለው የባህል ጨዋታ በራያ ጭንቋሌ የሚባል የጨዋታው ህግ አለ፡፡ ጨንቋሌ ማለት አንድ ሰው ጨዋታውን ለማስኬድ ጁሙን ወይም ጉድጓድ ውስጥ ያለውን ድንጋይ ሲያነሳ ከሚያነሳበት በፊት ካለው ጉድጓድ አንድ ጠጠር ካለ ጭኗቋሌ ይላል፡፡ ይህ ማለት ይች ከኋላ ጉድጓድ ያለችው ጠጠር ብታስፈልገኝ ወይም ብተጠቅመኝ ትከተለኝ ባትጠቅመኝ ትቅር ማለት ነው፡፡ እናም ጭንቋሌ ብወዳት ትከተለኝ ብጠላት ትቅርብኝ ብሎ ይነሳል፡፡ ይዞር ይዞርና ጠቃሚ ሆና ከተገኘት አንስቶ ይበላባታል/ያሸንፍባታል ካልጠቀመች ይተዋታል፡፡

የአግአዚያንም ፖለቲካ የጭንቋሌ ፖለቲካ ነው፡፡ መጀመርያ ከኤርትራዊያን በላይ አርትራዊያን ሆነው፤ የኤርትራ ጉዳይ ብለው ጽፈው ራሳቸውንና ሌላውን የሚያደነግር የቅኝ ግዛት ታሪክ ፈጥረው ፤ ኤርትራዊያን ራሳቸው በሆነ የአስተዳደር ስርአት ኢትዮጵያ ጋር ለመኖር ፍላጎት ሲያሳዩ በኤርትራ ህዝብ ፍላጎት እየተደራደራችሁ ነው ብለው ከሰው ፤ አገር በጋራ ሲቆጣጠሩ አመለካከታቸውን እንዲያለዝቡ አድርገው በጋራ መኖር እንዳይችሉ አለማቀፋዊ ወግና ስርአቱ ባልጠበቀ ሁኔታ አጣድፈው እንዲወጡ አድርገው አገሪቱን በቁጥጥር ስራቸው እንዳሻቸው ሲያደርጉ ከኖሮ በኋላ ሌላው የፍትሃዊነት ፤ የእኩልነት ፤ የነጻነት ጥያቄ አንስቶ በነበረው የበለጠ ተጠቃሚነት ደረጃ መጠቀም እንደማይቻል መገንዘብ ሲጀምሩ ጭንቋሌ ማለት ጀመሩ ማለት ነው፡፡ ለአግዚያን ኢትዮጵያ የጭንቋሌ ድንጋይ ነች ማለት ነው፡፡ ጥቅም ስትሰጥ የምትገለገልባት ከሌሎች በበለጠ መጠቀም እንደማትችልባት ስትረዳ አንገተህን አስግገህ ፤ ወንዝ ተሸግረህ ፤ ታሪክ መዘህ አግዚያዊነት የምታማትርባት የጭንቋሌ ድንጋይ፡፡

ፐሮፌሰሩ ባሰቀመጡት መንገድ እና በሁለቱ ማህበረሰቦች በነበረው ታሪካዊም ይሁን ማህበረ-ፖለቲካዊ መሰረት የሌለው መናናቅ ምክኒያት አዲስ አባባ እንደገቡ አብረው ለመቀጠል እንኳነ ቢስማሙ ተሰማምተው ሊዘልቁ የሚችሉባቸው ፖለተካዊም ፤ ኢከኖሚያዊም ይሁን ስነልቦናዊም ነባራዊ ሁኔታዎች አይኖሩም ነበር፡፡ ያም እዛ ሆኖ በቡና ምርት ላኪነት በአለም ደረጃ ደረጃው እንደተጠበቀለት መቀጠል ሲያምረው ፤ በዚህ በኩል ደግሞ ቡናን ጨምሮ ጥቅሙ በነሱ ከተያዘ ለእኛ ምን ተረፈ በሚል ግብግብ ጨዋታ ፈረሰ ደቦ ተቆረሰ ብለው ወንድሞቻችንን ላልረባ ነገር አስጨረሱብን፡፡

አሁን ምን አዲስ ነገር ተገኘ ????????? የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው::

እሳቸው ይህ ዝግጅት ኤርትራ ውስጥ የትግርኛ ተናጋሪውን ቁጥር በመጨመር የፖለቲካ ሚዛኑን ወደ ትግሬዎቹ ስለሚያጋድለውና ነባር ግንኙነቱን ስለሚያዛባው እንዲሁም አሁን ያለው በኤርትራዊ ዜግነት ላይ የተመሰረተ ማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ አተያይ ስለሚበክለው አይደግፉትም፡፡ ተጨማሪና ሁለተኛው ተያያዥ ምክኒያታቸው TPLF ኢትዮጵያ ውስጥ ያሳደገውን የበለጠ ተጠቃሚነት ቀመሩንና አስተሰሰቡን ይዞብን ስለሚመጣ ኤርትራ ውስጥ በማህበረሰብ ደረጃ የሰፈነውን ፍትሃዊ አመለካከትና አሰራር (አንድ ጎሳ በሌላው ኪሳራ የሚከብርበት ፖለቲካዊ አስተሳሰብም አሰረርም ባለመኖሩ) ኤርትራ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ማህበረሰቦች ማህበረሰባዊ ችግር ያስከትላል ብለው በማመናቸው እንዲሁም በአካባቢው ሌሎች ማህበረሰቦች ፍላጎት ካላቸው ውጫዊ አካላት ጋርም መልካም ባህላዊም ይሁን ፖለቲካዊ ግንኝነት ስለማይፈጥር ኤርትራ የተረጋጋች አገር አትሆንም ከሚል ስሌት የመጣ ይመስላል፡፡

የፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድሃኔ ትንታኔ እሳቸው በገለጡት መንገድ ትክክል ይሆን??? የሚል ጥያቄ ሊጭር ይችል ይሆናል (በተለይም በኤርትራ በኩል ይሰራል የተባለው ) ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ውስጥ ተሁኖ ከኤርትራ ጋር ሊፈጠር የሚፈለገው ወንድማማችነት ግን የሚያመላክተው በቁም ነገር ተይዞ እንደ አንድ የፖለተቲካ አማራጭ ዝግጅት እየተደረገበት ያለ አብይ ጉዳይ ሆኖ ይሰማኛል፡

ይህ ደግሞ ለእኛ ለራዮች ፤ ለዋጎችና ለወልቃይቴዎች በተለየ መንገድ ለሌሎች ኢትዮጵያዊያን ባጠቃላይ ምን ማለት እንደሆነ ማሰብና ማሰላሰል ያስፈልጋል፡፡ እንደ “ብሄረ አግአዚያኑ” ነን ባዮች ድንበር ሳንሻገር የዋግ ፤ የራያና ወልቃይት ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነት አያስፈልግም ተትላላችሁ?????? ለትብብራችን መነሻ የሚሆን የውሸት ታሪክ ሺ አመታት ወደ ኋላ ተጉዘን መፈብረክም አያስፈልግም፡፡ህያው ነዋ!!!!

የራያ ሰው ሁሩበ በሚባለው ማታ ማታ በሚደረግ የጎረምሳ ወንዶች የባህል ስፖርት ጨዋታ ለሁለቱም ቡድኖች እንደ ጆከር የሚያከለግለውን ግለሰብ በራይኛ “ወርሕ ኮለል” ይለዋል ፡፡ እናም ዋጎች ከመልከአ ምድራዊ አቀማመጣቸው ይችን ድርሻ መጫወት ያለባቸው ይመስለኛል፡፡