August 10, 2017 13:34

ኢሳት – ልዩ ዜና

–ባህርዳር ውጥረቱ በርትቷል። ነጋዴዎች እየታሰሩ ነው። መንገዶች በፍተሻ በተሰማሩ የመንግስት ሃይሎች ተወሯል።

 

–የአሜሪካን ኤምባሲ ለዜጎቹ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላፏል። ከአዲስ አበባ ጂጂጋ በሚወስደው መንገድ በባቢሌባ ሀረር መሃል መንገድ በመዘጋቱ ወደአከባቢው ከሚደረግ እንቅስቃሴ ዜጎቹ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።

 

–በሀዋሳ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች አድማ ተደርጓል። በመንግስት ሃይሎችና በአድማው ተሳታፊዎች መሃል ግጭት ተፈጥሯል። የመንግስት ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል።

ከአዲስ አበባ ወደ ጅጅጋ የሚወስደዉ መንገድ በባቢሌና በሃረር መካከል መዘጋቱን የአሜሪካ ኢምባሲ አስታወቀ፡፡ በጦር መሳሪያ የተደገፈ ከፍተኛ የተኩስ ልዉዉጥ እየተካሄደ መሆኑን፣ መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢዉ መንቀሳቀሱን ኢምባሲዉ ገልጿል፡፡ የአሜሪካ ዜጎች በባቢሌና ሃረር መካከል ባሉ ቦታዎች እንዳይጓዙ ኢምባሲዉ አስጠንቅቋል

Ayalew Menber

የባህር ዳር ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል።ከሶስት ቀን በፊት ክልል ምክርቤት ስነይፐርና ቦንብ የታጠቁ ብዛት ያለቸው ሰራዊቶች በፎቶ ተመልክቸ ነበር።በቀጣዩ ቀን ለግድያ የተሰማሩ መሆናቸውን አወቅን።ይውኸባህር ዳርን እያመሷት ነው።

<<የባህርዳር የትናንትና የዛሬ ውሎ፡ ትናንት ማታ የገባው 5 FSR ወታደር በሙሉ አቅሙ አፈሳ ላይ ተሰማርቶ አምሽቷል፡፡ ፓትሮል መኪኖች ያለማቋረጥ በየሰፈሩ ወጣቱን ሲለቁ አምሽተዋል፡፡ የባጃጅና የታክሲ ሹፌሮች ሲታፈሱ አምሽተዋል፡፡ ቀበሌ 5 የተገኘ ባጃጅ ሁሉ ታርጋ ፍታ ታርጋው የኛ ነው እየተባሉ ሲታሰሩና ሲዋከቡ አምሽተዋል፡፡ ፓትሮሎች ያለምንም ማቋረጥ ባዷቸውን ወጥተው ሙሉ ወጣት ጭነው ሲመላለሱ አምሽተዋል፡፡

ቀበሌ 5 ድርጅቶችን የማሸግ ስራው ተጠናክሮ ውሏል፡፡ በዚህ የተናደደው ህ/ሰብም ሁሉም ጥርስ በመንከስ በትግሬ ወያኔ ላይ ለበቀል እንነሳለን እያሉ ነው፡፡ የደህንነቱ ብዛት የአንድን ቀበሌ ነዋሪ ያክላል፡፡ያልታደለ ህዝብ ደግሞ ዛሬም በህወሃት ግፊት ለሌላ አመፅ እየተዘጋጀ ነው።>>

ይህ ያያዝኩት ከቦታው አሁን የተላከ ነው።

Source