መሬት ተከራይተው የሚያርሱ አማራወች በህወሓት ወታደራዊ አዛዦች ታሰሩ !!

በቤንሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ውስጥ በአባይ ወንዝን ታኮ የሚገኝ ጫካ በአካባቢው በሚኖሩ በርታወች ለአመት ተከራይተው እያረሱ የሚኖሩ አማራወች ህገወጥ ናችሁ በማለት ለአመታት ሲያርሱበት የነበረውን እና በአዲስ የተከራዩትን መሬት ለቀው እንዲወጡ የህወሓት ወታደራዊ አዛዦች መሬት የሚያከራዩቸውን ቢልኩባቸው ገንዘብ ከፍለን ነው

ለአመታት እያረስነ ያለነው ስለዚህ ህገወጥ አይደለንም በማለት አንወጣም በማለታቸው 6 የአማራ ተወላጆች ና አንድ የበርታ ጉሙዝ ተወላጂ ወደ ዞኑ ግልገል በለስ ተልከው ታስረዋል። በ3ቱ ላይ ከፍተኛ ድብደባ የተፈፀመባቸው ሲሆን የአካል ጉዳትም ደርሶባቸው ያለህክምና እንደታሰሩ ታውቋል። በአይሲድ ከተማ ተገንጥሎ ወደ አባይ ድንበር በሚዘልቀው አዲስ መስመር ወደ 50 ኪ.ሜ የሚሸፍን ጥቅጥቅ ደን በህወሓት ሰወች እየተጨፈጨፈ እየታረሰ የሚገኝ ሲሆን በወንበራ አካባቢ እስከ ወለጋ አዋሳኝ የአባይ ወንዝ ድረስ ከፍተኛ የሆነ የሰሊጥ እና ጥጥ ምርት ተከራይተው በሚሰሩ አርሷደሮች ይመረታል።

ሌላው ወርቅ በባህላዊ መንገድ በአባይ ወንዝ እና ዙሪያ አካባቢው የሚመረት ሲሆን በዚህ አካባቢ የሚታፈሰው ምርት ያስጎመዣቸው የህወሓት ወታደራዊ አዛዦች ከዚህ ቀደም የሚያርሱትን በተለያየ ምክንያት በማስወጣት ለራሳቸው ጠቅልለው የያዙ ሲሆን ወርቅ የበባህላዊ መንገድ የሚያወጡትን ደግሞ እንዲሰደዱ እና ሲያወጣ የተገኘ በእስር እና በገንዘብ ቅጣት በማውጣት አስመርረዋቸዋል። የታሰሩት አንድ የበርታ ጉሙዝ እና 6 የአማራወች ብሄር ተወላጆች የተከሰሱበት ምንም ጥፋት የሌለባቸው ሲሆን ክስም እንዳልተመሰረተባቸው ታውቋል።

የህወሓት ወታደራዊ አዛዦች እና ህወሓት ያሰፈራቸው የስርዓቱ አገልጋይ ትግሬወች በማናለብኝነት የያዙትን ሰፊ የእርሻ መሬት በቀን የጉልበት ስራ ውል ይዘው ሲያሳርሱ ይቆዩና ምንም አይነት ክፍያ ሳይከፍሉ ደብድበውና አስረው ያለምን እርህራሄ እንደሚልኳቸው ከአካባቢው የሚወጡ የቀን የጉልበት ሰራተኞች ይናገራሉ። እነሱን መክሰስ ሆነ መጠየቅ እንደማይችሉ የሚናገሩት ተጎጂወች ዕድል ኑሮት ትንሽ ገንዘብ ይዞ የሚወጣ የታደለ ነው፤ በተለያየ ወቅት ተገለው የምናገኛቸው ልጆች በማን እንደተገደሉ ባናውቅም ብዙ ናቸው ሲፈልጉም በምግብ የቀጡናል ይላሉ።

በአካባቢው የሚገኙ የህወሓት ሰወች ዕድሜ ጠገብ ዛፎችን በመቁረጥ ሰፊ መሬቶችን በሞኖፓል ከመያዛቸው በተጨማሪ ደን በመመንጠር ፣ በመጨፍጨፍ ከፍተኛ የክሰል ምርት እያስመረቱ ወደ መሃል ሀገር እንደሚጭኑ ይታወቃል። በተያያዘ መረጃ ከአባይ ግድብ ጋር ተያይዞ በጉባ ወረዳ ከፍተኛ የደን ምንጣሮ በትግሬ ኢንቨስተሮች በሄክታር በጨረታ ተረክበው በምንጣሮው ደግሞ የአማራ ወጣቶች በጉልበት ስራ በማይረባ ክፍያ በበሽታና በረሃብ እየሰሩ ይገኛል።

@እንቅዩጳዝዩን የአርበኞቹ ልጂ