“ሾህን በሾህ” በሚል የተሳሳተ መሪህ የተቋቋመው የሱማሌ ልዩ ፓሊስ(ልዩ ወታደራዊ ኃይል) ኢትዮጵያን ከማፍረሱ በፊት መፍረስ አለበት!
***************************************************************************
Birhanemeskel Abebe Segni

ሶማሊያ ከእንግሊዝና ከጣሊየን ቅኝ ግዛት ነፃ ከወጣች ከ1960 ጀምሮ አብዛኞቹ የሱማሌ ፓለቲከኞች እስከ ዛሬ ድረስ የኢትዮጵያ ሱማልኛ ተናጋሪ አከባቢዎችን በመውረር ታላቋን ሶማሊያ የመመስረት ህልም ይዘው ነው የሚኖሩት።

የታላቋ ሶማሊያ ህልም የ British Somali land፣ የItalian Somali Land፣ የFrench Somali Land፣ የEthiopian Somali Land እና የKenyan Somali Land ን አንድ ላይ በማምጣት በለ አምስት ኮኮብ በንድራ ባለቤት የምትሆንን ታላቋን ሶማሊያ መገንባት ነው።

ህልሙ እንደ አየሩ ሁኔታ አንደንዴ በግልፅ ሌላ ጊዜ ደግሞ በስውር ይገፋል።

ለምሳሌ የሶማሊያ መንግስት ከተቋቋመ በጥቂት አመታት ውስጥ ከአዋሽ ማዶ ያሉትን የኢትዮጵያን ግአዛቶች በመውረር ታላቋን ሶማሊያ ለመመስረት የነበረውን ህልም እውን ለማድረግ በ1964 እና በ1977 በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት አውጃዋል።

ሶማሊያ ነፃነት እንዳገኘችም፣ የምዕራብ ሶማሊያ ነፃ አውጭ ግንባር ተብሎ የሚታወቀውም ድርጅት በ1960 የቋቋሙት ይህንኑ የታላቋን ሶማሊያ ህልም እውን ለማድረግ ነበር።

ከሞለ ጎደል አሁን ለፓለቲካ ስልት ሲሉ በአገር ቤትና በውጭ አገር በተለያዩ ስያሜዎች የሚጠሩ የተለያዩ ቡድኖች የሶማሌ ልዪ ፓሊስ የሚባለውን ድርጅት ጨምሮ የሚንቀሳቀሱት በዚሁ የታላቋ ሶማሊያ የፓላቲካ ቀመር ነው።

ለዚህ ነው የኦሮሞ ህዝብ በቦረና ከኬንያ ጋር እና የአማራ ህዝብ በጎንደር ከሱዳን ጋር በተደጋጋሚ ድንበርን አስመልክቶ የሚያደርገውን ግጭት የኢትዮጵያ ሱማሌዎች ከሱማሌ ሱማሌዎች ጋር በድንበር ላይ ሲጋጩ የማናያው።

ይህንንም ከንቱ የትልቋን ሶማሊያ ህልሙን ተግባራዊ ለማድረግ ሰይድ ባሬ በኢትዮጵያ ላይ ከ1977 እስከ 1978 ያዋጃው ጦርነትና የፈፀመው ወረራ ትልቁ ነው።

የሰይድ ባሬ ጦርነት ሃረርጌን፣ አርሲን፣ ባሌን እና ቦረናን(ሲዳሞን ጨምሮ) ከኢትዮጵያ ገንጥሎ የሶማሊያ አከል ማድረግ ነበር። ሰይድ ባሬ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ድንበር የአዋሽ ወንዝ ነው ብሎ ያምን ነበር። አዳማ/ናዚሬት/ የድንበር ከተማችን ልትሆን ማለት ነው።

ይህ ብቻ አይደለም። ይህ የትልቋ ሶማሊያ ህልም የዋቤና የገናሌ ወንዞች መነሻ የሆኑትን የአርሲ፣ የባሌና የሀረርጌ ተራሮችን በመቆጣጠር ለሶማሊያ በተለይም ለመቀደሾ የመጠጥና የመስኖ ውሃ አቅርቦትን አስተማማኝ ማድረግ ነው። ግብፀ የኣባይ ተፈሰስን ለመቆጠጠር የምታደርገው አይነት ህልም መሆኑ ነው።( እኛ መቶ ሚሊዮን የሚበልጠው የኢትዮጵያ ህዝብ የመሬትን 75 ከመቶ የሚሆነውን የሚሸፉነውን የውቂያኖስ ውሃና ሀብት ተጠቃሚ ለመሆን ለምን እንደማናልም አይገባኝም።)

በወቅቱ ጃግናው የኢትዮጵያ ህዝብና መከላከያ ሰራዊት (እንደ ኩባ በመሰሉ ወዳጅ አገሮች በመታገዝ) ወራሪውን የሱማሌ ኃይል ዳግማኛ እንዳይነሳ አደርጎ ድባቅ መታው። በኃይል ከያዘው የኢትዮጵያ መሬትም ገርፎ አባረረው።

አሁን በኦጋዴን የፈሰሰው የጀግኖች አባቶቻችን ደም ሰይደርቅ ደግመኛ ጥቃት በአገራችን ላይ በእጅ አዙር በባሬ ጀሌዎች መከፈቱ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ሊያስደነግጥ ይገባል።

ከጦርነቱ በኃላም የሰይድ ባሬ መንግስት ኢትዮጵያን በማዳከም የግዛት መሰፈፈት ህልሙን እውን ለማድረግ የተለያዩ ስልቶች ለመጠቀም ቢሞክርም በትጉ ኢትዮጵያዊያን ብርቱ ትግል የባሬ መንግስት ፈረሰ፣ እርሱም ተሰዶ በስደት ሞተ።

ሰይድ ባሬ ብሞትም ከኣዋሽ ማዶ ያሉትን የኢትዮጵያ ግዛቶችን ወሮ ትልቋን ሱማሌ የመመስረት ህልም ግን አሁንም አልሞተም፣ ጥስሱም አልተደፋም። Union of Islamic courts ይባል የነበረው ቡድን ኣለማ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

የሶማሌ ልዩ ፓሊስ የሚባለው ኃይል “ሾህን በሾህ” በሚል መሪህ በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሰውን የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባርን በሌላ የሱማሌ ቡድን ለመምታት የተቋቋመ ኃይል ነው። አሜሪካኖቹ በኢራቅ የSunni awakening ብለው ያቋቋሙትና በኃላ ISIS የወለደላቸው አይነት ትንግርት።

ለዚህ አላማም ይውል ዘንድ ለሶማሌ ልዩ ፓሊስ ወታደራዊ ስልጠና (በኢትዮጵያ ስም) የተሰጣቸው በኢንጊሊዞች ሲሆን ያስታጠቃቸው ደግሞ ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ነው።

ወታደራዊ ኃይሉ የታጠቀው መሳሪያ ደግሞ የተገዛው ከኢትዮጵያ ህዝብ (የኦሮሞ ህዝብን ጨምሮ) በተሰበሰበ የግብር ገንዘብና ኢትዮጵያ ቡናና ወርቃችንን በመሸጥ በምታገኘው የውጭ ምንዛሪ ነው።

ይህ ወታደራዊ ኃይል መጀመሪያ ላይ የታለመለትን አላማ ያሳካ ቢመስልም አሁን አላማውን ቀይሮ የሶማሊያን ግዛት በኃይል የሚያስፋፋና የታላቋ ሶማሊያ አጃንዳ በዋነኛ አስፈፃሚነት የተያያዘው ስለመሆኑ ያለፉት አመታት ተግባሩ በግልፅ ያሳያሉ።

ልክ ሰይድ ባሬ ኢትዮጵያ በ1974 አብዮትና አብዮቱን ተከትሎ በተከሰተው የነጭና የቀይ ሽብር መዳከሟን በመየት የግዛት ማስፋፋት ወረራውን እንደፈፀመ ሁሉ የሶማሊያ ልዮ ፓሊስም የ#OromoProtests እና የ#AmharaProtests ተከትሎ የኢትዮጵያዊያን ትኩረት ሌላ ቦታ እንደሆነ በመገመት ነው በሀረር፣ በአርሲ፣ በባሌና በቦረ የከፈተውን የሶማሊያን ግዛት በጦርነት የማስፋፋት ዘመቻ እያካሄደ የሚገኘው። ይህ አደጋ አፋጣኝ ብሄራዊ ምላሽ የሚያስፈልገው ደረጃ ላይ ደርሷል።

ይህ ቡድን ኢትዮጵያዊ ለምድ ለብሶ በተለምዶ ኦጋዴን ወይም የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በምንለው አከባቢ የተደረጀና ሳይድ ባሬ ይህንኑ አከባቢ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ያመቸው ዘንድ ያስቀመጠውን የፓለቲካ ቀመር ተከትሎ የሚሠራና በሳይድ ባሬ ደቀመዛሙርት የሚመራ መሆኑና ድንበርን በኃይል በመቀየር መሪህ የሚመራ ባንዳ መሆኑ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ግልፅ ልሆን ይገባል።

የቅርብ ተግባሩ እንደሚያሳየው የየዚህ ወራሪ ሃይል አላማ ቀስ በቀስ፣ ከዓመት ወደ አመት፣ incremental በሆነ መልኩ የመሬት ወረራውን የኦሮሞና የሱማሌ ክልል የድንበር ግጭት በማስመሰል ባዶ እጅን እያረሰና ከብት እያረባ በሀረር፣ በአርሲ፣ በባሌ እና በቦረና የሚኖረውን የኦሮሞ ህዝብ እየገደለ በርካታ ወረዳዎችን በመውረር ነገ ሱማሌ አገር ሰትሆን ከሶማሊያ ጋር ቀላቂለው ለሚመሰርቱት ታላቋ ሶማሊያ የግዛት መሠረት እየጠለ ስለመሆኑ የቡድኑ ተግባር በቂ ምስክር ነው።

የቡድኑን አከሄዲ እና የፓላቲካ ስልት አደገኛ የሚያደርገው የበግ ለምድ የለበሰ ቀበሮ መሆኑ ብቻ አይደለም። ቡድኑ በኢትዮጵያ መንግስት የሚደገፉና ቡድኑ በአጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች ላይ ወረራ ስፋፅም ምናልባትም የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ በቂ ብሄራዊ ውክልና እንዲኖረው የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማዳከም ይረዳ ይሆናል በሚል እምነት የምመሩ እያዪ በማያዩ፣ እየሳሙ በማይ ሰሙ የተወሰኑ short sighted እና self-defeatist policy በሚያራምዱ ወይም የዚህ ቡድን እንቅስቃሴ long term agenda በመይገባቸው የኢትዮጵያ ፓለቲከኞች አለማወቅ ተጠቅሞ ነገ ሁሉን ኢትዮጵያዊ የሚቆጭና የሚያደማ እኩይ ተግባሩን እየፈፀመ መሆኑ ነው።

ይሄ የpolicy እብደትና ድንቁርና በአስቸኳይ መቆም አለበት። ይህን በገዛ እጀችን በራሳችን ላይ የተከልነውን የባንዳ ሃይል በአስቸኳይ በማፉረስ፣ በወረራ የተያዛውን መሬት ለማስመለስና የኢትዮጵያን የግዘት ሉዓላዊነት ለመረገገጥ የሚከተሉትን የፓሊሲና ወታደራዊ እርምጃዎች በአስቸኳይ መወሰድ ይገባል።

1) ወራሪውንና የሰይድ ባሬ የጥፋት መልዕክተኛ የሆነውን የሶማሌ ልዮ ፓሊስ በአስቸኳይ ትጥቅ ማስፈታትና መበተን፣ የዚህ ጥፋት ቡድን መሪዎችን ለፍርድ ማቅረብ፣

2) የቡድኑ ጀሌዎችና ቅጥረኞች በሱማሌ ክልል በኩል ሰርገው በመግባት በሀረር፣ በአርሲ፣ ባሌና በቦረና የኦሮሚያ ዞኖች በህዝብና በንብረት ላይ የሚያደርሱትን ግድያና ዝርፊያ የሚከላከል በኦሮሚያ ክልል የሚተዘዝ የኦሮሚያ National Guard በአስቸኳይ መቋቋም፣ በልዩ ፓሊሱ ወረራ የተፈናቀለውን ህዝብ ወደ ቦተቸው መመለስ፣

3) የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት መከላከያ ሰራዊት በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መከከል ያለውን ድንበር እንዲያስከብር ተገቢውን እርምጃ መውሰድ፣ የኢትዮጵያን ደህንነት የመጠበቁን ስራ ለሌሎች out source ማድረግን ማቆም።

4) ከ1991 ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ በሚልዮን የምቆጠሩ የሱማሌ ስደተኞች አሁን በአገራቸው ሰላም እየሰፈነ ሰለሆነ ከመሃል አገርም ሆነ ከሱማሌ ክልል ወደ ሶማሊያ እንዲመለሱ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ከለጋሽ አገሮች ጋር በመታባበር መስራት። በፓለቲካ ምክንያት መመለስ የማይችሉ ስደተኞች የሰይድ ባሬና የሱማሌ ልዮ ፓሊስ አጀንዳ አራማጅ እንደይሆኑ ቁጥጥር ማድረግ፣

5) የኢትዮጵያ ሱማሌዎች የሶማሊያ ተስፋፊዎች አጀንዳ መስፈፀሚያ አንደይሆኑ እና በኢትዮጵያዊነታቸው ማንነታቸው ተከብሮ ኮርተው እንዲኖሩ እኩልነትና ፍትህ የሰፈነበት ፌድራል ስረዓት በኢትዮጵያ መዘርጋት ወይም አሁን በወረቀት ላይ ያለውን ተግባራዊ ማድረግ። ይህ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ፣ ብሄረሰቦች የሚደግፉትና የሚታገለሉላት አላማ ነው።

6) የኢትዮጵያ የፓለቲካ ሓይሎችም (በስልጣን ላይ ያለውን ድርጅትን ጨምሮ) በኢትዮጵያ ፍትህና እኩልነት እንዲሰፉን ለማድረግ የሚደረግን ህገዊ የፓለቲካ ትግል መከከል እና በሱማሌ ልዩ ፓሊስ አይነቶቹ አገር አጥፊ ቡድኖች መከከል ያለውን ልዩነት ለደጋፊዎቻቸውና ለሚከተላቸው ህዝብ መስገዘብና የኢትዮጵያ ህዝብ አገራዊ በሆኑ ጉደዮች ላይ አብሮ እንዲቆም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

የ#OromoProtests እና የ#AmharaProtests እንዳሳየን የኢትዮጵያ ህዝብ የውስጥ ችግሩን ከየትኞቹም የውጭ ሃይሎች እርዳታ ሳይሻ መፈታት ይችል። በ1966 አብዮትም የሆነው ይሄው ነው። አሁንም የተለየ ነገር የለም።