By ሳተናው

August 17, 2017 06:57

 


ተክሌ በቀለ

እንደርታ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ኣጠገብ የምትገኝ ቀበሌ ናት ብሎ ለማስተዋወቅ መጀመሩን የመረጃና እዉቀት ማነስ በዚህ ትልቅ ተቋም ይኖራል ብየ እንድገምት ኣድርኛል፡፡እንዲህ የህዝብን ቁጥርም ሆነ ኣካባቢን የሚያሳንስ ኣስተያየት ሊታረምም ይገባል፡፡ትልቅ ግዛትና ህዝብ ነዉ፤እንደርታ፡፡

እንደርታ እንዲህ እንደዛሬዉ በዚህ ኣገዛዝ ስሙ እንኳን እንዳይነሳ ከመደረጉ በፊት በንጉሱም ይሁን በደርግ በርካታ ወረዳዎችን ያቀፈ ትልቅ ኣዉራጃ የነበረ ሲሆን የነገስታቱ መናገሻም ነበር፡፡ሽሙ እንዳይነሳ በትግራዋይ ኣንድነት ስም የሚነግዱ ሃይሎች የቻሉትን ሁሉ ቢያደርጉም(ኣሁንም ኣጋዝያዉያን ነን ባዮችን ጨምሮ ጭፍለቃ ላይ ናቸዉ) ባህሉና ህዝቡ ኣሁንም እዛዉ ነዉ፡፡ኣሸንዳም በድምቀት የእንደርታዉያን፤የተምቤንና የከፊል ራያ ዓዘቦ እንዲሁም የሰቆጣ፣ ላስታ ላሊበላ፣ የራያ ቆቦ ባህል ነዉ፡፡ሌላዉ ዉሸቱን ነዉ፡፡የባህል ንጥቂያና ወረራ ነዉ፡፡ሃይማኖታዊ ይዞታ ቢኖረዉ የመስቀል ደመራ ባዓልም ይሁን ኣሸንዳ በኣኩሱም በደመቀ ነበር፡፡መስቀል በዓድግራትና በመቐለ/ጮምዓ በድምቀት የሚከበረዉ ባህላዊ ይዘቱ እየጎመራ ስለመጣ ነዉ፡፡መነሻዉ ሃይማኖታዊ ሊሆን ይችላል፡፡ኣሁንም በትግራይ ዉስጥ ባህሉ የመቐለ/እንድርታዉያን እንዲሁም የከፊሉ ራያና የተምቤን ባህል ነዉ፡፡በዚህ ባህል ላይ ራያ ዓዘቦ፤ኢሮብም ይሁን ኩናማ ባህላቸዉን ለማስተዋወቅ መሳተፋቸዉ ምልካም ነዉ፡፡ኢሮብ ኢሮብ፤ ራያም ራያ ነዉ! በትግራዋይ ኣንድነት ስም ማንነት ጭፍለቃ መቆም ኣለበት፡፡
መስቀል በጉራጌ፤በወላይታ፤በከምባታ፤በሃድያና በጋሞጎፋ በድምቀት ይከበራል፡፡ከምባታና ሃድያ ከ100 ኣመታት በፊት የሙስሊም መንግስታት ግዛቶች ነበሩ፡፡ዛሬ ደግሞ በብዛት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ እነደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ታድያ መስቀልን ሲያከብሩ መነሻዉ ምንም ይሁን ምንም ኣሁን ባህላቸዉ ስለሆነ ነዉ፡፡ (እግረ መንገድ!! ከነችግሮቹም ቢሆን የደቡብ መንግስት በብዝሃነት ጥበቃ ጉዳይ የተሸለ እንደሁነ ማየት ይቻላል፡፡ኣንደኛዉ ደፍጣጭ የትግራዩ ህወሓት ሲሆን በመቀጠል ኦህዴድ ይመስሉኛል፡፡ራእዩን ይበልጥ ከፍ በማድረግ ለማስቀጠል ደግሞ ኣግኣዝያን በሚባል ቡድን መቐለና ኣዲስ ኣበባ ከተማ ተቀምተዉ ፀረ ህዝብ ሃሳብ ሲያራምዱ ድጋፍ የተቸራቸዉ ህግ የማይጠይቃቸዉ ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ )

የሆነዉ ሁኖ የመቐለ/እንደርታ፤ተምቤንና የራያና(በከፊል ሁለቱም) እንዲሁም የላሊበላ፤የሰቆጣና ላስታ ልጃገረዶች መልካም የኣሸንዳ (የሻዳይ፣ አሸንድየና ሰላን) በዓል ይሁንላችሁ፡፡

ባህሉ በጋራ የነዚህ ኣካባቢ የህዝብ ልጆች ባዓል ሆኖ በኣለም እንዲመዘገብና ለሃገሬ የቱሪዝም መስህብ እንዲሆን ምኞቴ ነዉ፡፡ሌላዉ ሁሉ ዉሸቱን ነዉ፤ኣያገባዉም፡፡ሽመታ- የፖለቲካ!!